ኢርትራውያንም በአንድነት ለኢትዮጵያውያን ወገኖች ድምጻቸውን አሰምተዋል
ሕገወጥ ስደተኞች ቢሆኑም ባይሆኑም ከ 20,000 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ በሳዑዲ አረቢያ ዜጎቸ የሚደርሰው ወከባ አስገዾ መድፈር ኢሰብአዊ የሆነ ግርፋት ግድያ በመላው ዓለም እየተወገዘ ይገኛል።በመላው ዓለም የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ እነሆ የወገኖቹ ችግርና ሰቆቃ ሳይነጋገር አግባብቶት በአንድነት ቆሟል።ሁሉም በየሚኖርበት አገር በተቃውሞ ሰልፍ ቁጣውን ሲገልጽ ከርሟል፤እየገለፀም ይገኛል።ኢርትራውያንም በአንድነት ከ ኢትዮጵያውያን ጋር በፍራንክፈርት,በስቶክሆልም….ለኢትዮጵያውያን ወገኖች ድምጻቸውን አሰምተዋል::
ነገር ግን ለሳውዲ ዓረቢያ በማገዝ የኢትዮጵያ መንግስት የአዲስ አበባውን ሰልፍ በትኗል። መበተን ብቻ ሳይሆን ለሰልፉ የወጡ ብዙ ወገኖቹን ወደእስር ቤት ከቷል።ለኢትዮጵያውያኑ ሰልፍ እንዳይደረገላቸው የተከለከለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። በዚህም ሳቢያ አገር ቤት ያለው ህዝባችን ከነ ህመሙእና ከነ ቁጭቱ እየተብሰከሰከ ይገኛል።
ለንደን፣ ደንሀግ፣ፍራንክፈርት፣ኦስሎ፣ስቶክሆልም፣እስራኤል፣በርግ፣ ሄልንስኪ፣ ኤድመንተን፣ ካልጋሪ፣ ኦታዋ፣ቶሮንቶ፣ሲያትል፣ቦስተን፣ ዋሽንግተን ዲሲ፣ሴዑል፣ ሪያድ፣ደቡብ አፍሪካ…..ማን ቀረ? ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከ ዳር ድምጻቸውን ማሰማት ቀጥለዋል።
እስካሁን በዓለም ላይ ለኢትዮጵያውያኑ በግዛቷ ሰልፍ እንዳይደረግላቸው የከለከለች አንዲት አገር ብቻ ነች- ኢትዮጵያ።
እስካሁን በዓለም ላይ ለኢትዮጵያውያኑ በግዛቷ ሰልፍ እንዳይደረግላቸው የከለከለች አንዲት አገር ብቻ ነች- ኢትዮጵያ።
በሰልፎቹ ኢትዮጵያውያን በብዛት ተገኝተዋል።
No comments:
Post a Comment