Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, September 30, 2018

ትክክለኛው የቅድስት አርሴማ ስዕል እና ቅድስት አርሴማ ተብለው የሚሰራጩ የሌሎች ቅዱሳን አንስት ሥዕላት!

ትክክለኛው የቅድስት አርሴማ ስዕል እና ቅድስት አርሴማ ተብለው የሚሰራጩ የሌሎች ቅዱሳን አንስት ሥዕላት!
በሀገራችን በሀበሾች በስፋት የቅድስት አርሴማ እየተባለ የሚሰራጨው ሥዕል የቅድስት ሉሲያና የቅድስት ባርባራ ናቸው፡፡
አንዳንዶች «አንዴ በልቦናችን ተስሏል» ብለው በዛው መቀጠልን የሚመርጡ ሰዎች አሉ:: በእርግጥ የሚያስረዳ ሰው ጠፍቶ ባለመረዳት ቢሆን ኩነኔ አይሆንም ብዬ አስባለሁ፡፡ ከተረዳን በኋላ ግን የቅድስት ሉሲያን ቅድስት ሉሲያ፤ የቅድስት አርሴማን ደግሞ ቅድስት አርሴማ ብለን ቢቻል ስለሁሉም ቅዱሳን ተምረን ከሁሉም በረከት መቀበል ይሻላል ወይስ ተረድተንም እንዳልተረዳ ሰው የቅድስት ሉሲያንና የሌሎችን ስዕላት ሁሉም ቅድስት አርሴማ እንደሆኑ አድርጎ መቀጠል?
"ጌታችን በወንጌሉ እውነትን እውነት፤ ሐሰትን ሐሰት ብለን እንድንናገር ያስተምረናል፡፡ በመሆኑም እውነተኛውን የቅድስት አርሴማን ወካይ የሆነውን ሥዕሏን እንድንጠቀም ለማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡ ከዚያም ሲቀጥል በሥዕሉ ላይ የተወከሉት ሌሎች ስለክርስቶስ ሲሉ ሰማእትነት የተቀበሉትን ቅዱሳንን እንድናከብር ያስፈልጋል፡፡"
ትክክለኛው የቅድስት አርሴማ ስዕል ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እዚህ አስረድቷል፤ ከፍታችሁ ማየት ትችላላችሁ፦ http://www.danielkibret.com/2014/10/blog-post_8.html?m=1q


No comments:

Post a Comment

wanted officials