Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 28, 2020

የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን፤ የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጩኸት፤ የመንግሥት ዝምታ


የተጋች ቤተሰብ
ከሚማሩበት የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቀ ወጣቶች የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምላሽ አላገኘም።
ተማሪዎቹ ከታገቱ 50 ቀናት አልፏቸዋል። ወላጆች ልጆቻቸው መታገታቸውን ከሰሙ አንስቶ ለሚመለከታቸው አካላት ልጆቻቸውን እንዲመለሱላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጠም።
የተማሪዎችን መታገት ተከትሎ ከቀናት በፊት ወደ አዲስ ዘመን ያቀናው የቢቢሲ ዘጋቢ ከተማዋ ሃዘን እንዳጠላባት ይናገራል።
የታጋች ቤተሰቦች ፊታቸው ጠቁሮ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው ነው ያገኘኋቸው የሚለው ዘጋቢያችን ቤተሰቦችን ማነጋገር እጅግ አሳዛኝ እንደነበር ያስረዳል።
መሪጌታ የኔነህ አዱኛ
አጭር የምስል መግለጫመሪጌታ የኔነህ አዱኛ
መሪጌታ የኔነህ አዱኛ የተማሪ ግርማሽ የኔነህ አባት ናቸው።
መሪጌታ የኔነህ ''በጥር 2 ተለቀዋል ስንባል ደስ ብሎን ነበር፤ ነገር ግን እስካሁን ከልጆቻችን ጋር አልተገናኘንም። መንግሥትም ያለን ነገር የለም። ገድለውብን ይሆናል ብለን እየፈራን ነው። በዚያ ላይ ልጆቹ አይተውት የማያውቁትን ነገር ሲያዩ ይደነግጣሉ ብለን እናስባለን። ሞተውም ከሆነ እውነቱን ነግረውን ቤተሰብ ጋር ተሰባስበን አልቅሰን እርማችንን ብናወጣ ይሻለናል፤ እንዲህ በየቀኑ ምን ሆነው ይሆን እያልን በሰቆቃ ከምንኖር" ይላሉ።
መሪጌታ እንደሚሉት የልጃቻቸው መታገት በቤተሰባቸው ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ማሳደሩን ይናገራሉ። "ባለቤቴ ጨንቅላቷ ተጨንቆ ጸበል ወስጄ ነው ያከረምኳት" በማለት ይናገራሉ።
ወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ
ወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ
አጭር የምስል መግለጫወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ
ወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ ናቸው።
ወ/ሮ ማሬ የእጅ ስልክ ስለሌላቸው በላይነሽን በስልክ ካገኙ ሰነባባተዋል። "ስልክ ስለሌለኝ የሆነው ሁሉ የምሰማው ከሰው ነው" ይላሉ።
''እህል አልበላ። ሌተ ተቀነ አይ ጉድ እያልኩ ነው። እግዜር ቢሰማን፤ መንግሥትም ቢራራልን፣ ልጆቻችን ቢሰዱልን እያልን ነው . . . አሳድጌ አሳድጌ ልጅ የለኝም ማለት ነው?" ሲሉም መልሰው ይጠይቃሉ።
ተማሪዎቹን መንግሥት እንዳስለቀቃቸው ሲሰሙ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸው እንደነበረ የሚያስታውሱት ወ/ሮ ማሬ፤ "ወሬ ሆኖ ቀረ እንጂ" በማለት ተማሪዎቹ ተለቀዋል ቢባልም ከልጃቸው ጋር ሳይገናኙ እንደቀሩ ያስረዳሉ።
አቶ ሃብቴ እማኙ
አጭር የምስል መግለጫአቶ ሃብቴ እማኙ የተማሪ ግርማ ሃብቴ ወላጅ አባት
አቶ ሃብቴ እማኙ የተማሪ ግርማ ሃብቴ ወላጅ አባት ናቸው።
ልጃቸው ግርማ ከታገተ በሶስተኛው ቀን በአጋቾቹ ስልክ ደውሎላቸው እንደነበረ ያስታውሳሉ። "የነበረበትን አልነገረኝም። ብቻ ደህና ነኝ ነው ያለኝ።"
"ተስፋዬ የነበረው እሱ ነው" የሚሉት አቶ ሃብቴ፤ "እናቱ ቤተ-ክርስቲያን እየተንፏቀቀች እኔም የምሰራው ቅጡ ጠፋኝ። ልጄ የሚያውቀው ነገር የለም፤ የቤት ልጅ ነው። እንኳን የሰው አገር የራሱንም አያውቀው። . . . እናቱም የእሱን ሁኔታ አይታ በቤት ውስጥ የሉትን ልጆች ልትመራልኝ አልቻለችም" ይላሉ።
አቶ ሃብቴ "የማደርገው ጠፋኝ፤ ከፍ ብል ሰማይ ዝቅ ብል መሬት ሆኖብኝ፤ የእሱን መከራ ሳላይ ብሞት አይነደኝም ነበር" ይላሉ።
Presentational grey line
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው ከታገቱ ተማሪዎች ወላጆች መካከል የተወሰኑትን አነጋግሬአለሁ ይላሉ። ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ፤ እንደ አገር ተማሪዎችን ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት አናሳ በመሆኑ ፈጥኖ መፍትሔ ማግኘት አልቻለም ባይ ናቸው።
«በተለይም አካባቢውን የሚያስተዳድረው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና የፌዴራሉ መንግሥት ትኩረት መስጠትና ተማሪዎችን ማስለቀቅ አለባቸው» በማለት ለክልሉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

የማሕበራዊ ሚድያ ጩኸት

የተማሪዎች መታገት ከተሰማ ወዲህ ጀምሮ በማሕበራዊ ሚድያዎች በተለይም በፌስቡክና ትዊተር አለፍ ገደም ያሉ ዘመቻዎች መካሄድ ጀምረው ነበር። ከጥቂት ቀናት በፊት ጀምሮ ግን የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ጩኸታቸውን በሰፊው ማሰማት ጀምረዋል።
ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችም ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። በተለይ ትዊተር በተሰኘው ማሕበራዊ መድረክ ላይ #Bringourgirlsback #Bringourstudentsback #WhereAreTheStudents? #ተማሪዎችየትገቡ? የተሰኙ ዘመቻዎች በመካሄድ ላይ ናቸው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials