Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, August 16, 2018

የፈረንሳይ ፖሊስ በበጎ ፍቃደኞች ላይ ጥቃት ያደርሳል ተባለ


የፈረንሳይ ፖሊስ ለስደተኞች የሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠት በተሰማሩ በጎ ፍቃደኞች ላይ የኃይል ጥቃት እና ወከባ እንደሚፈጽምባቸው ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል። በከተሞቹ የሚገኙ አራት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ባለፈው ሳምንት የፖሊስን ድርጊት የሚያወግዝ ጠንከር ያለ ዘገባ ለፈረንሳይ መንግስታዊ የሰብዓዊ መብት ተቋም አቅርበዋል።
    
አውዲዮውን ያዳምጡ።03:50

የፈረንሳይ ፖሊስ በበጎ ፍቃደኞች ላይ ጥቃት ያደርሳል ተባለ

ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ መሻገር የሚሹ ስደተኞች በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ ካሌ እና ዳንከርክ ሆነው ዕድላቸውን ይጠባበቃሉ። በእነዚህ ሁለት ከተሞች ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንን ጨምሮ ቁጥራቸው ከ1000 እስከ 1500 የሚገመቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቀናትን እያሳለፉ ይገኛሉ። የፈረንሳይ ፖሊስ ለእነዚህ ስደተኞች የሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠት በተሰማሩ በጎ ፍቃደኞች ላይ የኃይል ጥቃት እና ወከባ እንደሚፈጽምባቸው ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል።
በከተሞቹ ሰብዓዊ እርዳታ በመስጠት ላይ ያሉ የሚገኙ አራት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ባለፈው ሳምንት የፖሊስን ድርጊት የሚያወግዝ ጠንከር ያለ ዘገባ ለፈረንሳይ መንግስታዊ የሰብዓዊ መብት ተቋም አቅርበዋል። ቅሬታው የቀረበበት የፐርፌ ፓደ ካሌ ግዛት አስተዳደር ግን የማህበራቱን ክስ አጣጥሎታል።
ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  https://www.dw.com/am/
ሃይማኖት ጥሩነህ
ተስፋለም ወልደየስ
ሂሩት መለሰ

“የወልቃይትን ጉዳይ ብንሸሸው፣ ብንሸፋፍነው ሊተወን አልቻለም” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተናገሩ።


