በእኔ ዲ/ን አብርሃም ወርቁና ዲ/ን ዮሴፍ አባይ አስተባባሪነት ስድስት ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ይዘን በሰማዕታቱ በነኢያሱንና ባልቻ መኖርያቤት ከቀኑ 10:45 ሄደን አፅናንተን ተመልሰናል ቅዱስ ፓትርያርኩን ይዘን ለመሄድ ያደረግነው ሙከራ በኘሮግራም መደራረብ ምክንያት አልተሳካም ነገር ግን ልጆች ናቸው ብለው ሰሰይንቁን ማፅናናት ኃላፊነት አለብን ብለው ጥሪአችንን አክብረው 1ኛ/ብፁዕ አብነ ሉቃስ የሲኖዶሱ ዋና ፀሐፊና የሁመራ ሀ/ስ ሊቀ ጳጳስ 2ኛ/ ብፁዕ አብነ ማቲዮስ የኢ/ኦ/ተ ጠቅላይ ሥ/አስኪያጅና የወላይታ ዳውሮ ሀ/ስ ሊቀ ጳጳስ 3ኛ/ብፁዕ አብነ ቀሌምንጦስ የአዲስ አበባ ሀ/ስ ሊቀ ጳጳስ 4ኛ/ ብፁ አቡነ ሄኖክ የም/ወለጋና የቄሌም ወለጋ የአሶሳ ሀ/ስ ሊቀ ጳጳስ 5ኛ/ ብፁዕ አብነ ማቲያስ የካናዳ ሀ/ስ ሊቀ ጳጳስ 6ኛ/ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የለንደን ሀ/ስ ሊቀ ጳጳስ እነዚህን ስድስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ሟች ቤተሰብ ቤት በመገኘት ያፅናኑ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ሉቃስና ብፁ አብነ ማቲዮስ ልብ የሚነካ ትምህርተ ወንጌል አስተላልፎአል በነገው እለትም በቅ/ስላሴ ካቴድራል አጠቃላይ ፀሎተ ፍታት የሚደረግ ሲሆን በመላው ኢትዮጲያም አብያተ ክርስቲያናት ለ7 ቀን ምህላ ይደረጋል በየ 3 ሰአቱ ልዩነትም ደወል ይደወላል ሰማዕታቱም ይታሰባሉ አሁንም በረከታቸው ይደርብን።
No comments:
Post a Comment