በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በወላይታ ዞን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን ያቀረቡ 8 የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዞኑ እየደረሰባቸው የሚገኘው አፈና እና በደል መፍትሄ ካልተሰጠው ራሳቸውን ከመጭው ግንቦት 2007 ዓ.ም ምርጫ ራሳቸውን ሊያገሉ እንደሚችሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ፣ ለምርጫ ቦርድና ሌሎች የመንግስት ተቋማት ባስገቡት ደብዳቤ አስጠንቅቀዋል፡፡
ከመጭው ምርጫ ራሳቸውን ሊያገልሉ እንደሚችሉ ያስጠነቀቁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰማያዊ፣ የኢትዮጵያ ፍትሕና ዴሞክራሲ ሃይሎች ግንባር (ኢፍዴሃግ)፣ የወላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወሕዴግ)፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ናቸው፡፡

ማስጠንቀቂያውን ያቀረቡት ፓርቲዎች ለምርጫ ምቹ የሆነ አጋጣሚ እንዳለ በሚዲያ የሚገለፀው ትክክል እንዳልሆነ፣ ያለ ገደብ መብት የሰጠው ገዥው ፓርቲ ሰሆን በእነሱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና እና በደል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል፡፡ ፓርቲዎቹ አክለውም ምህዳሩ እጅግ የጠበበ መሆኑን በየጊዜው አቤቱታቸውን ለምርጫ ክልሎችና ለጋራ ምክርቤት ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙና በአባላቶቻቸው ላይ የሚፈፀመው በደል ከአቅማቸው በላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
‹‹የወረዳና የዞን የምርጫ አስተባባሪዎች የገዥውን ፓርቲ ድምጽ ከመስማት በስተቀር ምንም አይነት ውሳኔ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡›› ያሉት ፓርቲዎች በዚህም ምክንያት ምህዳሩ እጅግ መጥበቡንና ከችግር ላይ ችግር እየተደራረበ በመምጣቱ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸውን በደብዳቤው ገልጸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment