Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, April 30, 2015

የ23ኛ ክፍለጦር፤ 1ኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሰራተኞች ገንዘብ እየያዙ በመጥፋት ላይ ናቸው



የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው በኢህአዴግ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እምነት ያጡ የ23ኛ ክፍለጦር፤ 1ኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሰራተኞች ገንዘብ እየያዙ በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።

በማዕከላዊ እዝ የ23ኛ ክፍለ ጦር አባላት ለበዓል ማክበሪያ እየተባለ ከነፍስ ወከፍ ወታደር 87 ብር ያለፍላጎታቸው እንደተቆረጠባቸው የገለጸው መረጃው ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ የተባለ የአንደኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሓላፊ ሃላፊነቱን ተጠቅሞ የፋይናንስ ካዝና በመክፈት የሬጅመንቱን አምሳ ሁለት ሽህ አምስት መቶ (52,500) ብር ገንዘብ ይዞ ከዝባን ገደና ተነስቶ ከሽራሮ ከተማ በመኪና ተሳፍሮ ለማምለጥ ሲሞክር እንደተያዘ ለማወቅ ተችሏል።

በእዙ ውስጥ የሚገኙ የሰራዊት አመራሮች በየወቅቱ ምክንያቶችን እየፈጠሩ የሰራዊቱን ደመወዝ በመቁረጥ ለግል ፍላጎታቸው ማሟያ እያዋሉት ስለሚገኙ እያንዳንዱ ወታደር ተቆራርጣ በእጁ ከምትደርሰው አነስተኛ ደመወዝ ቤተሰቡን ሊያግዝ ይቅርና ለራሱም መሆን እንዳልቻለ የደርሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል ሲል ደህሚት ድምጽ ዘግቧል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials