Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, January 18, 2020

የ30 ዓመቱ ፈረንሳዊ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የአንበሳ ደቦል ደብቆ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።


የአንበሳ ደቦል
Image copyrightPA
አጭር የምስል መግለጫባለሥልጣናቱ የዱር እንሰሳትን እንደለማዳ እንሰሳ ቤት ውስጥ ማቆየት ወንጀል ስለመሆኑ ሲናገሩ ነበር

እንደ ፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ ፖሊስ መረጃው የደረሰው ግለሰቡ የስድስት ሳምንት ዕድሜ ያላትን ደቦል በ 10 ሺህ ዮሮ ለመሸጥ ሲያስማማ ነው።
ማክሰኞ ዕለት ጎረቤቶቹ ቤት ቁምሳጥን ውስጥ የደበቃት ሲሆን ደቦሏ ግን የሕፃን አልጋ ላይ ተገኝታለች።
ደቦሏ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ የተነገረ ሲሆን ለዱር አራዊት ባለሥልጣናትም ተላልፋ ተሰጥታለች።
እንደ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ወንጀለኛው ልማደኛ ሌባ ነበር ተብሏል።
ፖሊስ በሕገወጥ መልኩ በሰዎች መኖሪያ ውስጥ የዱር እንስሳትን ሲያገኝ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም።
በ2017 አንድ ግለሰብ በምግብ እጥረት የተጎዳ የአንበሳ ደቦል ሰው በማይኖርበት ሕንፃ ውስጥ ደብቆ መገኘቱ ይታወቃል። ወንጀለኛው የተደረሰበትም ከደቦሏ ጋር ምሥለ-ራስ ፎቶ (ሰልፊ) ተነስቶ ፎቶውን ከተሠራጨ በኋላ ነው።
የኋላ ኋላ ደቦሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ የእንስሳት ማቆያ ተወስዷል።
በዚህ ወርም ኔዘርላንዳዊ መንገደኛ አንድ ደቦል በመንገድ ላይ ተጥሎ አግኝቷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials