Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 29, 2015

በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸሙትን አሰቃቂ ድርጊቶች የሚያወግዙ ሰልፎችንና የሻማ ማብራት ስነስርአቶች ተካሄዱ


በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸሙትን አሰቃቂ ድርጊቶች የሚያወግዙ ሰልፎችንና የሻማ ማብራት ስነስርአቶች ተካሄዱ


ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባሳለፍነው ሳምንት በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ የሚቃወሙ ሰልፎች፣ የሻማ ማብራት ስነስርአቶችና ጸሎቶች በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእስያና በአውስትራሊያ ተካሂዷል። 
በለንደን ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓም በተካሄደው ከፍተኛ ተቃውሞ ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ የደረሱትን በደሎች አጥብቀው ኮንነዋል። ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ በስፍራው ተገኝቶ እንዳለው እስከ አንድ ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ከትራፋልጋር ስኩየር በመነሳት ወደ እንግሊዝ ፓርላማ አምርተዋል። በኒዉዚላንድ ኦክላንድ የኢትዮጵያ ትንሳኤ መወያያ መድረክ ባዘጋጀዉ የሻማ ሥነስርዓት ላይ ኢትዮጵያኑ የሻማ ማብራት ሥርዓት አካሒደዋል፡ ፡

በጃፓን ቶክዮ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ፣ በዙሪክ፣ በርን፣ ሴንት ጋለን፣ ባዝል፣በፈረንሳይ ፓሪስ፣ በሆላንድ አምስተርዳም፣ በአውስትራሊያ ፐርዝ ፣ በጀርመን ፍራንክፈርት ፣ በሉክሰንበርግ ፣በኖርዌይ አስሎ፡በግሪክየህሊና ጸሎት ተካሂዷል።
Ethiopians protested in Melbourne, Australia
Ethiopians anger in Australia Melburne 
በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በግብጽ እና በካይሮ በኩል ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመሩን ቢያስታውቅም፣ ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ትሪፖሊ ለሚገኘው የመንግስት ተወካይ ስልክ ደውለው ምላሽ
ማጣታቸውን ተናግረዋል። 
ግብጽ የሚገኘው ኢምባሲ የሚሰጠው የስልክ ቁጥር አይሰራም በማለት አቤቱታ እያቀረቡ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት ከ1 ሺ በላይ ወጣቶች፣ አብዛኞቹ ተፈትው ከ150 ያላነሱት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ ተቃውሞውን ያስነሱት ሰማያዊ ፓርቲና አንድነት ፓርቲዎች ናቸው ብሎአል። ሰማያዊ ፓርቲ የመንግስትን ክስ ወዲያው ውድቅ ሲያደርገው፣ አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ትዕግስቱ አወሉ አንዳንድ አባሎቻችን ከእኛ እውቅና ውጪ ሰልፍ ላይ
ተገኝተዋል ብለዋል። አቶ ትእግስቱ 1 የብሔራዊ ም/ቤት አባላችንና ሌላ 1 ጸሃፊ ሰልፉ ላይ መገኘታቸውን ከፖሊስ የምርመራ ሪፖርት ላይ ተመልክቻለሁ ብለዋል። የአቶ ትእግስቱ ንግግር በኤፍኤም ሬዲዮኖች እንዲራገብ የተደረገ ሲሆን፣ ንግግሩ ብዙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ማበሳጨቱ ታውቋል።

አዲሱ የአንድነት ፓርቲ የኢህአዴግ ተለጣፊ መሆኑን ከዚህ በላይ ማሳያ የለም በማለት የህዝብ አስተያየት በማሳባሰብ ዘጋቢያችን በላከው መረጃ ላይ ጠቅሷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials