Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, December 22, 2019

አሜሪካ አነፍናፊ ውሾዎቼ 'ነጡ፤ ገረጡብኝ' በሚል ወደ ግብጽና ዮርዳኖስ ላለመላክ ወሰነች



አነፍናፊ ውሻImage copyrightPRESS ASSOCIATION
አጭር የምስል መግለጫአነፍናፊ ውሾች የጸረ ሽብር ተግባሩን ለማገዝ በተለያዩ ሀገራት ተሰማርተው ይገኛሉ
አሜሪካ ፈንጂ አነፍናፊ ውሾችን ወደ ዮርዳኖስና ግብጽ ላለመላክ ወሰነች። እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በቸልተንነት የተነሳ በርካታ ውሾች ከሞቱ በኋላ ነው ተብሏል።
"በተልዕኮ ላይ ያለ የየትኛውም ውሻ ሞት ልብ ይሰብራል" ያሉት የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ናቸው።
በመስከረም ወር የወጣ አንድ ሪፖርት ይፋ እንዳደረገው በዮርዳኖስ፣ ግብጽና ሌሎች ስምንት አገራት ለግዳጅ ከተላኩ ከ100 በላይ አነፍናፊ ውሾች በቸልኝነትና እንክብካቤ ጉድለት የተነሳ መጎሳቆላቸወን አሳይቷል።

የአሜሪካ አነፍናፊ ውሾች የጸረ ሽብር ፕሮግራሙን ለመደገፍ የተሰማሩ ናቸው። ዮርዳኖስም ሆነች ግብጽ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ድረስ አስተያየታቸውን አልሰጡም።
አሜሪካ ጊዜያዊ እገዳዋን ይፋ ያደረገችው ሰኞ እለት ሲሆን የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው እርምጃው የተወሰደው ተጨማሪ ሞትን ለመከላከል ነው።
ውሾቹ "ከሌሎች አገራት ጋር በመሆን የምናደርገውን የጸረ ሽብር ተግባር በመደገፍና የአሜሪካዊያንን ሕይወት በመታደግ ረገድ ቁልፍ ሚና አላቸው" ብለዋል ባለስልጣኑ።
ባለስልጣኑ አክለውም በዮርዳኖስና ግብጽ ያሉት ውሾች ለጊዜው በዚያው ይቆያሉ ብለዋል።
በከፍተኛ ሁኔታ ክብደታቸው የቀነሰ አነፍናፊ ውሾች በጆርዳንImage copyrightCANINE VALIDATION CENTER
አጭር የምስል መግለጫበከፍተኛ ሁኔታ ክብደታቸው የቀነሰ ሁለት አነፍናፊ ውሾች በጆርዳን
የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው እ.ኤ.አ. በ2017 አንድ ውሻ በዮርዳኖስ በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ህይወቱ አልፏል።
ሌሎች ሁለት ውሾች ደግሞ "ክፉኛ ታመው ወደ አሜሪካ ተመልሰዋል" ይላል ሰነዱ።
የአሜሪካ ባለሰልጣናት እንዳሉት ከሆነ ውሾቹ ተጎሳቁለውና ክብደታቸው ቀንሶ ስለነበር ጤንነታቸው እስኪመለስና እስኪያገግሙ ድረስ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው።
በቅርቡ የወጣ ሌላ ሪፖርት እንደሚያሳየው ደግሞ ወደ ዮርዳኖስ ከተላኩ ውሾች ሁለቱ "ተፈጥሮአዊ ባልሆነ ምክንያት" ሞተዋል።
የፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ አንዱ ውሻ በከፍተኛ ሙቀት ሌላኛው ደግሞ የፖሊስ አባል በረጨው የተባይ ማጥፋያ ምክንያት ሞተዋል።
በርካታ አነፍናፊ ውሾች ከአሜሪካ ወደ ዮርዳኖስ የሚሄዱ ሲሆን 100 ያህሉ ደግሞ በመከከለኛው ምሥራቅ አገራት ተሰማርተው ይገኛሉ።
የአሜሪካ ሪፖርት እንደሚያሳየው ወደ ግብጽ ለግዳጅ ከተላኩ ውሾች አስር ያህሉ በሳንባ ካንሰር፣ በከፍተኛ ሙቀት እንዲሁም በሽንት ፊኛ መቀደድ ምክንያት ተልዕኳቸውን መፈፀም አቅቷቸዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials