Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 29, 2015

የኢህአዴግን የምርጫ ምልክት ቀደዋል የተባሉ ግለሰብ በአንድ አመት እስር ተቀጡ

የኢህአዴግን የምርጫ ምልክት ቀደዋል የተባሉ ግለሰብ በአንድ አመት እስር ተቀጡ

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ቀናው ክንዴ የተባሉ የከተማው ነዋሪ  ሚያዚያ 6/2007 ዓም ከጧቱ ሁለት ሰአት ላይ የብአዴን ኢህአዴግን የምርጫ ምልክት ቀደዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
ግለሰቡ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ በመሆናቸው ብቻ የሃሰት ክስ እንደተመሰረተባቸው ቢናገሩም የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በማግስቱ ሚያዚያ 7/2007 ዓም በዋለው ችሎት ግለሰቡ በአንድ አመት እስር እና በሁለት አመት ገደብ እንዲቀጡ ወስኗል።
ፍርድ ቤቱ የሰጠው ፈጣን ውሳኔ ጉዳዩ ፖለቲካዊ መሆኑን ለግለሰቡ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ተናግረዋል።


------------------------------------------------------------
የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተሮች በገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ሆን ተብለው እየተቀደዱበት እንደሆነ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፀ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የለጠፋቸው ፖስተሮችን የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እየተከታተሉ እንደቀደዷቸውና ላያቸው ላይ ማስታወቂያ እንዲለጠፍባቸው እየተደረገ መሆኑን አቶ ዮናታን ገልጸዋል፡፡
http://zethiopians.blogspot.com/2015/04/blog-post_32.htm

‹‹ፖስተሮቹ የተቀደዱት አንድ ቦታ ላይ አይደለም፡፡ በአሁኑ ወቅት ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ እያደረገ የሚገኘው ገዥው ፓርቲ ሆን ብሎ እየተከታተለ እያስነሳ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የሰማያዊ ፖስተሮች ሲቀደዱ የኢህአዴግ ፖስተሮች ላይ ግን ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም፡፡ ይህ ከፍርሃቱ የመነጨ ነው›› ያለው አቶ ዮናታን ተስፋዬ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች የሰማያዊ ፓርቲን ፖስተሮች እየቀደዱ ከህዝብ እንዳይደርስ ለማድረግ ቢጥሩም በህዝቡ ትብብር አማራጫቸውን በማቅረብ ላይ በመሆናቸው ገዥው ፓርቲ ባሰበው መልኩ እንቅፋት መፍጠር እንዳልቻለ አስታውቋል፡፡

‹‹ውንብድና ነግሷል›› ያለው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ሆኖም ሰማያዊ ይህን የገዥ



No comments:

Post a Comment

wanted officials