Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, January 24, 2020

ሩዋንዳ የወባ ትንኞችን ለመግደል 'ድሮኖችን' አሰማራች


ሩዋንዳ
Image copyrightGETTY IMAGES
የሩዋንዳ መንግሥት የወባ ትንኞች በመራቢያ አከባቢያቸው ለመግደል ድሮኖችን በመጠቀም ጸረ-ወባ ኬሚካል ርጭት ማካሄድ ጀመረ።
የሩዋንዳ ባዮሜዲካል ማዕከል ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ድሮኖች 10 ሊተር ጸረ-ተባይ ኬሚካሎችን ይዘው በመነሳት የወባ ትንኞች ያስወግዳሉ።
ቤት ለቤት የኬሚካል ርጭትን እንዲሁም አጎበርን በመጠቀም የወባ ትንኞችን የመከላከል ጥረትን ድሮኖቹ እንደሚያግዙ ኃላፊው አኢምብሌ አምቢቱዩሙሬመይ ተናግረዋል።
"አሁን ፍላጎታችን የወባ ትንኞቹን ከምንጫቸው ማስወገድ ነው። ድሮኖቹ በመጀመሪያ የእድገት ደረጃ ላይ ያሉ የወባ ትንኞችን የሚገድል ኬሚካል ነው የሚረጩት" ብለዋል።
ሰው አልባ በራሪዎቹ የሚረጩት ኬሚካል በሰው እና በአከባቢ ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት እንደማይኖር ተነግሯል።
የሩዋንዳ ባዮሜዲካል ማዕከል አሃዝ እንደሚጠቁመው በፈረንጆቹ 2018 እና 2019 መካከል 3.9 ሚሊዮን ሩዋንዳውያን በወባ በሽታ ተይዘዋል።
ይህ አሃዝ ግን 2017 ከነበረው በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር፤ ዝቅተኛ ነው።
እአአ 2017 ላይ 4.8 ሚሊዮን ሩዋንዳውያን በወባ በሽታ ተይዘው ነበር።
ሩዋንዳ ከዚህ ቀደም ድሮኖችን በመጠቀም በገጠራማ አከባቢዎች ለሚገኙ ክሊኒኮች ደም እና መድሃኒቶችን ያቀርባሉ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials