Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, September 25, 2018

ሰበር_ዜና: የሰኔ 16ቱ ጥቃት ጠ/ሚ አብይን ለመግደልና #ኦነግ ሀገሪቱን እንዲመራ ለማስቻል እንደሆነ የአቃቤ ህግ ገለፀ


በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት ክሱን ያቀረበው ዓቃቤ ሕግ የሰኔ 16ቱ የቦምብ ጥቃት የተፈጸመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን ለመግደል መሆኑን በክሱ አስታውቋል፡፡ በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩት አምስት ግለሰቦችም የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ክስ እንደገለጸው፣ ተከሳሾቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ላይ ግድያ ለመፈጸም ያነሳሳቸው በእሳቸው የሚመራ መንግሥት መኖር ስለሌለበት ነው፡፡ የአገሪቱ መንግሥት መመራት ያለበት ቀድሞ በተመሠረተው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው የሚል ዓላማ ተከሳሾቹ እንዳላቸው ዓቃቤ ሕግ በመሠረተው ክስ ጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም በማለትም፣ ተጠርጣሪዎቹ ለግድያ መነሳሳታቸውን ዓቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ ኮንግረስ የፀደቀውን ኤችአር 128 ለማስፈጸምና በስመ ሕዝበኝነት የራሳቸውን ዓላማ የሚያራምዱ መሆናቸውን፣ በዚህም ምክንያት የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት ስለማያስፈጽሙ ተጠርጣሪዎቹ ጥቃቱን ለመፈጸም መነሳሳታቸቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አክሏል፡፡
የሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል አደባባይ የወንጀል ድርጊት ያቀነባበረችው በኬንያ ናይሮቢ የምትገኝ ገነት ታምሩ (ቶለሺ ታምሩ) የምትባል መሆኗን፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ አመልክቷል፡፡
Via #EthioNewsflash & Reporter Newspaper
No automatic alt text available.

No comments:

Post a Comment

wanted officials