Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, April 9, 2015

የኢንጂነር ይልቃል ፓስፖርት ተመለሰላቸው *አሁንም ከኤርፖርት የሚመልሳቸው ሃይል ይኑር አይኑር አይታወቅም



ዘ-ሐበሻ) የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርና በቅርቡ ከሃገር እንዳይወጡ ለሁለተኛ ጊዜ ፓስፖርታቸውን ተቀምተው የተከለከሉት ኢንጂነር ይልቃል ፓስፖርታቸውን የስር ዓቱ የደህንነት ሃይሎች እንደመለሱላቸው ታወቀ::

ኢንጂነር ይልቃል ባለፈው ሳምንት ከሃገር እንዳይወጡ በመከልከላቸው የተነሳ በዋሽንግተን ዲሲ እና በቦስተን የጠሩትን ሕዝባዊ ስብሰባ በስካይፕ ለማድረግ ተገደዋል:: በሌሎች የአሜሪካ ከተሞችም የተዘረጋላቸው ስብሰባም ወይ በአካል አልያም በስካይፕ እንደሚቀጥል ተገልጾ ነበር::

የሰማያዊ ፓርቲ የቅርብ ሰዎች ለዘ-ሐበሻ እንዳስታወቁት ኢንጂነሩ ፓስፖርታቸው የተመለሰላቸው ሲሆን አሁንም ከኤርፖርት የሚመልሳቸው ሌላ ሃይል ሊኖር ይችል ይሆናል የሚል ስጋታቸውን ይገልጻሉ:: በቅርቡ በቴዲ አፍሮ ላይ የተፈጸመውን ያስታወሱትና ለ3 ሳምንት ያህል ከሃገር እንዳይወጣ እንዳጉላሉት ያስታወቁት እነዚሁ ምንጮች ሃገሪቱን ማን እንደሚያዛት ስለማይታወቅ አንዱ ሲፈቅድ አንዱ የሚከለክልበት ዘመን በመደረሱ ነፃ አሳቢ ዜጎችን ፓስፖርት እየነጠቁ ከውጭ ጉዟቸው እንደሚያስተጓጉሉ ጠቁመዋል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials