Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 31, 2019

ከሁለት ወር በፊት ሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ሰው 'ዳግም' ሞቱ



አቶ ሂርጳ ነገሮImage copyrightSIBU SIRE COMMUNICATION
አጭር የምስል መግለጫአቶ ሂርጳ ነገሮ
ከሁለት ወራት በፊት የሞትን ብርቱ ክንድ አሸንፈው ተነሱ የተባሉት አቶ ሂርጳ ነገሮ ሞተው ሳሉ የገጠማቸውን ለቢቢሲ አጫውተው የነበረ ሲሆን ከ70 ቀናት በኋላ ትናንት 'ዳግም' ማረፋቸውን ከሁለት ጊዜ ገናዣቸው ሰምተናል።
መቃብር ፈንቅለው ከወጡ በኋላ ጤናማ የነበሩት አቶ ሂርጳ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ግን በፅኑ ታመው ከፈሳሽ ውጭ ምንም ነገር ይወስዱ እንዳልነበር ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችለናል። እሳቸው አይሆንም ቢሉም ቤተሰቦቻቸው ነቀምት ሆስፒታል ወስደዋቸው ነበር።
ቤተሰቦቻቸው አቶ ሂርጳ ዳግም መቃርብር ፈንቅለው ይነሳሉ የሚል ተስፋ እንደሌላቸው ገልፀዋል። አቶ ሂርጳና ገናዣቸው አቶ ኢታና ቀንአን አነጋግረን የሰራነው ዘገባ የሚከተለው ነበር።
ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለየች የሚባለው መቼ ነው? ምን ሲሆን?
አቶ ሂርጳ ነገሮ ለዚህ ፍንጭ ሊሰጡን የሚችሉ ሁነኛ ሰው ናቸው፤ የቅርብ ጊዜ ምሥክር። ትውልዳቸው ከወደ ምሥራቅ ወለጋ ሲቡ ስሬ ወረዳ ነው።
ዘለግ ላለ ጊዜ በጽኑ ታመው ቆይተዋል። ከ2 ዓመት በፊት ሆድ ዕቃቸው ተከፍቶ በቀዶ ጥገና ታክመዋል። የጤና ታሪካቸው በአጭሩ ይኸው ነው።
ማክሰኞ ረፋድ ላይ ግን ድንገት ደካከሙ። በዚያው ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ሞቱ [ተባለ]። ጥሩምባ ተነፋ፣ ጥይት ተተኮሰ፣ ድንኳን ተጣለ፤ ለቀስተኛ ተሰበሰበ፤ ሬሳ ተገነዘ።
ከአራት ተኩል ሰዓታት በኋላ ግን አቶ ሄርጳ[ሳጥን ፈንቅለው ወጡ]፤ 'ኢጆሌ ኢጆሌ እያሉ....'። ይህ የኾነው ማክሰኞ 'ለታ ተሲያት ላይ ነው። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከእርሳቸው ጋር የስልክ ቆይታ አድርጓል። በ'ሞቱበት' ሰዓት ያለ ቀጠሮ ያገኙት 'መልአክ' ምን ሹክ እንዳላቸው ጭምር አብራርተዋል።
ኾኖም መቅደም ያለበትን እናስቀድም። አቶ ኢታናን፤ ገናዣቸውን።
ቢቢሲ፦ ሳይሞቱ እንዳይሆን አጣድፋችሁ ሳጥን ውስጥ የከተታችኋቸው።
አቶ ኢተና፦ "ዛሬ አይደለም እኮ ሰው የገነዝኩት [ቆጣ አሉ]። ስንትና ስንት ሰው ገንዣለሁ። ትና ስንት..."
ቢቢሲ፦ እና ሳጥን ውስጥ ሲከቷቸው ትንፋሽ አልነበራቸውም? እርግጠኛ ኖት?
አቶ ኢታና፦ "[ምን ነካህ!] ስንትና ስንት ሰው ሲሞት ይቻለሁ። ስንትና ስንት አው ገንዣለሁ። መሞቱን አረጋግጬ ነው ሳጥኑ ውስጥ ያስገባሁት። ዝም ብዬ እከታለሁ እንዴ [የምር እየተቆጡ መጡ]
ቢቢሲ፦ ታዲያ እንዴት የሞቱ ሰውዬ ሊነሱ ቻሉ?
አቶ ኢተና፦ እንጃ! እንዲህ ዓይነት ነገር ሆኖ አያውቅም። ይሄ ከእግዛቤር የሆነ ነው እንጂ...

እሑድ ሊናዘዙ ቀጠሮ ነበራቸው

"ሞቼ ተነሳሁ" የሚሉት አቶ ሂርጳ በሽታቸውን በውል አያውቁትም። ኾኖም እምብርታቸው አካባቢ ለረዥም ጊዜ ይቆርጣቸው ነበር። ነገርየው የጉበት ሕመም ሳይሆን እንዳልቀረ ይጠረጥራሉ። ሐኪምም ዐይቷቸዋል። የፈየደላቸው ነገር ባይኖርም።
መጀመርያ ነቀምት ሆስፒታል፣ ከዚያ ደግሞ ጥቁር አንበሳ 'ሪፈር' ተብለው ሄደዋል። ደንበኛ ምርመራ አድርጊያለሁ ነው የሚሉት። ኾኖም የምርመራ ውጤቱ አልተነገራቸውም። በታኀሣስ 1፣ ሊነገራቸው ቀጠሮ ተይዞ ነው በዚያው 'ያሸለቡት'።
በዚያ ላይ ለመዳን ከነበረ ጽኑ ፍላጎት የተነሳ በሬ ሽጠዋል። ዘመድ አዝማድ ተቸጋግሯል። ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄዶ ለመታከም።
ከሰሞኑ ጉልበት ሲከዳቸው ታዲያ እንደማይተርፉ ጠረጠሩ። ያለቻቸውን ጥሪት ለአምስት ልጆቻቸው ሊናዘዙ ፈለጉ። ሰኞ ሊሞቱ እሑድ ዕለት ለመናዘዝ ቀጠሮ ተይዞ ነበር። ያጋጣሚ ነገር ኾኖ በዕለቱ የበኩር ልጃቸው ስላልነበረ ኑዛዜው ላልተወሰነ ጊዜ ተላለፈ። ማክሰኞ 'ለት 'ሞቱ'።
"ሬሳ ሳጥን የሰጠሁት እኔ ነኝ"
ገናዥ አቶ ኢታና ቤተሰብም ናቸው፤ ጎረቤትም ናቸው። 'ሟች' የወንድማቸው ልጅ ናቸው። 3ሺህ የሚያወጣ ሬሳ ሳጥን በታላቅ ቸርነት ያበረከቱትም የገነዙትም እርሳቸው ናቸው።
"ጋዜጠኞች ትናንት መጥተው ዐይተዋል። የወንድሜ ልጅ ስለሆነ የራሴን ሳጥን ሰጠሁት" ይላሉ።
ቤተሰቡን ከወጪ ለመታደግ ነው ታዲያ ይህን ያደረጉት። ሳጥኑ ውስጥ ልብስ ምናምን ነበር የሚቀመጥበት። ምናምኑን ሁሉ ወለል ላይ ጣጥለው፣ አራግፈው፣ የወንድማቸውን 'ሬሳ' በክብር አኖሩበት።
"ነጭ ልብስ የለበሰ መልአክ 'ተመለስ' አለኝ"
እጅግ በተረጋጋ ሁኔታ የሚያወጉት አቶ ሄርጶ በሰማይ ቤት ቆይታቸው የተመለከቱትን ለቢቢሲ አጋርተዋል።
እርግጥ ነው አንዳንድ ነገሮች ተዘንግተዋቸዋል። አንዳንዶቹ ትውስ ይሏቸዋል፣ ኾኖም በጠራ መልኩ አይደለም። አንዳንዶቹን ነገሮች ግን አጥርተው ማስታወስ ይችላሉ። ልክ ዛሬ የኾነ ያህል።
ለምሳሌ በሰማይ ቤት በብረት ሰንሰለት የሚታጠር ግቢ ብዙ ሺ ሰዎች ተሰብስበው ተመልክተዋል። አጥሩ ከምን እንደተሠራ ግን አያስታውሱም፤ በሩ የብረት ይሁን የሳንቃ ትዝ አይላቸውም። አካባቢው ደጋና ልምላሜ የወረሰው እንደነበር ያስታውሳሉ። ኾኖም የሰማይ ቤቱ መልከዐምድር አይከሰትላቸውም።
ከሁሉ ከሁሉ ያልዘነጉት ግን ከባድ ንፋስ ይነፍስ እንደነበረ ነው። ክብደቱን ሲገልጹ ድምጻቸውን ሁሉ ይበርደዋል።
ሰዎች ተሰብስበውበታል ከሚሉት ከዚያ ግቢ ታዲያ ማንንም አያውቁም። ከሦስት ሰዎች በቀር። እነርሱም ከ2 ዓመት በፊት የሞቱትን አባታቸው፤ ከዓመታት በፊት የሞቱትን አማቻቸውን እና አንድ ሌላ አጎት ናቸው።
ከሦስቱ ጋር ምን እንዳወጉ በውል አያስታውሱም። የሚያስታውሱት "እኛን ተከተለን" ብለዋቸው ቢከተሉ፣ ቢከተሉ፣ በፍጥነት ቢራመዱ፣ ቢሮጡ ሊደርሱባቸው እንዳልቻሉ ነው። ነገሩ የሕልም ሩጫን ይመስላል።
ቀዩን መልአክ ግን መቼም አይረሱትም። በሁለተኛው ምዕራፍ የሕይወት ዘመናቸውም የሚረሱት አይመስልም።
ቢቢሲ፦ መልአኩ ቀይ ነው ጥቁር?
አቶ ሂርጶ፦ ነጭ ነው፤ ቀይ ነው...ጌታን ኢየሱስንም ይመስላል
ቢቢሲ፦የሰው መልክ ነው ያለው ወይስ የመልአክ?
አቶ ሄርጶ፦ፊቱ በደንብ አላየሁትም። ወደ አጥሩ ቆሞ እኔ ውጭ ነበርኩ። መልኩ ቀይ ነው ነጭ ልብስ ይለብሳል። ሰዎቹን ወደ ውስጥ አስገባና ይዟቸው ሄደ
ቢቢሲ፦ሌላ መልአክ አልነረም አጠገቡ?
አቶ ሄርጶ፦ አላስታውስም፤ እሱን ብቻ ነው ያየሁት
ቢቢሲ፦ምን አሎት?
አቶ ሄርጶ፦ 'አንተ የት ትሄዳለህ? ተመለስ!' አለኝ።
ቢቢሲ፦በምን ቋንቋ ነው ያናገርዎት?
አቶ ሄርጶ፦ በኦሮኛ።
ቢቢሲ፦ አልፈሩም?
አቶ ሄርጶ፦ አቅም አጣሁ እንጂ አጥሩን ኬላውን አልፌ ብገባ ደስ ባለኝ ነበር።
"ኢጆሌ ኢጆሌ..."
ማክሰኞ ተሲያት ላይ ከሬሳ ሳጥኑ ውስጥ ድምጽ ሲሰማ የአጋጣሚ ነገር በቅርብ የነበሩት የ'ሟች' እናትና ባለቤቱ ነበሩ። "ኢጆሌ ኢጆሌ..." ይላል ድምጹ። ሚስትና እናት ራሳቸውን አልሳቱም፤ በርግገው ከአካባቢው ተሰወሩ እንጂ። ድምጹ አልቆመም። "ኢጆሌ ኢጆሌ ነምኒ ሂንጂሩ?..."
ለቀስተኛው ግማሹ እግሬ አውጪኝ አለ። ግማሹ የሚይዘው የሚጨብጠውን አጣ። የሰሙት ሬሳው እየጮኸ እንደሆነ ተናገሩ። ለመጠጋት የደፈረ አልነበረም። ከገናዣቸው በስተቀር። "ወንዶቹ ሁሉ ጥለው ጠፉ" ይላሉ አቶ ኢታና።
ቢቢሲ፦ እርስዎ ግን አልፈሩም?
አቶ ኢታና፦ ለምን እፈራለሁ፤ ሬሳውን ማስቀመጤን አውቃለ...

"ከዚህ በኋላ የምኖረው ትርፍ ሕይወት ነው"

ያን 'ለታ ፀሐይ ስታዘቀዝቅ ሚሪንዳ ቀመሱና ነፍሳቸው መለስ አለች። ሲረጋጉ ዘመድ አዝማድ መሰብሰቡን አስተዋሉ። እልልታና ለቅሶም ሰሙ። "ምንድነው ይሄ?"። 'ሞተው ነበረኮ' ተባሉ።
"እንኳን በሰላም ገባህ፤ እንኳን በሰላም ተመለስክ ብለው ተደሰቱ" ይላሉ የወቅቱን የለቀስተኛውን መደነቅና ደስታ ለቢቢሲ ሲያስረዱ።
"ተጸጸቱ እንዴ ግን? ወደ ሕይወት በመመለስዎ?" ብለናቸው ነበር።
"እዛ ብሆን ጥሩ ነበር...። ግን አሁን ቅር የሚለኝ ነገር የለም። ወደ ልጆቼ፣ ወደ ቤተሰቤ በመመለሴ በጣም ደስ አለኝ።"
ከዚህ በኋላ ምን ለማድረግ እንዳሰቡ ሲጠየቁ ጊዜያቸውን የሃይማኖት ትምህርት በመስጠትና የተጣሉ ሰዎችን በማስታረቅ ለማሳለፍ እንዳሰቡ ተናግረዋል።
ለቀስተኞችImage copyrightSIBU SIRE COMMUNICATION
አጭር የምስል መግለጫለቀስተኞች
ወለጋ ሲቡ ስሬ ወረዳ እነ አቶ ሄርጳ ቤት ዛሬም ለለቅሶው ሲባል የተተከለው ድንኳን ባለበት አለ። "ሰዎች በብዛት እየመጡ ነው። እንደለቅሶ ነው የሚመጡት" አሉ ገናዡ አቶ ኢታና።

ጥቁር አንበሳ ቀጠሮ አላቸው

"ከመሞቴ በፊት ከነሐሴ ጀምሬ እንጀራ በልቼ አላውቅም" የሚሉት አቶ ሄርጳ "አፌም እንደዚህ መናገር አይችልም ነበር" ይላሉ።
ከሬሳ ሳጥን ከወጡ በኋላ ግን ሕመማቸው ሙሉ በሙሉ ድኖ በሶም እንጀራም መቀማመስ ጀምረዋል። ድምጻቸው ደከምከም ይበል እንጂ ዘለግ ላለ ሰዓት እንደልብ ያወራሉ።
የተዘነጋው ጉዳይ! ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቀጠሮ አላቸው። ለታኅሣሥ አንድ። ለውጤት ነው የተቀጠሩት።
ከዚህ በኋላ ሐኪም ዘንድ ይሄዳሉ? ተብለው ሲጠየቁ ታዲያ መልሳቸው አጭርና ፈጣን ነው። "ለምን ብዬ!"

Tuesday, December 24, 2019

Why Japan celebrates Christmas with KFC


This is a news in December 2016

How a fast-food marketing campaign turned into a widespread Yuletide tradition for millions.


Every Christmas, Ryohei Ando gathers his family together for a holiday tradition. Just like their father did as a child, his two children will reach deep into a red-and-white bucket and pick out the best piece of fried chicken they can find.



Every Christmas season, an estimated 3.6 million Japanese families treat themselves to Kentucky Fried Chicken, in what has become a nationwide tradition



Yes, it’s a Merry KFC Christmas for the Ando family. It may seem odd anywhere outside Japan, but Ando’s family and millions of others would never let a Christmas go by without Kentucky Fried Chicken. Every Christmas season an estimated 3.6 million Japanese families treat themselves to fried chicken from the American fast-food chain, in what has become a nationwide tradition.

“My kids, they think it’s natural,” says Ando, a 40-year-old in the marketing department of a Tokyo sporting goods company.


Demand is so high for KFC at Christmastime that people can queue outside for meals (Credit: KFC Japan)



While millions do celebrate Christmas with KFC, others in Japan treat it as a romantic holiday similar to Valentine’s Day, and couples mark the occasion with dinner in upscale restaurants. For other Japanese families, Christmas is acknowledged but not celebrated in any particular way.

But for those who do partake, it’s not as simple as walking in and ordering. December is a busy month for KFC in Japan – daily sales at some restaurants during the Christmas period can be 10 times their usual take. Getting the KFC special Christmas dinner often requires ordering it weeks in advance, and those who didn’t will wait in line, sometimes for hours.

The genesis of Japan’s KFC tradition is a tale of corporate promotion that any business heading to Japan ought to study, one that sounds almost like a holiday parable.

‘Kentucky for Christmas’

According to KFC Japan spokeswoman Motoichi Nakatani, it started thanks to Takeshi Okawara, the manager of the first KFC in the country. Shortly after it opened in 1970, Okawara woke up at midnight and jotted down an idea that came to him in a dream: a “party barrel” to be sold on Christmas.

Okawara dreamed up the idea after overhearing a couple of foreigners in his store talk about how they missed having turkey for Christmas, according to Nakatani. Okawara hoped a Christmas dinner of fried chicken could be a fine substitute, and so he began marketing his Party Barrel as a way to celebrate the holiday.


In 1974, KFC took the marketing plan national, calling it Kurisumasu ni wa Kentakkii, or Kentucky for Christmas



In 1974, KFC took the marketing plan national, calling it Kurisumasu ni wa Kentakkii, or Kentucky for Christmas. It took off quickly, and so did the Harvard-educated Okawara, who climbed through the company ranks and served as president and CEO of Kentucky Fried Chicken Japan from 1984 to 2002.




People walk beneath Christmas decorations in the Marunouchi shopping district of Tokyo on December 2, 2016 (Credit: Getty Images)



The Party Barrel for Christmas became almost immediately a national phenomenon, says Joonas Rokka, associate professor of marketing at Emlyon Business School in France. He has studied the KFC Christmas in Japan as a model promotions campaign.

“It filled a void,” Rokka says. “There was no tradition of Christmas in Japan, and so KFC came in and said, this is what you should do on Christmas.”

Advertisements for the company’s Christmas meals show happy Japanese families crowding around barrels of fried chicken. But it’s not just breasts and thighs – the meals have morphed into special family meal-sized boxes filled with chicken, cake, and wine. This year, the company is selling Kentucky Christmas dinner packages that range from a box of chicken for 3,780 yen, ($32), up to a “premium” whole-roasted chicken and sides for 5,800 yen. According to KFC, the packages account for about a third of the chain’s yearly sales in Japan.

It also helped that the stores dressed up the company mascot, the smiling white-haired Colonel Sanders, in Santa outfits. In a country that puts high value on its elders, the red satin-suited Sanders soon became a symbol of a holiday.

‘One of the strangest things I’ve heard’

This phenomenon is unique to Japan – and can seem strange to some outside the country. The idea is unlikely to take off in the home of KFC, says Kevin Gillespie, chef of two restaurants in Atlanta, Georgia.


If you brought a bucket of fried chicken to Christmas dinner, honestly, I’d be mad at you



“KFC on Christmas. It’s one of the strangest things I’ve heard,” Gillespie says. “If you brought a bucket of fried chicken to Christmas dinner, honestly, I’d be mad at you.”

It isn’t a crack on KFC’s products necessarily, says Gillespie. The general idea of bringing fast food to Christmas dinner “would be viewed as rude by most anyone,” Gillespie says.

In Japan, however, where around 1% of the population is Christian, Christmas isn’t an official holiday, Rokka says. So the idea that families are going to spend all day cooking a ham or turkey and side dishes just isn’t practical. Instead, they show up with a bucket of chicken.


This is another sign of globalisation, where rituals spread to other countries and get translated in different ways



“This is another sign of globalisation, where consumer rituals spread to other countries and often get translated in different ways,” Rokka says. “It’s not abnormal now to have an Ikea store everywhere in the world. This KFC for Christmas is just taking our consumerism and turning it into a holiday.”




After the manager of Japan’s first KFC overheard foreigners talk of how they missed Christmas turkey, a nationwide tradition was born (Credit: Getty Images)



An excuse for a reunion

Having done some travelling abroad, Ando knows that his country might is alone in celebrating Christmas with a bucket of KFC. But for him, he sees the tradition as more than just a company promotion.


It’s not about the chicken. It’s about getting the family together



For Ando, he’s still planning to get KFC for his kids this year. But he goes to a bakery for the Christmas cake. On Christmas night, the family will gather around the KFC bucket, just as Ando once did as a child, and just as his children will do in another generation.

“It’s kind of a symbol of family reunion,” Ando says. “It’s not about the chicken. It’s about getting the family together, and then there just happens to be chicken as part of it.”

በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ላይ እያለች ሎተሪ እንደደረሳት ስታውቅ የሥራ ባልደረቦቿን 'ነገ ሥራ አልመጣም' ያለችው ስፔናዊት ጋዜጠኛ ይቅርታ ጠየቀች።



ስፔናዊቷ ጋዜጠኛ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ላይ እያለች ሎተሪ እንደደረሳት ስታውቅ ለጓደኞቿ ከነገ ጀምሮ ስራ እንደማትመጣ ተናግራለችImage copyrightGETTY IMAGES

ናታልያ እስኩድሮ አርቲቪኢ ለተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ የምትሰራ ሲሆን፤ የቀጥታ ስርጭት ላይ እያለች ሎተሪ እንደደረሳት ስታውቅ በደስታ ተሞልታ እየጮኽች በነጋታው ወደ ሥራ ገበታዋ እንደማትመጣ ተናግራለች።
ነገር ግን ቆየት ብላ የደረሳት ሎተሪ በጠቅላላ 4 ሚልዮን ዩሮ ከሚያስገኘው ዕጣ ናታልያ የደረሳት 5ሺህ ዩሮ ብቻ መሆኑን ተረድታለች።
የገና ሎተሪው ከፍተኛ ሽልማት 4 ሚሊዮን ዩሮ ቢሆንም ብሩ ግን ለበርካታ አሸናፊዎች የሚከፋፈል ነበር። ናታልያ ይህንን እንዳወቀች ለድርጊቷ ይቅርታ ጠይቃለች።
ናታልያ እንዳለችው እንደዛ "ስሜታዊ" ሆና በመናገሯ እንደተፀፀተችና ባደረገችው ነገር ጥሩ ስሜት ላልተሰማቸው ተመልካቾቿም ስለሁኔታው እንደምታብራራ ገልፃለች።
የናታልያ ምላሽ የመጣው የቴሌቪዥን ምስሉ በሰፊው ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ ሲሰራጭ 'ሙያዊ ስብዕና ይጎድላታል' የሚል ክስ ከቀረበባት በኋላ ነው።
በሎተሪው ዕጣ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ሻምፓኝ ተከፍቶ፣ ትልቁ የዕጣ መጠን በሚነገርበት ግዜ ናታልያ በደስታ ስትዘል በቀጥታ በቴሌቪዥን ተላልፏል።
ተመልካቾችም ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንዳሸነፈችና ሥራዋንም እንደምታቆም የገለፀችበት አኳኋንን እንደነቀፉት የስፔን መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል።
ይህ የእርሷን ስሜት የያዘው ስርጭት ከተላለፈ በኋላ እስኩድሮ ዳግመኛ በቴሌቪዥን መስኮት ላይ ብትቀርብም ብዙም አላወራችም።
ለቀረበባት ትችት ትዊተር ላይ የሰጠችው ምላሽ እንደሚለው በጊዜው ለወራት ያክል ግላዊ በሆነ ምክንያት ችግር ገጥሟት የነበረ ቢሆንም በ25 ዓመት ብቁ በሆነ የጋዜጠኝነት ህይወቷ በቅንነት ተግታ እንደሰራችና እንደምትኮራበትም ተናግራለች።
"ናታሊያ እስኩድሮ አደናጋሪና ውሸታም የአርቲቪኢ ጋዜጠኛ" ተብላ ትዊተር ላይ ለተፃፈው ክስና ለተፈጠረው ግራ የሚያገባ ድርጊቷ ይቅርታ በመጠየቅ አሰትባብላለች።

ጃኖ ባንድ በኤርትራ እንዳይዘፍን የተደረገው ሙዚቃ አለ?


የጃኖ ሙዚቃ ቡድን አባላትImage copyrightJANO BAND OFFICAL/INSTAGRAM
ወደ ኤርትራ የሙዚቃ ሥራዎቹን ለማቅረብ ከተጓዘው የባህል ቡድን መካከል አንዱ የሆነው 'ጃኖ ባንድ' መድረክ ላይ ሥራውን እያቀረበ እያለ እንዲያቋርጥ መደረጉን በተለያዩ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ሲገለጽ ተሰምቷል።
የሙዚቃ ባንዱ ሥራውን እንዲያቋርጥ የተደረገው 'ይነጋል' የሚለውን ሥራውን እያቀረበ እያለ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፤ ይህ የሆነውም በምጽዋ ከተማ በነበረው የሙዚቃ መድረክ ላይ እንደነበረ አንዳንዶች ጠቅሰው መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
የባንዱ አባል የሆነው ጊታሪስት ሳሙዔል አሰፋ እንዲሁም የባንዱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳሙዔል ተፈራ ለቢቢሲ እንደገለጹት "ይህ አሉባልታ ሐሰት ነው።"
አቶ ሳሙዔል ተፈራ ለቢቢሲ እንዳስረዱት በኤርትራ ለጃኖ ባንድም ሆነ ለአጠቃላይ የልዑካን ቡድኑ የነበረው አቀባበል እጅግ በጣም የተለየ ነበር።
"የሚያለቅሱ ሁሉ ነበሩ" ያሉት አቶ ሳሙዔል የጃኖ ባንድ በልዑካን ቡድኑ ውስጥ የተካተተው በኤርትራዊያኑ ጥያቄ እንደነበር ገልፀዋል።
ምጽዋ በነበረን የሙዚቃ መድረክ ላይ በርካታ ሙዚቀኞች ሥራቸውን አቅርበዋል የሚለው ጊታሪስት ሳሙዔል፤ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ድምጻዊያን ረዥም ሰዓት በመውሰድ ሥራቸውን ማቅረባቸውን ይናገራል።
የጃኖ ባንድ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሳሙዔል በበኩላቸው "የሙዚቃ ድግሱ ሲቀርብ የነበረው በጄኔሬተር ስለነበር እና ቡድኑ ሥራውን ያቀረበው መጨረሻ ላይ በመሆኑ እንዳይቋረጥባቸው በሚል እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለው" ይገልፃሉ።
አቶ ሳሙዔል አሰፋ በበኩላቸው ባንዱ ወደ መድረክ ሲወጣ ያላቸው ሰዓት አጭር ስለሆነ ሙዚቃ እንዲቀንሱ እንደተነገራቸው በማስታወስም፤ ከያዙት 19 ሥራ 13ቱን ማቅረባቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል።
" 'ይነጋል' የሚለውን ሥራችንን አቅርበን 'ዳሪኝ' የሚለውን ጀምረን እያለ እንድናቋርጥ ተነግሮናል። ምክንያቱም የነበርንበት አካባቢ ከመሸ በኋላ [በከፍተኛ ድምጽ] መረበሽ ስለማይቻል እንደሆነም ሰምተናል" ብሏል።
ሳሙዔል አክሎም ሙዚቃቸውን ባቀረቡበት ስፍራ ሁሉ የሕዝቡ አቀባበል ደስ ይል እንደነበር በማስታወስ እነርሱም በሕዝቡ አቀባበልና በሥራቸው ደስተኛ እንደነበሩ ገልጿል።
በየሄድንበት ሁሉ ፈንዲሻ እየተበተነ የመሪ አቀባበል ነው የተደረገልን ያሉት ደግሞ ሥራ አስኪያጁ ናቸው።
ጃኖ ባንድ በኤርትራ ታዋቂ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ በአሥመራ የሚገኙ የሙዚቃ ፕሮሞተሮች ዳግመኛ መጥተው ሥራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ እንደጠየቋቸው እነርሱም በድጋሚ ለመሄድም ሀሳቡ እንዳላቸው ገልፀዋል።
የጃኖ ባንድ አባላት በአሥመራ በነበራቸው ቆይታ በነጻ የሙዚቃ ሲዲያቸውን መስጠታቸውንና በቆይታቸው ደስተኛ እንደነበሩም ጨምረው አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላትImage copyrightYEMANE G. MESKEL/TWITTER
የኢትዮጵያ የሙዚቃ ልዑክ ወደ ኤርትራ ያቀናው ባለፈው ሳምንት ታኅሣሥ 6 ቀን 2012 ዓ. ም ሲሆን ከስድሳ በላይ አባላትን ይዟል።
የኢትዮጵያ የባህል ቡድን በኤርትራ ሦስት ከተሞች የሙዚቃ ትርዒቱን እንደሚያቀርብ ቀድሞ የተነገረ ቢሆንም በምጽዋና በአሥመራ ብቻ ማቅረቡን ለማወቅ ችለናል።
ልዑካን ቡድኑ አባላት ከውጭ ጉዳይ፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴሮች፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ ከታዋቂ ድምፃዊያንና ከጃኖ ባንድ የተወጣጡ ነበሩ።
በትናንትናው ዕለት በአሥመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ የመጨረሻ ሥራቸውን ማቅረባቸውንም የጃኖ ባንድ ሥራ አስኪያጅ ጨምረው ተናግረዋል።
የኤርትራ ስፖርትና ባህል ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዘመዴ ተክሌ ለኤርትራ መገናኛ ብዙኀን እንዳሉት "በሁለቱ አገራት የሚደረገው የባህልና የኪነ ጥበብ ልውውጥ የሁለትዮሽ ግንኙነትን በማዳበርና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ይረዳል።"
ኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት በበኩላቸው፤ ይህ ጉብኝት ባለፈው በኤርትራ የባህል ቡድን የተጀመረው ቀጣይ ምዕራፍ እንደሆነ በመግለጽ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከዚህ ባላይ ሊያድግና ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል።
ቡድኑ የሙዚቃ ሥራውን በአሥመራና ምጽዋ ያቀረበ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።
ከዚህ በፊት የኤርትራ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ባህርዳር፣ አዳማ፣ ሀዋሳ እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ የሙዚቃ ሥራዎቹን ማቅረቡ ይታወሳል።

"በጎጃም ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስጊድ 3ሺ ብር ረድታለች' ተባልኩኝ" ሐጂ ዑመር ኢድሪስ



ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በሚሊንየም አዳራሽ ከጠ/ሚ ዐብይ የክብር ዶክትሬት በተቀበሉበት ወቅትImage copyrightOFFICE OF THE PM
አጭር የምስል መግለጫተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በሚሊንየም አዳራሽ ከጠ/ሚ ዐብይ የክብር ዶክትሬት በተቀበሉበት ወቅት
ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባለፈው ቅዳሜ በሚሌኒየም አዳራሽ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ይህንኑ ተከትሎ ከሙፍቲህ ሐጂ ዑመር ጋር ያደረግነውን አጭር የስልክ ቃለ ምልልስ እነሆ፤ [ማስታወሻ፡ በርሳቸው የተነገሩ የአረብኛ ቃላትን ሙሉ በሙሉ ከመግደፍ ይልቅ በቅንፍ አቻ የአማርኛ ትርጉም መስጠትን ወደናል።]
እንኳን ደስ አለዎት ሐጂ፤ ያውቁ ነበር እንዴ እንደሚሸለሙ? መቼ ነበር የሰሙት?
ወላሂ አሁን ለታ..ማነው ሐሙስ ማታ ነው ታከለ፣የተከበሩ ምክትል ከንቲባ፣ ደውለው የነገሩኝ። 'ቅዳሜ እንዲህ ያለ ነገር ስላለ እንዲትመጡልን' ብለው ምክትል ከንተባው ደወሉልኝ። አሁን ለታ ማታ። በጣም ነው የደነገጥኩት፣ እኔ እንዳው።ይሄ ነገር መስመሬም ስላልሆነ ደሞም ያሰብኩትም፣ የጠረጠርኩትም ስላልሆነ በጣም በጣም ነው 'ያኣጀበኝ' [የደነቀኝ]፤ አለቀስኩኝ የሚገርምህ ነገር...ወላሂ አለቀስኩኝ...
ሐጂ! ለምን የተሸለሙ ይመስሎታል ግን...?
ምን አልከኝ...ልጄ!
በምን ምክንያት የተሸለሙ ይመስሎታል...ምን ስላበረከቱ...?
ወላሂ እንግዲህ የሽልማቱ ምክንያት የልፋት ውጤት ነው የሚመስለኝ። እንግዲህ አዲስ አበባም 54 ዓመቴ ነው ከመጣሁ። እንግዲህ እዛም አገራችን 'ስቀራ' [ቅዱስ ቁርዓንን ስማር]፣ ሳስቀራ [ሳስተምር]...በሌላም በሌላም ለሕዝብ ልፋቴ በጠቅላላ ወደ 70 ዓመት ይሆናል። አንድ ቀን ለልጆቼ ወይ ለራሴ ብዬ አላቅም።
በየክፍለ አገሩ በየዞኑ በየወረዳው እዞራለሁ። በኢትዮጵያ በሙሉ 'ፈትዋ' ሳደርግ ነው የኖርኩት። ደግሞ በኋላ አንድነት ብለን የዛሬ 11 ዓመት ገደማ ጀምረን ነበር። ኋላ አንድነቱ ደስ ያላላቸው ሰዎች አፍርሰውት ነበር። [እኔንም] ተው አሉኝ፣ ተውኩት። አላህ ደግሞ ጊዜያት አምጥቶት የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ እሳቸው ናቸው እንግዲህ ወደ አንድነት እንድንሄድ ያደረጉን። 'ጀዛቸውን' [ውለታቸውን] አላህ ይክፈላቸው።
አላኩሊሃል [ያም ሆነ ይህ] ሽልማቱ መሠረቱ የመሰለኝ አንደኛው በሙስሊሙና በክርስቲያኑ መካከል ሰላምና አንድነት የምፈልግ መሆኔና በዚህም መልፋቴ። ሁለተኛ በመንግሥት እና በሕዝበ ሙስሊሙ መካከል የሚያቀራርብ ሰላም መፈልጌ፤ ሦስተኛ ሙስሊሙና ሙስሊሙ ደግሞ ከመቃረን፣ ከመዳማት [ወጥቶ] አንድ መሆን አለበት እያልኩ እንግዲህ ወደ 40 ዓመታት መድከሜ ይመስለኛል። ዋናው ይሄ ይመስለኛል።
ከይህ ሌላ 'አላኩሊሃል' [እንዲሁ በአጠቃላይ] የሙስሊም አገልግሎት በብዙ ዓይነት ነው። በማስተማር በዳእዋ [የስብከት አገልግሎት]። ቁርዓን እንዲሁ በሁለት በሦስት ዓይነት ተርጉሚያለሁ። ሌሎችም የተውሂድ ኪታቦችን [መጻሕፍትን] ብዙ የተረጎምኳቸው አሉ።
ሌላ በአረብኛ ደግሞ 'ዱአ'ን [ጸሎትን] በተመለከተ የነብያችንም ውዳሴ በተመለከተ ወደ 80 መጽሐፎች በአማርኛ ደርሻለሁ። እንግዲህ መቼም 'አላኩሊሃል' [ከሞላ ጎደል] ሕይወቴን መቼም የጨረስኩት ሕዝብን በሚያቀራርብ ነገር ነው።
አሁንም ደግሞ ዶ/ር ዐቢይ አንድነት ኮሚቴ ሰብሳቢ አድርጎኝ በዚያ ምክንያት አንድነት ባይገኝ ኖሮ ብዙ ደም እንደሚፋሰስ ሙስሊሙ በጣም በጣም ከባድ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ነበር ጥርጣሪያችን፤ አልሀምዱሊላህ ይኸው መቼም አንድነቱ ተከናውኖ ጀምረነዋል። አላህ መጨረሻውን ቢያሳምረው መቼም።
በአጠቃላይ ስለ ሙስሊሙም ሆነ ስለ ክርስቲያኑ፣ ስለመንግሥትም ሆነ ስለ ሕዝብ በለፋሁት ልፋትና በተጨነኩት ምክንያት ይመስለኛል [የተሸለምኩት]።..ብዙ አልቅሻለሁ፤ ብዙ ለቅሶ ነው ያለቀስኩት [ይህ እንዲሆን]። በዚያ መነሻ አላህ ይህን [ስጦታ] ያመጣው ይሆናል እንጂ የምለው... እኔ [ይህ ይመጣል ብዬ] የጠረጠርኩት ጉዳይ አይደለም። መንግሥትም ይሄን ጉዳይ ያስብበታል ብዬ ትዝ አላለኝ...።
ለሃይማኖት አባት እንደዚህ ያለ ደረጃና ሽልማት መሸለም በተለይ በአገራችን እኮ ይሄ የመጀመርያ ነው፤ ታይቶም አይታወቅም፤ ተሰምቶም አይታወቅም። ለክርስቲያኖች አልተሠራም፣ እንኳን ለሙስሊሙና። እኔ ብቻ ሳይሆን የሚያስደስተኝ ሙስሊም ሁላ ሊደሰትበት የሚገባ ነው። በሕይወት ያሉት አደለም የሞቱት የታገሉት አባቶቻችን ሁላ ውጤት ነው የሚል አመለካከት ነው ያለኝ መቼም...
ሐጂ ዑመር፤ ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን የሌላ እምነት ተከታዮችም'ኮ እንደ ሃይማኖት አባት ለርስዎ መልካም ስሜት ያላቸው ይመስለኛል፤...ሰዎች ያንን ይነገርዎታል? እርስዎስ ያውቃሉ ይሄን?
አውቃለሁኝ'ና፤ አሁንም ሳይሆን ፊትም ቀደም ባለ ጊዜ መጅሊስ ባለ ጊዜ ከ[ሃይማኖት] አባቶች ጋራ ስንሰባሰብ፣ ስንነጋገር ወዲያው እዚያው ጽፈው ይሰጡኛል። 'እርስዎ ንግግርዎ ወርቅ ነው፤ ብር እንኳ አይደለም፣ ወርቅ ነው' ይሉኛል።
ሁለተኛ ደግሞ አጠቃላይ ነው ስለሃይማኖትህ ብቻ፣ ስለመስጊድ ብቻ ሳይሆን አንተ የምትናገረው ስለ አጠቃላይ ስለ ሙስሊሙም ስለክርስቲያኑም፣ ስለሆነ ንግግርህ መልካም ነው ይሉኛል። 'እንዳው ሙስሊሞች ጥሩ መሪ ሰጥቷቸዋል' እያሉ ሁልጊዜ ጽሑፍም ይሰጡኛል።
ባሁን ደግሞ እኔንጃ ከሙስሊሙ የበለጠ ክርስቲያኑ ነው ደስ ያለው የሚመስለኝ። በትናንቱ ሁኔታ ከሙስሊሙ የባሰ ክርስቲያኑ ነው ደስ ያለው።[እሑድ' ለታ ነበር ያነጋገርናቸው] በሄድኩበት 'አብረነህ ፎቶ እንነሳ፣ ዕድሜህ ይቆይልን' የማይል አንድ እንኳ የለም።
እኔም ደሞ ሙስሊምና ክርስቲያን ልዩነት የለኝም። የብሔር፣ የሃይማኖት ልዩነት አላውቅም፤ ድሀ ሀብታም አልልም። የተማረ ያልተማረ አልልም። እምነቴና አመለካከቴ እኩልነት የተመረኮዘ ስለሆነ የዚያ ውጤት ቢሆን ነው እንጂ [ተሸለምኩ] የምለው በጣም እንደው [የሰው ፍቅር] ካቅሜ በላይ ነው። ይህን በጣም አመሰግናለሁ።
ዕድሜዎ ስንት ደረሰ ሐጂ?
አሁንም ምናልባት ወደ 85ኛ ሳልጀምር አልቀርም... ይመስለኛል።
ጠ/ሚ ዐቢይ መምጣት ጋ ብዙ ተስፋዎች ነበሩ፤ አሁን ደግሞ 'ይቺ አገር መፍረሷ ነው፤ የሃይማኖትም ሆነ የብሔር እልቂት አይቀርላትም' የሚል ፍርሃት አለ። እርስዎ እንደው በቀረው የሕይወት ዘመንዎ ይህ ክፉ አጋጣሚ ይመጣል ብለው ይጨነቃሉ?
እኛ እንግዲህ በንጉሡ ጊዜ መቼም ዳር እስከ ዳር የኢትዮጵያ ሰላም ነበረ፥ እኛ የምናውቀው እንኳ በአገራችን በገጠር እንኳ በመንግሥት የተባለ እንደሁ የተቀመጠው አይነሳም፣ የቆመው አይቀመጥም። እግሩ ሊራመድ አንስቶ እንደሆነ መሬት አያስቀምጥም። ያንን ወቅት አይተናል።
በደርግም ደግሞ ያንን እልቂት፣ ያንን ረብሻም፣ ያንን 'ፊትና'ም [የሕይወት ፈተና] ደግሞ አይተናል።
ከዚያም በኢህአዴግ እንዲሁ ያየነውን አይተናል።
አሁን ግን የኔ አመለካከትና እንደኔ ሐሳብ ተሆነ ለእውነቱ እኔ ሰው አለሥራው ማመስገን አላውቅም። ዶ/ር ዐቢይ በተመረጡ ጊዜ በማግሥቱ ሲጠይቁኝ 'ባካችሁ ተስድስት ወር በኋላ ጠይቁኝ፤ አሁን አመስግኜ በኋላ ማማረር አልፈልግም' ነው ያልኳቸው።
እና አሁን ያሉት መሪ አመለካከታቸው አንድነት፣ ሰላም፣ ልማት፣ ዕድገት ስለሆነ 'የሚያአጅብ' [የሚደንቅ] እኮ ነው። አይተንም ሰምተንም አናውቅም። የደካሞች ቤት እኮ እየተሠራ ነው'ኮ በምክትል ከንቲባና በዶ/ር ዐቢይ አመራር። የሽማግሌዎች የባልቴቶች ቤት እየተሠራ ነው።
መቼም አሁን ችግር እፈጥራለሁ ቢል ችግር ፈጣሪውም ይሳካለታል ብዬ ምንም ሐሳብ የለኝም። ጥርጣሬም የለኝም። ይሄን [መልካም ጅማሮ] መቼም የማይቀበል አእምሮ ያለው ሰው፣ አለ ብዬ አልገምትምና ሁሌም አገራችን ታድጋለች፣ ትለማለች፣ አንድነታችን ይጠናከራል የሚል ሐሳብ ነው ያለኝ እንጂ እኔ አገር ይፈርሳል፣ ሽግር ይፈጠራል አልልም።
በዚህ ረመዳን ወቅት በሙስሊም አካባቢ ሰላም ይከርማል ወይ ብሎ ሰው ጥርጣሬም ነበረው፤ አላህ ግን ሰላም አክርሞናል። ሐሳቤ የኔ አመለካከትም ይኸው ነው። ከይህ ሌላ ያለውን ደግሞ 'ረበል አለሚን አላህ' [የዓለማቱ ጌታ] ያውቃል።
አላህ ደግሞ ችግር ፈጣሪውን ወደ ሰላም እንዲመለስ፣ ሥልጣን ፈላጊውም በመንገዱ እንጂ አለመንገዱ እንዳይፈልግ አላህን እንለምናለን፤ ዱአ አናደርጋለን።
ዓለማዊ ትምህርትን ምን ያህል ገፍተውበታል ሐጂ?
ዓለማዊ ትምህርት የለኝም፤ እኛ ከቶም ሀሁ ማለት ያን ጊዜ ፊደል በ'መሻኪኮቻችን' [በሃይማኖት አዋቂዎች ዘንድ] እና እንደ 'ኩፍር' [ከሃይማኖቱ ማፈንገጥ] ነበር የምንቆጥረው። እኛ ነን ከተማ ከገባን በኋላ አሁን ደረሳውንም ተማሩ ያልነው። ያን ጊዜ ከተማረ በሴት ወይ በሥልጣን ደልለው 'ያከፍሩታል' [ሃይማኖቱን ያስጥሉታል] ተብሎ በወሎ ኡለማው በጣም ያስጠነቅቅ ነበር። ስለዚህ እኔ ሃይማኖታዊ እንጂ ዓለማዊ ትምህርት የለኝም።
ግን የሚገርመው ዓለማዊ ትምህርት የተማሩትን ጽፈው ያመጡትን ማስተካከል እችላለሁ። ይሄ የተፈጥሮ ጸጋ ይመስለኛል።
ከወሎ ብዙዎቹ ወደ አልአዝሃር ዩኒቨርስቲ እየሄዱ ይማሩ ነበር በዚያን ጊዜ?እንዴት ሳይሄዱ ቀሩ?
አልአዝሃር አልሄድኩም። ከወሎ ብቻ ነው የተማርኩት፤ ሐጂ መሀመድ ሳኒ ዘንዳ መጣሁ እንጂ ..። ደግሞስ ለሃይመኖት ትምህርት አል አዝሃርም ሆነ ማንም ሆነ እንደው ዲግሪ ለመቀበሉ፣ ስም ለማውጣት ነው እንጂ በትምህርት በኩል እኮ የአገራችንን 'ዑለማ' [የሥነ መለኮት ምሁር] የመሰለ አንድ እንኳ በዓለም አይገኝም። ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው የአገራችን 'ዑለማዎች' ናቸው። ችግሩ ብቻ ወደ ከተማ አልገቡም፤ እና ወደ አመራሩም ኪታብ ወደማበጀቱ [መጽሐፍ መድረሱ] ውስጥ አልገቡም ነው እንጂ አገራችን ዑለማዎችን የሚያህል አንድም የለም፤ በየትም።
እርስዎ የቀድመው ተወዳጅ የሃይማኖት አባት ሐጂ መሐመድ ሳኒ ሀቢብ ተማሪ ነዎት እንዴ?
አዎ እርሳቸው ዘንዳ 'ሐዲስ 'ልቀራ'፣ ሌላውን 'ፊቂሁን' [ኢስላማዊ ሕግ] ነህው [የአረብኛ ሰዋሰው] ጨርሼ እዛ ተመልሼ ሼክነት ልወጣ ነበር ሼኮቹ የላኩኝ። አላህ እሳቸውን እዚህ [አዲ'ሳባ] አመጣ፣ እሳቸውን ብዬ እዚህ መጣሁኝ፤ እዚህ ሕዝብ ያዘኝ፣ በዚያው ቀረሁ፣ እሳቸውም እዚሁ ቀሩ።
በሚሊንየም አዳራሽ በብዙ ሙያ ዘርፍ ለተመረቁ ብዙ ሺህ ተማሪዎች ንግግር ሲያደርጉ ነበር። እርስዎ ግን የቱ ትምህርት ዘርፍ ይበልጥብዎታል?
[ሳቁ] እኔ ይሄን ይሄን አልልም። ሁሉም ጠቃሚ ነው። ያስተዳደሩን ብታየው፣ አለ አስተዳደር አይሆንም። የኢኮኖሚውን ብታየው አለ ኢኮኖሚስት ታልሆነ መቼም ይሆንም። የማስተማርም ሙያ ብታየው አስተማሪ ከሌለ ተማሪ የለ። እና ዕውቀት ሁሉም አስፈላጊ ነው። ሁሉም አንገብጋቢ ነው። ግን እገሌ ከእገሌ ትምሀርት ይሻላል አልልም። ዝንባሌው እንጂ በኔ በኩል ሁሉም እኩል ጠቃሚ ነው፤ ሁሉም ጥሩ ነው የሚል አመለካከት ነው ያለኝ፤
እኔንኳ ጥያቄዬ የነበረው ሐጂ... እርስዎ ዝንባሌዎ ምን ነበር? ከዓለማዊው ትምህርት...
ወላሂ እኔ ብማር ኖሮ የምማረው ኢኮኖሚን በተመለከተ ይመስለኛል። እኔ ሼክነቱ በቀረ ነጋዴ ነበር የምሆነው። ሥልጣንን አልወደውም። የአመራር ትምህርት አልመርጥም። የኢኮኖሚ ትምህርት ነበር የምመርጠው ይሆናል።
የግል ሕይወት በተመለከተ ትንሽ ጥያቄ ላንሳልዎ? ስንት ቤት አለዎ...?ስንት መኪና?
[በአጭሩ ከሳቁ በኋላ] እኔ የምኖርበት ብታየው ያስቀሃል፣ ያስገርምሃል። እላይ መርካቶ ቤት ነበረኝ። እኔ መስጊድ እሠራለሁ እንጂ መኖርያ ቤት አልሠራም ብዬ የሚመጣው ሁላ 'የሙፍቲ ቤት ይሄ ነውንዴ?' ጉድ አረ ይሄን ቤት ለውጡ' ያላለኝ ሰው የለም። አሁን ደግሞ አዲስ ቦታ ነው ያለሁት።
ሁን የት አካባቢ ነው የሚኖሩት ታዲያ?
እዚህ ጋርመንት የሚባል ሐና ማርያም ይባላል። በሱ አሻጋሪ ነው የምኖረው። አሁን እዚህ ከመጣሁ ሦስት ዓመቴ ነው። ሰፊ ቦታ ነው። ቆርቆሮ ነው፤ ግድግዳውም፣ ጣሪያውም ቆርቆሮ በቆርቆሮ ነው። ግን ሰፊ ነው።
ይሄን ያህል'ኮ ጭንቅ የለኝም፤ እኔ አዲስ አበባ ይሄን ያህል 54 ዓመት ስቀመጥ ሙተአሊም [ተማሪዎቼ] ጋ ነው የምቀመጠው። የምበላው ሙተአሊም ጋ ነው። ገንዘቤን ለሙተአሊም ነው የማወጣው። ይሄን ያህል የደላ ኑሮም የለኝም።
ስንት ልጆች አለዎት?
ዐሥራ አንድ ነበሩ። አንድ ሞቷል። አሁን 10 አሉ።
እርስዎ የመጡት ከወሎ አካባቢ ይመሰለኛል እና እዛ ደግሞ ሙስሊምና ክርስቲያኑ በመተሳሰብ ተፋቅሮ የመኖር ጠንካራ ባህል አለ። የተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ከዚያ አካባቢ ምን ሊቀስም ይችላል?
ወላሂ እኛ እንግዲህ እስካለንበት ሕይወት ድረስ በወሎ ክፍለ አገር የብሔር ወሬ ጭራሽ የለም። ሁለተኛ የሃይማኖትም ልዩነት የለም። ወጣቶች ሙሽርነት እንኳ አብረው ይሞሸራሉ። ልዩነት ነገር አናውቅም፤ ሙስሊሙ ቤተክርስቲያን ሲገነባ ይረዳል፤ክርስቲያኑ ደግሞ መስጂድ ሲሠራ ይረዳል። የሚገርመው ክርስቲያኑ ደረሳ [መንፈሳዊ ተማሪዎች] ጠርቶ፣ አርዶ፤ አሳርዶ ሰደቃ [ዝክር] ይሰደቃል [ያበላል]። ይሄ ወሎን በተመለከተ ነው።
ሌላው ቀርቶ ክርስቲያኑ አገር የሚባለው ጎጃም ሎማኔ የሚባል ከተማ መስጊድ ለምርቃት ሄጄ 'እገሌ ክርስቲያን ለመስጊድ ይሄን ያህል ረድቷል፤ እገሌ ደግሞ ይሄን ረድቷል፤ ከተባለ በኋላ በመጨረሻ 'ማርያም ቤተክርስቲያን 3ሺ ብር ረድታለች' ብለው ነው ያቀረቡልን። እንደዚያ ተባልኩኝ።
ይሄ ነው ሕዝባችን። የፖለቲካ ሰዎች በታተኑት እንጂ የኢትዮያ ሕዝብ የብሔር ልዩነት አያቅም፤ የሃይማኖት ልዩነት አያውቅ። ይሄ አሁን [በሃይማኖት መቃቃር] መጤ ተግባር ነው። እና እንዲህ ያለውን አሁንም ቢሆን ከሕዝቡ ልብ ላይ እንዲፋቅና እንዲለቅ ማድረግ ያስፈልጋል። ለመፋቅ ወደፊት ብዙ ዓመታት ይጠይቃል ነው እንጂ የምለው መልቀቁ መቼም እንደማይቀር ነው።
ባለሥልጣኖች እንዲሁ ለሥልጣናቸው ሲሉ [ሕዝቡ ላይ] መርዝ ነሰነሱበት እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ አልነበረም። እኛ ተወሎ በዚህ በአርሲ በባሌ በጅማ የመጣ እንደሆነ ተከብሮ ተረድቶ ነበር የሚኖረው። ባሌን ያቀና የወሎ 'ኡለማ' ነው፤ አርሲን ያቀና የወሎ ኡለማ ነው፤ ጅማን በአባጂፋር ጊዜ ያቀና የወሎ ኡለማ ነው፤ ልዩነቱ እኮ በአገራችን አናውቅም ፤ ከመጣበት አናውቅም፤ በሽታው ከመጣበት ይመለስልን እያልን ነው [ዱአ የምናደርገው]።
እየከፋ የመጣውን ዘረኝነትንስ በተመለከተስ ምን ይላሉ ሐጂ...
ዘረኝነትን በተመለከተ ሃይማኖታችን 'ቆሻሻ ነው' ብሎ ነው የሚለው። ነብያችን (አለሂሰላቱ ወሰላም) 'ወደ ዘረኝነት መጠጋት፣ እኔ የገሌ ዘር ነኝ ብሎ በቀለም፣ በሀብት ወይ በሌላ ማድላት፣ መኩራራት ይሄ የሚሸት ነገር [ክርፋት] ነው' ነው ብለው ነው ያስተማሩት።
አሁንም ዘረኝነት ሕዝባችን ቆሻሻነቱን አውቆ እንዲጠነቀቅ ከማስተማር በስተቀር ሌላ ምንም መፍትሄ የለውም። ይለቃል የሚል አመለካት ነው ያለኝ። መልቅቁ ግን ጊዜ ሊወስድ ይችላል።
አንድ በሽታ በአካል ከተሰራጨ መድኃኒቱ ጊዜ ይፈልጋል እኮ፤ ጊዝያዊ በሽታ የሆነ እንደሆነ በአንድ መርፌ በኪኒኒ ይመለሳል። ውሎ ያደረ በሽታ ሕክምና ያስፈልገዋል። [የዘረኝነት] በሽታው ትንሽ ዓመታት ወስዶ ስለነበረ አሁንም ደግሞ ለማስለቀቅ ጥንካሬና ጊዜ ይጠይቃል።
አመሰግናለሁ ሐጂ!
በአገር ጉዳይና በኔ ጉዳይ አስበህ ለመጠየቅህ በጣም አመሰግናለሁ ልጄ፤ ለአገራችንም ሰላም እመኛለሁ፤ ወሰላሙ አለይኩም።

wanted officials