Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, April 4, 2015

የታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች የእንግሊዝን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከሰሱ:






በሕገወጥ መንገድ ከየመን አየር ማረፊያ ታፍኖ ወደ ኢትዮጵያ ከተወሰደ በኋላ ኢሰብአዊ በሆነ አያያዝ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ቶርች በመደረግ ለከፍተኛ ስቃይ ሲዳረግ የእንግሊዝ መንግስት ዜጋውን ሊያስፈታ ካለመቻሉም በላይ ከፍተኛ ንዝህላልነት አሳይቷል ጉዳዩንም ሊከታተል በጎ ፈቃደኝነት አላሳየም በማለት የታጋይ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች የእንግሊዝን የወጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሃሞድን መክሰሳቸው ታውቋል::


ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ቶርች እየተደረገ ነው ብለዋል ቤተሰቦቹ የእንግሊዝ መንግስት የውጪ ጉዳይ ቢሮ ምንም አይነት ጉዳዩን ሊፈታ የሚችል አጥጋቢ እርምጃ ባለመውሰዱ ታጋይ አንዳርጋቸው በማይታወቅ ቦታ ታስሮ ከማንም ጋር እንዳይገናኝ መደረጉ እየታወቀ እያለ አትኩሮት በሚኒስትሩ የተነፈገው ሲሆን ከዚህ ቀደም የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለጉዳዩ አትኩሮት አልሰጡም በመባል በባለስልጣናቶቻቸው በጥብቅ መወቀሳቸው ይታወሳል::የእንግሊዝ መንግስት እርዳታ አቋረጥኩ ቢልም ከ350 ሚሊዮን ፓውንድ ለወያኔ መንግስት በእርዳታ እንደሚሰጥ ታውቋል::

ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በጁን 23 2014 ከዱባይ ወደ አስመራ በሚበርበት ወቅት ለትራንዚት ካለፈበት የየመን ከተማ ሰንአ ውስጥ በወያኔ የደህንነት ሃይሎች ታፍኖ ወደ አዲስ አበባ መወሰዱ የሚታወስ ነው::

No comments:

Post a Comment

wanted officials