Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, April 24, 2015

ኢህአዴግ የሞቱትን ወገኖች ክብር እያራከሰ ነው ሲል ሰማያዊ ወቀሰ

ኢህአዴግ የሞቱትን ወገኖች ክብር እያራከሰ ነው ሲል ሰማያዊ ወቀሰ
• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ጉዳዩን በዝምታ አያልፈውም›› አቶ ዮናታን ተስፈዬ
ኢህአዴግ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በሚል በሚጠራቸው ሰልፎች ሰማያዊን በማውገዝ ላይ መጠመዱንና ይህንም ሰማያዊ ፓርቲ በዝምታ እንደማያልፈው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ትናንት ሚያዝያ 15/2007 ዓ.ም በባህርዳር፣ ሆሳና እና ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰልፈኞቹ አይ ኤስን ሳይሆን ሰማያዊ ፓርቲን የሚያወግዙ መፈክሮችን ይዘው እንደወጡ የታወቀ ሲሆን አብዛኛዎቹ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ደም ከማፋሰስ ተግባሩ መቆጠብ አለበት›› የሚሉ መፍክሮችን ይዘው ወጥተዋል፡፡ 
ይህ የሆነው አዲስ አበባ ውስጥ መንግስት የጠራው ሰልፍ ላይ ሰልፈኞች መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ ምልሽ አልወሰደም በሚል ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ገና ፖሊስ ምርመራውን ሳይጨርስ ተቃውሞውን ያሰማው ሰማያዊ ፓርቲ ነው ብለው ከወነጀሉ በኋላ ፓርቲያቸው የያዘው አቋም እንደሆነ ኃላፊው ገልጾአል፡፡ አቶ ዮናታን ይህን የኢህአዴግ አቋምም ‹‹እጅግ አሳፋሪና አፀያፊ ነው›› ብሎታል፡፡ የባህርዳርና የሆሳና ሰልፈኞች ሰማያዊ ፓርቲን ለማውገዝ በያዟቸው መፈክሮች ፊታቸውን እንደሸፈኑ የገለፀው አቶ ዮናታን ሰልፈኞቹ በኢህአዴግ ተገድደው እንጅ አምነውበት እንዳልወጡ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት ሲያቅተው የሚነሱበትን ተቃውሞዎች ሰማያዊ ፓርቲና ድምጻችን ይሰማ የፈጠሯቸው አድርጎ መወንጀሉ ለስርዓቱም ሆነ ለሀገሪቱ አደጋ የሚፈጥር ነው ያለው አቶ ዮናታን ለአይ ኤስ አይ ኤስ ተብሎ የተጠራውን ሰልፍ ለራሱ የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ማዋሉ የሞቱትን ወገኖቻችን ክብር የሚያረክስ፣ ርካሽና ፀያፍ ፕሮፖጋዳ ነው ሲል ወቅሷል፡፡
ኢህአዴግ እንደ መንግስት መስራት ያለበትን ባለመስራቱ የሚነሱበትን ተቃውሞዎች ለመሸፈን እና አጀንዳ ለማስቀየስ ሲል በሰማያዊ ላይ እየፈጠራቸው ያሉትን ውንጀላዎች ፓርቲው በዝምታ እንደማያልፋቸውና ክስ እንደሚመሰርትም አቶ ዮናታን ገልጸዋል፡፡


Like · Comment ·  · 611924

No comments:

Post a Comment

wanted officials