“ቀጨኔ መደሀኒዓለም አካባቢ ያለ ድልድይ ለዓይነስውራን ሞት ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ሸገር ሬዲዮ ዘገበ።
መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንድ ራዲዮው ዘገባ ትናንትና አንዲት ወጣት አይነስውር ድልድዩን ስትሻገር ገደል ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል።
ይህ ቀጭኔ መድህኒ ዓለም አካባቢ ያለው ድልድይ በቀኝና በግራ በኩል አደጋ መከላከያ ድጋፍ የሌለው በመኾኑ ለሰዎች መጥፋት ምክንያት እየሆነ መምወጣቱን የ አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አካል ጉዳተኞችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ከደረጃ በታች የሆኑ ድልድዮች በከተማው የተለያዩ ቦታዎች በብዛት እንደሚገኙ ይታወቃል።
ድልድዮቹን በባለቤትነት ወስዶ ያስራው የመንገዶች ባለስልጣንም ሆነ የክፍለ ከተማው መስተዳድር በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። በኢትዮጵያ 1.2ሚሊዮን ዓይነስውራን የሚኖሩ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ደግሞ 1ነጥብ 4 በመቶ ያህሉ ያህሉ
ዓይነስውራን መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ
No comments:
Post a Comment