Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, April 14, 2015

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የርሃብ አድማ መቱ

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የርሃብ አድማ መቱ
በማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው የሚገኙት ብርሃኑ ተክለያሬድና ፍቅረ ማሪያም አስማማው አብራቸው በታሰረችው እየሩስ ተስፋው ላይ እየተፈፀመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም የርሃብ አድማ መቱ፡፡ ብርሃኑና ፍቅረማሪያም ከትናንት የትንሳኤ በዓል ጀምረው የእርሃብ አድማ ያደረጉ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የገባላቸውን ምግብ እንዳልበሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
እየሩሳለም ተስፋው ከሳምንት በላይ ብቻውን እንድትታሰር ተደርጋ ከፍተኛ ምርመራ እየተደረገባት ሲሆን ከቤተሰቦቿ ጋር እንዳትገናኝ ተደርጋለች፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ ጥበቃ ፖሊሶች ቤተሰቦቿ ስለ እየሩስ በሚጠይቁበት ወቅት ‹‹መግባት አይቻለም›› ከማለት ውጭ ምክንያቱን እንደማይናገሩም ከቤተሰቦቿ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡
እነ ብርሃኑ እየሩስ ተስፋው ላይ እየተፈፀመ ያለው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እስካልቆመ ድረስ የርሃብ እድማቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
Like · Comment · 

No comments:

Post a Comment

wanted officials