Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 15, 2015

በትግራይ አብይ ዓዲ የአረና አባላት ናችሁ በሚል እየታሰሩ መሆኑ ተሰማ

በዓብይ ዓዲ ከተማ ልዩ ስሙ ዓዲ ግዲ በተባለው አካባቢ የሚኖሩ ወገኖቻችን የአረና አባላት በመሆናቸው ብቻ እየታሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል ሲል ደህሚት ዘገበ::
ምንጮቹን ጠቅሶ የዘገበው ደህሚት በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ዓብይ ዓዲ ከተማ ልዩ ቦታው ዓዲ ግዲ በተባለው አካባቢ የሚኖሩ የአረና ድርጂት አባላት ምንም የሰሩት ወንጀል ሳይኖራቸው ከመኖሪያ ቤታቸው የስርዓቱ ተላላኪ ፖሊሶች ያለምንም ህጋዊ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እያሰሩ እየወሰዷቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል::
መረጃው ጨምሮም ዮናስ ገብረአምላክ ተላ የተባለ የአረና ድርጅት አባል መጋቢት 18/ 2007 ዓ/ም ከጧቱ 2።30 ከመኖሪያ ቤቱ ፖሊሶች ትፈለጋለህ በማለት እንደወሰዱት የገለፀው መረጃው ይህን ህጋዊነት የሌለው ተግባራቸውን ይታዘቡ የነበሩ ቤተሰቦቹ ለምን ታስሩታላችሁ? ብለው በጠየቁበት ጊዜ ምርመራ ካደርግን በኋላ እንነግራችኃለን በማለት ወስደው በከተማዋ ቀበሌ 03 እንዳባዴራ በተባለው ፖሊስ ጣቢያ አስረውት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣

No comments:

Post a Comment

wanted officials