“የወልቃይትን ጉዳይ ብንሸሸው፣ ብንሸፋፍነው ሊተወን አልቻለም” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተናገሩ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 07 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይህን ያሉት፤ ከአማራ ክልል ምሁራን ጋር በባህር ዳር ከተማ እያደረጉት ባለው ውይይት ላይ ጉዳዩን አስመልክቶ ለተሰነዘረባቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ነው።
ከተሳታፊ ምሁራኑ መካከል አንዱ “የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነታችን ይከበር በማለት ፌዴራል መንግስት ድረስ እየሄደ ጥያቄ ሲያቀርብ ከላይ የሚሰጠው ምላሽ ግን ‘’ህወሓትን ጠይቁ” የሚል ነው። በወልቃይት ጉዳይ የብአዴን አቋም ምንድነው?” በማለት ነው ጥያቄ የሰነዘሩት።
ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ በወልቃይት ጉዳይ ብአዴን እስካሁን ዋነኛ ጠያቂ እንዳልነበረም አምነዋል።
“ይሁንና የወልቃይትን ነገር ብንሸሸው፣ብንሸፋፍነው፣ ምን ብንለው መሄጃ የለንም” ያሉት አቶ ገዱ “መፍትሔው ያ ህዝብ የፈለገውን ማንነት እንዲመርጥና እንዲከበርለት ነጻነት መስጠት ነው” ብለዋል።
“የወልቃይት የማንነት ትያቄ ከአማራ ህዝብ ጥያቄ በላይ የሌላም ሆኗል” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ሕዝቡ በነጻነት እንዲወስን ከማድረግ የተሻለ መፍትሔ እንደሌለ አስረድተዋል። ወልቃይት የትግራይ ክልል ግዛት ነው የሚል አቋም የሚያራምደው ህወሃት፣ ከአሁን በኋላ በወልቃይት ጉዳይ ምንም አይነት ጥያቄ መነሳት የለበትም በማለት ደጋግሞ እያስጠነቀቀ ይገኛል።
አንዳንድ የድርጅቱ አባላትና ካድሬዎች ሳይቀሩ “ከእንግዲህ ወልቃይትን የሚነካ ካለ ለጦርነት ዝግጁ ነን” እያሉ በማህበራዊ ሚዲያው መቀስቀስ ጀምረዋል። በማንነት ጥያቄ ምክንያት በርካቶች መስዋዕት የከፈሉበት የወልቃይት ጉዳይ ባለፊት ዓመታት በአማራ ክልል ለተቀጣጠለው ሕዝባዊ ትግል ዋና መነሻ መሆኑ ይታወቃል።
ጉዳዩ በወቅቱ ለነበረው የአቶ ኃይለማርያም አስተዳደር ጭምር ራስ ምታት በመሆኑ በጥያቄው ዙሪያ ብአዴን እና ህወሓት እንዲወስኑ የሚል መመሪያ ከማውረድ አልፎ ውሳኔ ማሳለፍ ሳይችል ቀርቷል።
ከዚያም በቀድሞው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር በአቶ ዓባይ ወልዱ ጫና ወልቃይት የትግራይ እንደሆነ መወሰኑ ቢገለጽም ጉዳዩ ሲብላላ ቆይቶ ወደ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ዶክተር አብይ ተላልፏል።
ዶክተር አብይ በመቀሌው እና በጎንደሩ ጉብኝታቸው ከገጠሟቸው ፈታኝ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ይኸው የወልቃይ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። መቋጫው ምን ይሆን? የሚለው፣ ዛሬም የብዙዎችን ቀልብ ሰቅዞ እንደያዘ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ክልል የተፈጠረ አለመረጋጋትን ተከትሎ በክልሎች መካከል ግልጽ ወሰን እንደሌለ በማውሳት እና አሁን ያለው አከላለል አገሪቱን ‘’ጠቅሟታል?’’ ወይስ ‘’ጎድቷታል?’’ የሚለውን ጉዳይ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ አወቃቀሩ ጉዳት ካለው እንደሚከለስ በመግለጽ ሕዝቡ አገራዊ አንድነቱ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ቢያሣስቡም፣ ቀደም ባለው ጊዜ በክልሎች መካከል የተፈጠሩ ግጭቶች እልባት ሊያገኙ አልቻሉም።
ይልቁንም የነጻነት ጸሀይ ብልጭ ማለቷን ተከትሎ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አገራዊ ጥሪና መልዕክት በተጓዳኝ ዜጎችን በማፈናቀል፣ ድንበር በማስመርና ካርታ በመንደፍ በብሔሮችና በክልሎች መካከል የሚደረጉ ፉክክሮችና ሽኩቻዎች እዚህም፣ እዚያም እየተስተዋሉ ነው።

የአፋር መንፈሳዊ መሪ ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ከስደት ተመለሱ

ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ከስደት ተመለሱ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010)  የአፋር መንፈሳዊ መሪ ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ከስደት ተመለሱ።በከሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ጋር የአፋር ሕዝብ ፓርቲ መሪ ዶ/ር  ኮንቴ ሙሳ እንዲሁም የአፋር ሰብዓዊ መብት ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድም  በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
በተመሳሳይ ዜና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮችም ዛሬ  ወደ  ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
ከአምስት አመታት በፊት የሱልጣን አሊ ሚራህን ማለፍ ተከትሎ፣ የሱልጣን ማዕረጉን የወረሱትና ባዕለ-ሲመታቸውን በአፋር ክልል በአሳይታ   ከተማ  ያካሄዱት ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ  ሥልጣን ላይ ካለው መንግስት ጋር ባለመስማማት እና  በሕዝብ ላይ የሚደርሰወን በደል በመቃውም ከሃገራቸው ከተሰደዱ ጥቂት ኦመታትን አስቆጥረዋል።
በውጭ ሃገር ቆይታቸው ለአፋር ሕዝብ በጥቅል ለኢትዮጵያውያን መብት ሲታገሉ  መቆየታችው የተገለጸው  ሱልጣ ሃንፍሬ አሊሚራህ እና በርሳቸው የተመራው ልኡክ ዛሬ   አዲስ አበባ ሲደርስ የፌደራል እና የአፋር ክልል ባለሥልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ከአምስት ዓመት በፊት  በአሳይታ በዓለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ  የጅቡቲውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ጨምሮ 11 ሚኒስትሮች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ አፋሮች ከኤርትራና ከጅቡቲ በክብረ-በዓሉ ሲገኙ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት አለመሳተፋቸውን ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በበዓለ ሲመቱ ላይ አለመገኘት ብቻ ሳይሆን  ኢትዮጵያውያን አፋሮች እንዳይገኙ የተለያዩ ተፅዕኖ ማድረጋቸውን እንዲሁም ሂደቱን ለማደናቀፍ 2 ሚሊዮን ብር መመደባቸውንም ከዓመት በፊት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በዝርዝር ተመልክተዋል።
አፋሮች  በሁሉም መስክ ግፍ እና በድል ሲፈጸምባችው መቆየቱን  እንዲሁም ከፍተኛ የሃብት ምዝበራ መካሄዱንም መግለጻቸው አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባለፈወ ሳምንት የሰላም ስምምነት የተፈራረመው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ልኡካን ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።  የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና ቃል አቀባይ በሆኑት  በአቶ ቶሌራ አዳባ የተመራው ልኡክ አዲስ አበባ ሲገባ የኦህዴድ እና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት አቀባበል አድረገውለታል።
የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በቀርቡ ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ልኡካን ቅዳሜ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል ።
የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮችን የጨመረው የአርበኞች ግንቦት  ቡድን በቅረቡ አዲስ አበባ እንድሚገባም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል።

Wednesday, August 15, 2018

በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ ጎርፍ በመግባቱ የበረራ መዘግየት አጋጠመ፡፡


በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ #ጎርፍ_በመግባቱ የበረራ መዘግየት አጋጠመ፡፡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮለኔል ወሰንየለህ ሁነኛው እንደገለፁት፥ በትራፊክ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ ጎርፍ የገባው ሌሊት 9 ሰዓት ላይ ነው። በዚህም ምክንያት በአውሮፕላን ማረፊያው የበረራዎች መዘግየት ያጋጠመ ሲሆን፥ የተወሰኑ አውሮፕላኖችም #በአቅራቢያ (?) በሚገኙ የአውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ ተደርጓል ነው ያሉት። #FBCሮፕላን ማረፊያው የበረራዎች መዘግየት ያጋጠመ ሲሆን፥ የተወሰኑ አውሮፕላኖችም #በአቅራቢያ (?) በሚገኙ የአውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ ተደርጓል ነው ያሉት

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ሰራተኞች ወደ ስራቸው መመለስ አለመቻላቸውን ተናገሩ

በሽብር ወንጀል ተከሰው በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ሰራተኞች ወደ ስራቸው መመለስ አለመቻላቸውን ተናገሩ

በሽብር ወንጀል ተከሰው በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ሰራተኞች ወደ ስራቸው መመለስ አለመቻላቸውን ተናገሩ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአማራ ክልል ነዋሪ የሆኑ ሃሳባቸውን በመግለጻቸው በሽብርተኝነትና በተለያዩ ወንጀሎች ታስረው በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ ከደረሰባቸው በሁዋላ ከእስር የተፈቱት የመንግስት ሰራተኞች፣ ቀድሞ ወደ ነበሩበት የስራ ቦታ መመደብ ባለመቻላቸው ለችግር መደረጋቸውን ለኢሳት ተናግረዋል።
በአርበኞች ግንቦት7 ስም ተከሶ 5 አመታት ከ6 ወር በእስር ቤት ያሳለፈው አቶ አሸናፊ አካሉ እንደገለጸው፣ መንግስት አሸባሪው እኔ ነኝ ብሎ ካመነ በሁዋላ፣ ለእኛ አስፋለጊውን የሞራል ካሳ ክሶና የአለፉትን ክፍያዎች አስቦ በመክፈል ወደ ስራችን መመለስ ሲገባው፣ ይህን ባለማድረጉ፣ ያለስራ እንድንቀመጥና ለችግር እንድንዳረግ አድርጎናል ብለዋል።
“ ተርበን ከሰውነት ተራ ወጥተን ከእስር ቤት ብንወጣም አሁንም በችግር እየተጎሳቆልን” ነው የሚሉት አቶ አሸናፊ፣ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች በችግር ተጠብሰው ጎዳና ላይ እየሄዱ ነው ብለዋል።

በቴፒ ከተማ የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ 4 ሰዎች ተገደሉ

በደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን በቴፒ ከተማ የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ 2 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
ብሄር ተኮር ባሆነው በዚሁ ጥቃት የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ መሆናቸው ታውቋል።
ነዋሪው ራሱን ለመከላከል እርምጃ መውሰድ መጀመሩንም ለኣኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
መኖሪያና ንግድ ቤቶች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከፍተኛ ውድመት መድረሱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የደኢህዴን ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በከተማዋ ተገኝተው ሁኔታውን ለማረጋጋት ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱም ታውቋል። በዘር አትከፋፍሉን በሚል የከተማው ነዋሪ ተቃውሞን እያሰማም ነው ተብሏል።
በሸካ ዞን ዘርን ያተኮረ ጥቃት ሲከሰት የሰሞኑ የመጀመሪያው አይደለም።
በየዓመቱ ወቅት እየጠበቀ የሚከሰት ለበርካቶች ህይወት መጥፋት ምክንይስት ሰበብ የሆነ ችግር ነው።
የዘንድሮው ግን የከፋ ነው ይላሉ ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች። ባልፉት ጥቂት ሳምንታት ያዝ ለቀቅ ሲያደርገው የሰነበተው ጥቃት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ ወደለየለት ብሄር ተኮር ጥቃት ተለውጦ በቴፒና በዙሪያዋ የሚገኙ መንደሮች ላይ ከፍተኛ አደጋ ማንዣበቡን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ከትላንት በስቲያ በቤት ግንባታ ስራ በተሰማሩ ወጣቶች ላይ ጥቃት በመፈጸም የተጀመረው አለመረጋጋት ወደለየለት ቀውስ እንዳይሸጋገር ስጋታቸውን የሚገልጹ ነዋሪዎች የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል።
በዛሬው ዕለት በተፈጸመ ጥቃት 2 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ዘግይተው በወጡ ዜናዎች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር አራት መድረሱ ታውቋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደሚገልጹት በዘር ላይ ያተኮረው አስተዳደር ህዝቡ እንዲገፋ አድርጎታል።
በሸካ ዞን ውስጥ ተወልዶ ያደገ የሌላ ብሄር ተወላጅ የትምህርትም ሆነ የስራ እድል እንዲነፈግ ይደረጋል።
ወጣቱ በተወለደበትና ባደገበት አከባቢ ስራ ባለማግኘቱ ወደሌሎች የሀገሪ ክፍሎች መሰደድ እጣ ፈንታው ሆኗል ይላሉ።
መብታችንን ብንጠይቅ የሚደርስብን ቅጣት እስከሞት የሚደርስ ነው የሚሉት ነዋሪዎች አከባቢውን ለቀን እንድንወጣ የሚደረገው ጫና በዞኑ አመራሮች አማካኝነት የሚፈጸም ነው ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል።
ባለፈው ሳምንት ወደ ቴፒ የመጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የከተማዋን ነዋሪዎች ቢያነጋግሩም መፍትሄ ሊሰጡት አልቻሉም ይላሉ ኢሳት ያነጋገራቸው።
የእሳቸውን መመለስ ተከትሎ በአከባቢው መጠነ ሰፊ ጥቃት መከፈቱን የሚገልጹት ነዋሪዎች ዛሬ ከተገደሉት በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሰዎችም በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው ማለፉን ጠቅሰዋል።
በጥቃቱ የልዩ ሃይልና የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎችም መሳተፋቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጥቃቱን ተከትሎ በቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙት የአከባቢው ነዋሪዎች መንግስት በፋጣኝ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል።
ጥቃት ፈጻሚዎች በቴፒ ከተማ በዘረፋ ተግባር ተሰማርተው ሱቆችንናና መደብሮችን ሰብረው እቃ በመጫን እየወሰዱ መሆኑም ተገልጿል።

በአርበኞች ግንቦት 7 ስም በሽብርተኝነት የተከሰሱ እና በእስር ላይ የሚገኙ አርበኛ ታጋዮች ዛሬ ከእስር መፈታታቸው ተሰማ

በአርበኞች ግንቦት 7 ስም በሽብርተኝነት የተከሰሱ እና በእስር ላይ የሚገኙ አርበኛ ታጋዮች ዛሬ ከእስር መፈታታቸው ተሰማ !!
ከዚህ ቀደምም የተፈቱም ሆነ በቀጣይ የሚፈቱትን በተለያየ መልኩ የማህበራዊ አኮኖሚያዊ ጉዳት የደረሰባቸውን ዳግም በዘላቂነት ለማቋቋም አንድ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ስራ መገባቱን የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አሳውቀዋል ።
Image may contain: 11 people, people smiling

"ሄጎ በየኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ባንዲራ ተመልሶ ሁከት እየፈጠረ ነው" (የጅግጅጋ ወቅታዊ ሁኔታ)

"ሄጎ በኦብነግ ባንዲራ ተመልሶ ሁከት እየፈጠረ ነው"
(የጅግጅጋ ወቅታዊ ሁኔታ)
በትናንትናው እለት በጅግጅጋ ከተማ የመንግስት መኪኖችን ጭምር በመጠቀም አብዲ ኢሌ ያደራጃቸው ሄጎ የተባሉ ቡድኖች የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባርን (ኦብነግ/ONLF) ባንዲራ በመያዝ ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክረዋል። ሰሞኑን ክልሉን በማረጋጋት ላይ ከነበረው የመከላከያ ሰራዊት ጋር በፈጠሩት ግጭት ምክንያት መከላከያ ሰራዊት በመሳሪያ ሀይል ለመበተን የተገደደ ሲሆን በተከፈተው ተኩስም የፖሊስ መኪና ላይ የኦብነግ ባንዲራ ሰቅሎ ሲያሽከረክር የነበረ የሂጎ አባል ቆስሏል።
በሌላ በኩል ህዝቡ ከነዚሁ ሂጎ ከተባሉ ቡድኖች ጋር በድንጋይ እየተወራወረ የነበረ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት ወደቦታው ደርሶ ግጭቱን ቢያበርድም ሂጎዎቹ ግን በመኪና እየተጫኑ መከላከያ ወደማይቆጣጠረቻው አካባቢዎች አምልጠዋል።
በክልሉ በተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ጄነራል ሀሰን እንደገለፁት ከሆነ ኦብነግ ራሱን ሂጎ ከሚባሉት በመነጠል እና ስርዓት አልበኝነታቸውን በማውገዝ የለውጡን ሂደት እንዲያግዝ ጠይቀዋል።
በአሁኑ ወቅት ወደ አምስት የሚደርሱ የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች የሚመሩ (Somali Printing, Delta Printing, Jigjiga Jet, Fiqi Printing, Nation Voice, Gadhle Printing) ማተሚያ ቤቶች በሂጎ መሪ በሆነው በልዩ ፖሊስ አዛዥ አብዱራህማን ወንድም አብዱላሂ ትዕዛዝ የሶማሌ ሪፐብሊክ ባንዲራ በብዛት እየታተመ ሲሆን ኦብነግን ለመቀበል ነው በሚል እየተዘጋጀ ባለ ሰልፍ ላይ የሚያዙ ባነሮችም እየተዘጋጁ ነው። ባነሮቹ የሶማሌን መገንጠል የሚያወሱ፣ ነዳጁ የሶማሌ መሆኑን፣ ኢትዮጵያ ወራናለች እና የመሳሰሉትን መፈክሮች ታትመውባቸዋል።
በተለይም የአብዲ ኢሌ ዘመድ እና የጎሳው አባል የሆነው የኦብነጉ ቃል አቀባይ አዳኒ ሂርሙግ ከትናንት በስተያ ወደ ሀገር ቤት ከመግባቱ በፊት ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ "የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሶማሌን ህዝብ ወሮታል ህዝቡ ወጥቶ ይቃወማቸው" ማለቱን ተከትሎ የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች ኦብነግን ከአብዲ ኢሌ ቅፅል ስም (CMC) ጋር በየባነሮቹ እና መኪናዎች ላይ በመፃፍ ቅስቀሳ እያደረጉ እና ባቃጠሏቸው ቤተ ክርስቲያኖች ሱቆች እና በዘረፏቸው መኪኖች ላይ ONLF እና CMC እያሉ ሲፅፉ እንደነበር ይታወሳል - ይሄው ቅስቀሳ አሁንም ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የኮማንድ ፖስቱ ሀላፊዎች ኦብነግ ይህን ስርዓት አልበኝነት ያውግዝ ከማለት ባለፈም - "እንዲህ ያለውን ሁኔታ አንታገሰውም" በማለት አስጠንቅቀዋል። ከህዝቡ ጋር በነበረው ውይይትም በዚሁ የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች እየተሰራጨ ያለውን ፕሮፖጋንዳ በጋራ አውግዘው - ሰላማችን እና የለውጥ ተስፋችን እንዳይቀለበስ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ቆመው እንደሚታገሉ አረጋግጠዋል።
የሀገር ሽማግሌዎች እና የክልሉ ምሁራንም በግጭቱ የተጎዱትን መልሶ ለማቋቋም እየሰሩ ሲሆን - የተቃጠሉ ቤተ ክርስቲያኖችም ተመልሰው እንዲሰሩ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን የክልሉ ምሁራን አስተባባሪዎች ገልፀውልኛል።

Tuesday, August 14, 2018

በአዳማ ከተማ በተፈናቃዮችና በአካባቢው ማኅበረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት የተወሰኑ መጠለያ ቤቶች ተቃጠሉ።


በአዳማ ከተማ በተፈናቃዮችና በአካባቢው ማኅበረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት የተወሰኑ መጠለያ ቤቶች ተቃጠሉ።
ተፈናቃዮቹ ህገወጥነትን እያስፋፉ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ይከሳሉ። ተፈናቃዮች በበኩላቸው መንግስት የገባልንን ቃል ያክብር፤ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለን ብለዋል።
ከሶማሌ ክልል በአብዲ ኢሌ ልዩ ተዕዛዝ ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው በግዳጅ ተፈናቅለው በአዳማ ከተማ በመንግስት በተሰራላቸው መጠለያ ቤቶች ውስጥ ነዋሪ በሆኑት ተፈናቃዮችና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ። በግጭቱም የተፈናቃዮቹ የተወሰኑ መጠለያ ቤቶች በእሳት መቃጠላቸው ታውቋል። ለግጭቱ መቀስቀስ ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ ጊዜያት የሚፈጽሙት ህገወጥ ዝርፊያና ሥርዓት አልበኝነት መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።
በአካባቢው ገንደ ጋራ ልዩ ስሙ ዶሮ እርባታ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ነዋሪዎች እንዲሁም በግብርና ሙያ በሚተዳደሩት የቀጨማና አካባቢው አርሶ አደሮች እህል ወደ ገበያ ይዘው በሚመጡት ወቅት ይዘረፋሉ፤ አካላዊ ጥቃቶችም ይደርስባቸዋል። በከተማዋ መውጫ ላይ በድንጋይ መጥረብ ካባና አሸዋ ሥራ ላይ በህጋዊነት የተሰማሩት ሰራተኞችን ጨምሮ አሽከርካሪዎችን በግዳጅ ክፍያ እንዲፈጽሙ ይጠየቃሉ። ይህን ህገወጥነት በማይቀበሉት ላይም ጥቃት ለማድረስ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው ነዋሪዎቹ በምሬት መናገራቸውን ምንጮቻችን አስታውቀዋል። በተለይም ፍልሰተኞቹ ነዋሪዎች ላይ የሃይማኖታዊ ግጭት የማስነሳት ስጋት መፍጠራቸው ለትናትናው እረብሻ መቀስቀስ ምክንያት ሆኗል።
በከተማዋ ዳርቻ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የሆነውን ቅዱስ መርቆሪዮስ ቤተክርስቲያን ለማቃጠል ሙከራ ማድረጋቸው፤ የሃይማኖት አባቶች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜያት ትንኮሳዎች መፈጸማቸው ምእመናኑንና ነዋሪዎችን አሳዝኗል። ቤተክርስቲያኗ ምእመናኑንና አርሶ አደሮችን በማስተባበር የምግብና የአልባሳት እገዛ በማድረግ ስትታደጋቸው ቆይታለች። ‘’ለዚህ መልካም ውለታችን ይሄን ዓይነት ወንጀል ሊታሰብብን አይገባም ‘’ ብለዋል።
አክለውም ‘’በተደጋጋሚ ለፖሊስና የጸጥታ አካላት ብናመለክትም ወንጀለኞቹ ተይዘው ካለምንም ህጋዊ ቅጣት በነጻ ይለቀቃሉ። ፍትህ ልናገኝ አልቻልንም። ይህን ተከትሎ እራሳችንን ከጥቃት ለመከላከል ተገደናል። መንግስት አፋጣኝ መፍትሔ ይስጠን።’’ ሲሉ የከተማው ነዋሪዎች እና አርሶ አደሮች ብሶታቸውን አሰምተዋል። በዚህም ምክንያት በተፈጠረ ግጭት የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ የተፈናቃዮች የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶች በእሳት መቃጠላቸውንና አሁንም በጸጥታ ሃይሎችና በተፈናቃዮች መሃከል ውጥረት መንገሱን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ተፈናቃዮቹ በበኩላቸው ከቀጨማ ተራራ ሥር ጣራና ግድግዳው ቆርቆሮ በቆርቆሮ በተሰራ መኖሪያ ቤት ውስጥ በጋውን በሃሩር፤ ክረምቱን በቁር እንዲሰቃዩ መደረጋቸውን ይናገራሉ። መንግስት ከዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ግብረሰናይ ድርጅቶችና በስማቸው የሰበሰውን ገንዘብና እርዳታ እንዳልሰጣቸውና ሕይወት ከባድ እየሆነባቸው መምታቱን በተለይም ታዳጊ ሕጻናት፣ በዕድሜ የገፉ አቅመ ደካማ አዛውንቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ ህመምተኞች ለርሃብና እርዛት ተጋላጭ ሆነዋል። ይህ ምሬት ለሥርዓት አልበኛ ወጣቶች ወንጀል መስፋፋት መንስኤ መሆኑንና ሁሉም ተፈናቃዮች የወንጀሉ ተባባሪ አለመሆናቸውን ይናገራሉ።
ተፈናቃዮቹ ‘’መንግስት ቃል የገባልንን በተግባር ይፈጽም። ኃላፊነት በመውሰድ ወደ መኖሪያ ቀያችን ይመልሱን። መንግስት እንደ ዜጋ ቆጥሮን ልጆቻችን መሰረታዊ የሆነውን የምግብ፣ የአልባሳት፣ የመጠለያና የሕክምና አገልግሎት ያቅርብልን። በስማችን የተሰበሰበውን የዘረፉ ሌቦች በሕግ ይጠየቁልን።’’ ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል።
ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት ሰዓት ድረስ የከተማ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ቤተክርስቲያኑን ዙሪያውን ከበው ከጥቃት ለመከላከል በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ተጠየቀ


(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 8/2010)የመብት ተሟጋቹ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ጥሪ ቀረበ ።
ለዚህ ታዋቂ አትሌት የጀግና አቀባበል ለማድረግ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዝግጅት ማድረጋቸውን ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።
በነሃሴ 2008 ዓም በብራዚል ሪዮ ዲጄነሮ በተካሄደው ኦሎምፒክ በማራቶን ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው  አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ  ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል።
በዚሁ ወቅትም ሩጫውን ሲያጠናቅቅ በኢትዮጲያ የሚካሄዱ ግድያዎችን በአጠቃላይ የመብት ጥሰቶችን በመቃወም እጁን በማነባበር በዓለም ሕዝብ ፊት ባሳየው ተቃውሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታን ማግኘቱ ይታወሳል።
በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ ግፍ እና በደሎችን በአጠቃላይ የመብት አፈና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ስም እና ዝናውን ያተረፈው ጀግናው አትሌት ፈይሳ ላለፉት 2 ዓመታት በአሜሪካ በሰደት ላይ ቆይቷል።
አትሌቱ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ዛሬ ጥሪ ያቀረቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሪሽን እና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ  ኮሚቴ ናቸው።
በአሜሪካ አሪዞና ግዛት ከባለቤቱ እና ከልጆቹ ጋር የሚኖረውን ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ርሱም ወደ ሃገሩ የመመለስ ፍላጎት እንዳለው ለቢቢሲ ገልጿል።

