የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሰቆቃ ጩኸት ከያቅጣጫው መሰማቱ በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡
የህወሓት አገዛዝ የፈጠረው በእጅጉ የተውሰበሰበ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለስደት የዳረጋቸው ኢትዮጵያዊያን የረገጡት መሬት ሁሉ ሲኦል ሆኖባቸው የድረሱልኝ ተማፅኖ ጥሪያቸውን ያለማቋረጥ እያሰሙ መሆናቸውን መገናኛ ብዙኃን በሰፊው እየዘገቡት ይገኛል፡፡ ማህበራዊ ድረ ገፆችንም እያነጋገረ ያለው የወቅቱ አንገብጋቢ ርዕስ ጉዳይም ይህ ነው፡፡
ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የመን ውስጥ ከላይ በአውሮፕላን ቦምብ ከታች በሞርታር እየተቀጠቀጡ ታቹ እሳት ላዩ እሳት ሆኖባቸው “የመውጫ ያለህ! ወገን ድረስ” እያሉ የፍዳ ድምፃቸውን ለዓለም ህዝብ በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡
ቤይሩት ውስጥ ተገድለው አስከሬናቸው በየጎዳናው ተንጠባጥቦ እየተገኘ ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካ ውስጥም እንዲሁ፡፡
በታንዛንያ ወንዶች ሳይቀር እየተደፈሩ ነው፡፡
ኬኒያ የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በፖሊስ ቆመጥ እየተደበደቡ፣ በወታደር ክላሽን ኮቭ አፈሙዝ አየተደቁና ሴቶች እየተደፈሩ በመታፈስ ወደ ወህኒ በመጋዝ ላይ መሆናቸው በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን እየተዘገበ ነው፡፡
ለእነዚህ የግፍ ገፈትን እየተጎነጩ በተለያዩ አገሮች በጥገኝነት ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደት መንስኤ የሆነው ባለዝሆን ጆሮው የህወሓት አገዛዝ ለኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ አያገባኝም ብሎ ከሚያልፍበት ዓለም በሙሉ ያወቀው አስነዋሪ ባህሪው ውጭ በመራመድ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ ግፍና በደል ለሚፈፅሙ አካላት ተባባሪ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡
ስለሆነም በፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ችግር ምክንያት አገራቸውን ጥለው ለመሰደድ የበቁ ኢትዮጵያዊያን በየአገሩ የሚደርስባቸውን ሰቆቃ በየጊዜው በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት የሚከታተለው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያዊያን ተባብረው በአንድነት በመቆም የድህነታቸው፣ የውርደታቸውና የመከራቸው ብቸኛ ምንጭ የሆነውን የህወሓት አምባገነን ስርዓት ባፋጣኝ በመገርሰስ ከስቃይ ተገላግለው እፎይ ሊሉ ይገባል፡፡ በማለት አስተያየቱን እየሰጠ ነው፡፡
የህወሓት አገዛዝ የፊታችን ግንቦት 16 2007 ዓ.ም የሚያደርገው የይስሙላህ ምርጫ ውጤትና እሱን ተከትሎ ይከሰታል ብሎ የሰጋውን ህዝባዊ አመፅ ልክ እንደ 1997 ዓ.ም ግንቦት ሰባቱ ምርጫ ወቅት በጠብመንጃ ጉልበት በመደፍጠጥ ሊቀለብሰው ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡
የህወሓት አገዛዝ ምንጊዜም ቢሆን በየአምስት ዓመቱ የሚያደርገው ምርጫ ድራማ መሆኑና ሁሉንም ተግባር ጡንቻውን ብቻ እየተጠቀመ የሚያስፈፅም መሆኑ የታወቀ ቢሆንም ቅሉ ያሁኑ ወታደራዊ ዝግጅት መቼም ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ እንደሆነና የኢትዮጵያ ከተሞች በደም መንኩሶ ቀይ የጭካኔ አክሊል በደፋው ከክላሽን ኮቭ በተጨማሪ ባለሳንጃና ባለገመድ በሆነው አግአዚ ኮማንዶ ጦር ሊወረሩ ምደባው መጠናቀቁን ለአርበኞች ግንቦት 7 ሬድዮ የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡
የህወሓት አገዛዝ እያደረገው ያለው እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ዝግጅት የምርጫውን ድራማ ተከትሎ ህዝባዊ አመፅ ይኖራል ከሚል ፍርሃትና በየበረሃው በመመሸግ አድፍጠው የሚገኙ ጠብመንጃ የታጠቁ የነጻነት ኃይሎች ጡንቻ መፈርጠምና የትኛውንም የተደራጀ ኃይል ድባቅ መትቶ የመደምሰስ አቅም እየፈጠሩ መምጣት ከ97 ምርጫ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ህዝባዊ አመፁን በቀላሉ ማስቆም እንደማይችል በማመኑ ነው፡፡
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከወታደራዊ ዝግጅቱ በተጨማሪ እሱ ካቋቋማቸው የሀሰት ተቃዋሚነት ካባ ከደረቡት ሀሳዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ውጭ ያሉት ለህዝብ ነፃነት የሚታገሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትን በማሰር፣ በመደብደብና በማስፈራራት እንዲሁም በመገደል እያዋከበ ይገኛል፡፡ ብዙዎቹ ለህዝብ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫው ራሳቸውን እንደሚያገሉ እየገለፁ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተዘዋዋሪ መንገድ በሚደርስባቸው ተዕፅኖ ምርጫ እንደማይወዳደሩ ያሳወቁትም ቢሆን ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
በመሆኑም ህወሃት በዚህ የማዋከብ እኩይ ምግባሩ ከቀጠለ የመጭው ግንቦት ምርጫ ሙሉ በሙሉ በህወሓትና በጥቅም ለህወሓት ባደሩ ሀሳዊ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የሚደርግ ነፃ ትግል ውድድር ይሆናል

No comments:
Post a Comment