Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, May 21, 2017

Deutschlands Luftwaffe and Ethiopian lalibela Emblem







ስዕለ ኪሩብ እና የጀርመኑ Luftwaffe አርማ !
___________________________
የምስጢር ማህበረሰብ በመባል የሚጠሩት የስማዝያ ጭፍሮች በተለያየ ዘመን ወደሃገራችን በመግባት የተለያዩ ቅርሶችን መጽሀፍትን መንፈሳዊ አንድምታ ያላቸውን ጠልሰሞች ከሃገራችን መበዝበዛቸው አሁንም እየበዘበዙ እንዳሉ በተደጋጋሚ ለመግለጽ ሞክሬያለሁ፡፡
ታዲያ ለዚህ ስውር ደባ እንደ ማስረጃ ከማቅረባቸው ጠልሰማት አንዱ ስዕለ ኪሩብ የተሰኘውን ጠልሰም ነው፡፡ የምስጢር ማህበረሰቡ አንድ እጅ የሆነው የጀርመኑ የናዚን ቡድን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ አካላት ሰዋስቲካ ብለው የሰየሙትን ምልክት ለጦር ሃይላቸው አርማ ሲጠቀሙ በመመልከታችን የኛ እንዳልሆነ ለዘመናት ተቀብለን አምነናል እንዲሁም ተምረናል፡፡ እውነቱ ግን ይህ አይደለም የምስጢር ማህበረሰቡ መንፈሳዊ ጥበቦች እና ምስጢራቶችን ተቀራምቶ ዓለምን ለመግዛት ለዘረፋ ከተሰማራባቸው ሀገራት ቀደሚ ስፍራ የምትይዘው ኢትዮጵያ ስትሆን ከተወሰዱብን ጠልሰሞች መካከልም በነርሱ አጠራር ሰዋስቲካ የተሰኘው ጠልሰማችን ነው፡፡
ይህ ጠልሰም የስድስት ሺህ ዓመት ታሪክ ባላት በጥንቷ ኢትዮጵያና በጥንታዊ መጽሀፍቶቻችን ስዕለ ኪሩብ ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ኢዮር በተሰኘችው የእሳት ዓለም ውስጥ የሚገኙ የመላእክት ነገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ የመላእክት ነገዶች የካህናት ተምሳሌት(ጠልሰም) ሲሆኑ ከወገባቸው በታች አንድ ከወገባቸው በላይ አራት ተደርገው እንደተፈጠሩ የስነፍጥረት መጽሀፍት ያስረዳሉ፡፡ እነዚህ መላእክት አራት ገጽ አላቸው ገጸ አንበሳ ገጸ ሰብእ ገጸ ንስር እና ገጸ ላም ናቸው፡፡ ከእግራቸው ጀምሮ እስከራሳቸው ድረስም እንዲሁ በዓይን የተሸፈኑ ናቸው፡፡
የሱራፌል የመላእክት ነገድ የካህናት ተምሳሌት ናቸው ካህናት ደግሞ የነገስታት ተምሳሌት ሲሆኑ በላሊበላ አብያተ ክርስትያናት ላይ የምንመለከተው ጠልሰም ደግሞ የነገስታት እና የሃይል ተምሳሌት ነው ስያሜውም ስዕለ ኪሩብ ነው፡፡ ከዚህ አንድምታ በመነሳት ጀርመኖች ይህን ጠልሰም ከኛ በመውሰድ ሃያል እና ገዢ ነን ሲሉ ይህን ምልክት ለመንግስታቸው እና ለመከላከያ ሰራዊታቸው ምልክት አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡


የኪሩቤል ነገደ መላእክት ለአገልግሎት የሚዘዋወሩበት እሳታዊ የሆነ ሠረገላ አላቸው፡፡ ይህ እሳታዊ ሠረገላ በታላቅ ሃይል የኪሩብ ነገደ መላእክትን ተሸክሞ ወደሚሄዱበት የሚያደረስቻው መንኮራኩር እና የሃይላቸው ማረፊያ ነው፡፡ ቅዱሳን መጽሃፍት እንደሚያስተምሩን ነገደ ኪሩብ መላእክት ስድስት ክንፍ አላቸው በሁለት ክንፋቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፋቸው እግራቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፋቸውም እንዲሁ ይበራሉ፡፡ በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ለአገልግሎት በአራቱ ማእዘን የእሳት ሰረገላን ይዘው ይበራሉ፡፡ በላሊበላ አብያተ ክርስትያናት በቤተማርያም መስኮት ላይ የምንመለከተው ስእለ ኪሩብ የተሰኘው ጠልሰም የነገደ ኪሩብ ሰረገላ እና የሃይላቸው ማረፊያ የሆነ መንኮራኩር ተምሳሌት ነው፡፡ይህ ምልክት የነገደ ኪሩብ የሃይላቸው ማረፊያ በመሆኑ በሃይል ሲመሰል እንዲሁም የነገደ መላእክቱ እሳታዊ መንኮራኩር ተምሳሌት ነው፡፡ የጀርመኑ የናዚ ቡድን ይህን ጠልሰም ከኛ ወስዶ ለአየር ሃይል የውጊያ ቡድናቸውI(Luftwaffe) አርማ ሲያደርጉትም ከላይ የገለጽኩትን የኪሩብ ሰረገላን መሰረት አድርገው ነው፡፡ ቢሆንም ግን እኛ መረዳት ያለብን የጀርመኑ የናዚ ቡድን ከኛ የወሰደውን ይህን ጠልሰም(ተምሳሌታዊ ምልክት) ላልተገባ አላማ መጠቀሙን ነው ስለዚህ የኛ ሃላፊነት ከኛ ተወስደው ላልተገባ አላማ የዋሉትን ንብረቶች እና ጥበባቶች ከማስመለስ ባለፈ ትውልድ እውነተኛውን የጥበባቱን መንፈሳዊ አንድምታ እንዲረዳ ማስቻል ነው፡፡
#ከኛ ወስደው የኛ ነው ስላሉን ብቻ አዎን የኛ አይደለም ብለን የአባቶቻችንን ቅርሶች ገሸሽ ማድረግ የለብንም ክፉውን ከበጎ እየለየን ማንነታችን የሚያሳዩ ቅርሶችን እና መረጃዎችን ለቀጣዩ ትውልድ እናሳልፍ፡፡
#ጥንታዊነት_የዘመኑ_ፋሽን_ነው #ራፋቶኤል

Website: http://www.rafatoel.net/
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCEoeD5UdIu-x4jSv3KzzGMg
Facebook: https://www.facebook.com/Rafatoel/?hc_ref=SEARCH

No comments:

Post a Comment

wanted officials