Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 22, 2020

አሜሪካ ነፍሰ ጡር ቪዛ አመልካቾች ለመቆጣጠር አዲስ ሕግ አወጣች



አውሮፕላን በአሜሪካ ሲያርፍImage copyrightGETTY IMAGES
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነፍሰ ጡር ሴቶች ለመውለድ ሲሉ ወደ አሜሪካ እንዳይሄዱ ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ሕግ አወጣ።
'የወሊድ ቱሪዝም' ተብሎ የሚጠራውን እና አሜሪካ ሄዶ ለመውለድ የሚደረግን ጉብኝት ለመከላካል የወጣው ፖሊሲ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።
ሕጉ ነፍሰ ጡር ሴቶች ለሥራ ወይም ለጉብኝት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቪዛ ሲያመለክቱ፤ ወደ አሜሪካ የሚሄዱበት ዋነኛ ምክንያት ለመውለድ አለመሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ይላል።
በአሜሪካ ሕግ መሠረት በአገሪቷ የሚወለዱ ልጆች በቀጥታ የአሜሪካ ዜግነት ያገኛሉ። ይህ ሕግ ግን በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሲተች ቆይቷል
የፕሬዚደንት ትራምፕ አስተዳደር አዲሱ የጉዞ ሕግ የአገሪቷን ብሔራዊ ደህንነትና የሕዝብ ጤና ለመጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግሯል።
ትራምፕ ወደ አገሪቷ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቀነስ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን፤ ቀደም ብሎ "በአሜሪካ ለተወለዱና ለኖሩ የሌላ አገር ዜጎች" ዜግነት እንደሚሰጥ የሚገልፀው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት መሻሻል እንዳለበት ጠይቀዋል።

አዲሱ ሕግ ምን ይላል?

አዲሱ ሕግ 'ቢ' ቪዛ የሚጠይቁ ሁሉንም አመልካቾች ይመለከታል።
የቪዛ ኦፊሰሮች ዋነኛ አላማቸው ለመውለድ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሴቶችን ቪዛ እንዲከለክሉ ይፈቅዳል።
"የወሊድ ቱሪዝም ኢንደስትሪ የዓለም አቀፉን የወንጀል መስፋፋት ጨምሮ ከወንጀል ድርጊቶች ጋር የተያያዘ ነው" ሲልም ሕጉ ያስረዳል።
ከዚህም በተጨማሪ ሕጉ የተሻለ ሕክምና ለማግኘት ሲሉ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሰዎችም ላይ የሚደረገውን ቁጥጥርም ያጠብቃል።
በመሆኑም ቪዛ አመልካቾች የህክምና ወጪያቸውን ለመሸፈን የሚያስችል የገንዘብ ምንጭና አቅም እንዳላቸው፤ እንዲሁም ህክምናውን ከሚሰጣቸው ዶክተር ጋር ቀጠሮ እንዳላቸው ለቪዛ ኦፊሰሩ በማቅረብ ማሳመን ይጠበቅባቸዋል።
የፕሬዚደንቱ ፕረስ ሴክሬታሪ ስቴፋኒ ግሪሻም፤ በመግለጫቸው እንዳሉት "የወሊድ ቱሪዝም ኢንደስትሪው በሆስፒታሎች ወሳኝ ግብዓቶች ላይ ጫና ያሳደረ ሲሆን የወንጀል ድርጊቶችንም አባብሷል ብለዋል።
በመሆኑም ሕጉ ይህንን አገራዊ የሆነ ችግር ለመከላከልና አሜሪካን በዚህ ምክንያት ከሚከሰቱ የብሔራዊ ደህንነት አደጋዎች መጠበቅ እንደሚያስችል ጨምረው ተናግረዋል።

በወሊድ ቱሪዝም ምን ያህል ህፃናት ተወልደዋል?

በየአመቱ ወደ አሜሪካ ከሚያቀኑ ሰዎች ምን ያህል ህፃነት እንደተወለዱ የሚያሳይ የተመዘገበ መረጃ ባይኖርም የተለያዩ አካላት ግን ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።
እንደ የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል መረጃ በአውሮፓዊያኑ 2017 በአሜሪካ ከሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች 10 ሺህ የሚሆኑ ሕፃናት ተወልደዋል። ይህም የቅርብ ጊዜ መረጃ ነው።
ይህ ቁጥር በአውሮፓዊያኑ 2007 ከነበረው 7,800 የህፃናት ቁጥር ጨምሯል።
የስደተኞች ጥናት ማዕከል ደግሞ በ2016 እና 2017 መጀመሪያው አጋማሽ ጊዜያዊ የጉብኝት ቪዛ ካላቸው እናቶች 33 ሺህ ህፃናት መወለዳቸውን ያስረዳል።
አሁን ላይ ነፍሰጡር ሴቶች እስከሚወልዱ ድረስ ለመቆየት ወደ አሜሪካ መግባት እንደሚችሉ የአሜሪካ የጉምሩክና ድንበር ጥበቃ መሥሪያ ቤት አስታውቋል።
ይሁን እንጅ እናቶች ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በመቆየት ለመቅረት ፍላጎት እንዳላቸው ከታመነ ጉዟቸው ሊከለከል ይችላል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials