ወጣቱ የቪኦኤ ጋዜጠኛ ስሙን እንዲደብቅለት ከተማፀነ በኃላ እንዲህ አለ –
”….እኔ ያለሁት ትሪፖሊ ውስጥ ነው።አሁን ከግማሽ ሰዓት በፊት ፊታቸውን የተሸፈኑ
ሰዎች እኔ ወደምኖርበት ግቢ ገቡ እና ወደ 40 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ይዘው በመኪና ሄዱ።ከተወሰዱት ውስጥ በቅርቡ ኦፕራሲዮን የሆነች እና ነፍሰ ጡር አለችበት።
እነማን እንድሆኑ ማወቅ አልቻልኩም።እኔ ተደብቄ ነው ያመለጥኩት።
እዚህ እስላም እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያንን ሊለያዩን ሞክረው ነበር።ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እሪ! ብለው አለቀሱ አንለይም አሉዋቸው።ከዛ ተዉን……ሊብያ ውስጥ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለእኛ ህይወታቸውን ነው የሰጡት።እንዴት ብዬ እንደምነግርህ አላውቅም አሁን ወደ ጣልያን የሄዱት ሁሉ ያውቃሉ።” ካለ በኃላ ጋዜጠኛው ”በግድ እስልምና እንድትቀበሉ ትገደዳላችሁ?”
የሚል ጥያቄ ሲያቀርብለት ወጣቱ ሲመልስ እንዲህ አለ – ”አዎን! እራሴም ደርሶብኛል እንጂ።እኔን እና አንድ ከትግራይ የመጣ ልጅ ቤንጋዜ ውስጥ ወደ እስልምና ተቀየሩ ብለው በኤሌክትሪክ ጠበሱን አንቀየርም ስላልናቸው ጥለውን ሄዱ..”