ዘ-ሐበሻ (ሰበር ዜና) ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ሞተው የኔ 25ኛ ዓመት የሢመት በዓል እንዲከበር አልፈልግም አሉ * በስደት ያለው ሲኖዶስ በሊቢያ ያለቁት ወገኖች “ሰማዕታተ ኢትዮጵያ በምድረ ሊቢያ” ተብለው እንዲታሰቡ ወሰነ
(ዘ-ሐበሻ) በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕጋዊ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ የ25ኛ ዓመት የሢመት በዓል ሰሞኑን እንደሚከበር ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ፓትሪያርኩ “ወገኖቼ በሊቢያ በደቡብ አፍሪካ እና በአረብ ሃገራት እያለቁ የኔ በዓል እንዲከበር አልፈልግም” አሉ:: የበዓሉ መርሃ ግብር ተቀይሮም መታሰቢያነቱ በሊቢያ ለሞቱት መታሰቢያ እንዲሆን ጠይቀዋል::
ሲኖዶሱ ዓመታዊ ጉባኤውን በባልቲሞር መካነ ሰላም ኢየሱስ ቤ/ክ ዛሬ ያካሄደ ሲሆን በሊቢያ በአይሲኤል የተገደሉት 28 ኢትዮጵያውያን ልክ ሰማዕታተ ናግራን ተብሎ እንደሚዘከሩት “ሰማዕታተ ኢትዮጵያ በምድረ ሊቢያ” ተብለው እንዲዘከሩ መወሰኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::
No comments:
Post a Comment