Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, September 22, 2018

ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ወገኖቻቸው ድጋፍ ለማግኘት የተንቀሳቀሱ 35 ወጣቶች ታሰሩ


ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ወገኖቻቸው ድጋፍ ለማግኘት የተንቀሳቀሱ 35 ወጣቶች ታሰሩ
 35 የጨርቆስና እና አካባቢው ወጣቶች ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውንና ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በሰንዳፋ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ተናግራል።
ወጣቶቹ ከአካባቢያቸው በሰበሰቡት ገንዘብ የገዟቸውን ምግብ እና ቁሳቁሶች አስረክበው ሲመለሱ ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ፖሊስ ምግብ እና ቁሳቁስ ጭነውበት ከነበሩት 3 መኪኖች ጋር በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስን አስተያየት ለማግኘት ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢደረግም አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials