ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል በሰብአዊ መብት ጋዜጠኝነት መስፈርት አራት ጊዜ ኣዋርድ አሸናፊ ጋዜጠኛ በጋምቤላ ክልል ታሰረ
ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል በሰብአዊ መብት ጋዜጠኝነት መስፈርት አራት ጊዜ ኣዋርድ አሸናፊነቱ የሚታወቀው የናሽናል ጂኦግራፊ የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ሮቢን ሃሞንድ በጋምቤላ ክልል በቁጥጥር ስር መዋሉን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ፓሪስ ከሚገኘው የኢትዩጵያ ኢምባሲ ቪዛ ያገኘው ሮቢን በኢትዩጵያ በተለያዩ ክልሎች በመዘዋወር ፎቶ ግራፍ የማንሳት እቅድ እንደነበረው ተነግሯል፡፡የፎቶግራፍ ጋዜጠኛው ከኢትዩጵያዊ ረዳቱ ጋር ለእስር የተዳረገው 4000 የአሜሪካ ዶላር በእጁ ይዞ በመገኘቱ ነው ሲል ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘግቧል ፡፡ወደ አገር የሚገባ ማንኛውም የውጪ አገር ዜጋ በእጁ የሚገኘውን ገንዘብ ማሳወቅ የሚገባው ቢሆንም ሮቢን ወደ አገር ሲገባ ከገለጸው ገንዘብ በላይ ይዞ መገኘቱ ለእስሩ እንደምክንያት ተወስዷል፡፡
ሮቢን በ2007 በዚምባቡዌ በሁለት አጋጣሚዎች ለእስር ተዳርጎ ነበር፡፡የሮበርት ሙጋቤ አስተዳደር በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ኢ ሰብአዊ ድርጊትና በአገሪቱ የተንሰራፋውን ድህነት በፎቶ ግራፉ ቀርጾ በማስቀረቱ ለ26 ቀናት ታስሮ በመጨረሻ አገሪቱን ለቅቆ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡በጋምቤላ ለእስር የተዳረገበትን ሁኔታየመንግስት ደጋፊዎች ከተናገሩት ውጪ ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልተቻለም ሲል ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘገባውን አጠናቋል።
No comments:
Post a Comment