ከደብረ ብርሃን 12 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው ጫጫ ከተማ አቅራቢያ በተከሰተ የመኪና አደጋ 16 ሰዎች ሞቱ


ከደብረ ብርሃን 12 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው ጫጫ ከተማ አቅራቢያ በተከሰተ የመኪና አደጋ 16 ሰዎች ሞቱ፡፡
በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን ሰዎች ጭኖ ሲሄድ የነበረ ቅጥቅጥ መኪና፣ ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ ከሚመጣ ሚትስቡሽ ሲኖ ትራክ መኪና ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋው የደረሰው፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ዋና ሳጅን ላቀው ዘነበ ለኢቢሲ እንዳሉት አደጋው ከባድ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ከ16 ሊጨምር ይችላል፡፡
በአደጋው የተጎዱ ተሳፋሪዎች ለህክምና መላካቸውንም አመልክተዋል፡፡
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ዋና ሳጅን ላቀው ተናግረዋል፡፡
Ebc

Monday, August 13, 2018

በሻሸመኔ ከተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በሻሸመኔ ከተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ እንደተናገሩት በተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት እጃቸው ያለበትን አካላት በመያዝ ለፍርድ ለማቅረብ ሂደቱ ተጀምሯል።
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን ቡድንን ለመቀበል በአስርሺዎች የሚቆጠሩ የሻሸመኔና አካባቢዋ ነዋሪዎች አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉም ታውቋል።
ፖሊስ ከተማዋን ለማረጋጋት እየሰራሁ ነው ብሏል። በሻሸመኔ በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸመውን ግድያ በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል።
የሻሸመኔው አሰቃቂ ግድያ ብዙዎችን አስደንግጧል።
አንድን ግለሰብ በድብደባ ህይወቱ ካለፈ በኋላ ቁልቁል ተሰቅሎ የሚታይበት ፎቶግራፍ በማህበራዊ መገናኛ መድረኮች በስፋት ተሰራጭቷል።
ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን በማውገዝ የተቃውሞ መልዕክቶችን በየመድረኩ አሰምተዋል።
ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን ቡድን አባላት አቀባበል የወጣው የሻሸመኔ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪ በተሰሳሳተ መረጃ በተፈጠረ ግርግር አራት ሰዎች ተረጋግጠው መሞታቸንም ለማወቅ ተችሏል።
ቦምብ ይዟል ብሚል ያልተጣራ መረጃ ተደብድቦ የተገደለው ወጣት ከተሰቀለም በኋላ በመኪና ለመጎተት የተደረገው እንቅስቃሴ ብዙዎችን አስቆጥቷል።
ጉዳዩ ከውግዘት ባለፈ ድርጊቱን በፈጸሙ ሰዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ተጠይቋል።
በዛሬው ዕለት ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔት ወርክ መግለጫ የሰጡት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አሰቃቂውን ግድያ የፈጸሙት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።
በሻሸመኔ ከተማ ቦምብ ተገኝቷል በሚል የተፈጠረው ግርግር የሰው ህይወት ማጥፋቱንም በመግለጽ መረጃ ትክክል አልነበረም ብለዋል።
ፖሊስ እስከአሁን ባደረገው ማጣራት ቦምብም ይሁን ከቦምብ ጋር የሚመሳሰል ምንም ዓይነት ነገር እንዳልተገኘ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ ለኦቢኤን ገልጸዋል።
ሻሸመኔ ከገባችበት አለመረጋጋት እየወጣች ሰላም እየሰፈነ ያሉት የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ዓለማየሁ እጅጉ አጠቃላይ የተፈጠረው ሁኔታ በተመለከተ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን መናገራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ ፈጽመው የሰቀሉት አካላት በቁጥጥር ስር መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ ምርመራው እንድተጠናቀቀ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ጠቁመዋል።

wanted officials