Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, April 26, 2015

በጨርቆስ አካባቢ የሚኖሩ ሙስሊም ወጣቶች ሃዘን ለደረሰባቸው ቤተሰቦች የአርባሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ




ፍትህ ራዲዬ /ዕለተ ቅዳሜ ሚያዚያ 17/2007
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩


በሊቢያ ልጆቻቸው በግፍ የተገደሉባቸውን ኢትዬያውያንን ለማፅናናት የጨርቆስ አካባቢ ሙስሊም ወጣቶች ሃዘን ለደረሰባቸው ቤተሰቦች የ 40.000 ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች አስታውቀዋል፡፡

በሊቢያ በግፍ ከተገደሉት ኢትዬጲያውያን ክርስቲያኖች መካከል 5 የሚሆኑት የጨርቆስ አካባቢ ተወላጆች መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን በጨርቆስ አካባቢ የሚኖሩ ሙስሊም ወጣቶችም በሰፈራቸው ወጣቶች ላይ የደረሰውን አሳዛኝ ግድያ በማውግዝ ለቤተሰቦቻቸው የ 40.000 ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልፆል፡፡

ሙስሊም ወጣቶቹ በሃገራችን ለረጅም አመታት የቆየውን የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህላችንን ህያው በማድረግ ኢስላም በመልካም መረዳዳት የሚያዝ መሆኑን በተግባር ለተጎጂ ቤተሰቦች አቅማቸው የፈቀደውን ወጣቶቹ ገንዘብ በማዋጣት አጋርነታቸውን ማሳየታቸው ተዘግቧል፡፡

መንግስት በሊቢያ የተደሉትን ወገኖች ለግሉ የፖለቲካ ፍጆታ በማዋል በሙስሊም እና በክርስቲያኑ መካከል የማየበርድ እልቂት ለምፍጠር ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ በሚገኝት በዚህ ወቅት ህዝበ ሙስሊሙ እና ክርስቲኑ ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ መደጋገፉን በማጠናከር በሃዘን እና በደስታ ጊዜ በጋራ አየተረዳዳ ይገኛል፡፡

የጨርቆስ አካባቢ ሙስሊም ወጣቶች ከራሳቸው የሰበሰቡትን 40.000 ብር ለ 5ቱ ተጎጂ ቤተሰቦች ሃዘናቸውን በመግለጽ አላህ መፅናናት እና ብርታቱን እንዲሰጣቸው በመማጸን ገንዘቡን እንዳከፋፈሏቸው ተዘግቧል፡፤

ይህ ድንቅ የአብሮነት እና የመረዳዳት ባህል በመንግስት እኩኝ በሆነ ሰይጣናዊ የፕሮፖጋንዳ የማሸረሸር መሆኑን የጨርቆስ አካባቢ ሙስሊም ወጣቶች በተግባር አሳይተዋል፡፤

የጨርቆስ አካባቢ ሙስሊም ወጣቶች ሃይማኖት ሳይገድባቸው አደጋ ለደረሰባቸው ለክርስቲያን ወገኖች ያደረጉት ድጋፍ ለሁሉም ኢትዬጲያዊ ትልቅ የአብሮነት መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው፡፡

የኢትዬጰያን ህዝብ በእምነት ከፋፍሎ ለማፋጀት የሚደረገው ሴራ አይሳካም!!

አላሁ አክበር!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials