Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 28, 2020

ስለታገቱት ተማሪዎች የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች በአማራ ክልል፡ ተካሄዱ


በባህር ዳር
አጭር የምስል መግለጫባህር ዳር
ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ የደረሱበት ያልታወቀ የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደህንነት ያሳሰባቸው በተለያዩ የአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ድርጊቱን የሚቃወሙ ሰልፎች አካሄዱ።
በዩኒቨርስቲው ያጋጠመን አለመረጋጋት ሸሽተው ወደ መጡበት ሲመለሱ ባልታወቁ ወገኖች ተይዘው ደብዛቸው የጠፋው ተማሪዎች ጉዳይ ከመገናኛ ብዙሃን ርዕስነት አልፎ ለሰልፎቹ መካሄድ ምክንያት ሆኗል።
በዛሬው ዕለት በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ በተካሄደው የተማሪዎቹን መታገት በሚያወግዘው ሰልፍ ላይ በርካታ ቁጥር ያለው የከተማው ነዋሪ ተሳታፊ ሆኗል። በዚህም ምክንያት የተለያዩ የመንግሥትትና የግል ተቋማት ተዘግተው እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የአማራ ክልል የሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ በክልሉ የተካሄዱት ሰልፎች ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቃቸውን አስታውቋል።
ቢሮው ይህን ይበል እንጂ በባህር ዳር በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የክልሉ ባለስልጣናት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለተገኘው ህዝብ መልዕክት ለማስተላለፍ ሲሞክሩ የተቃውሞ ድምጽ ተሰምቶ ዝግጅቱም መቋረጡን ሪፖርተራችን ከስፍራው ዘግቧል።
ከክቡር ትሪቡን አቅጣጫ ደንጋይ የተወረወረ ሲሆን ከስታዲየም ውጪም የተኩስ ድምጽ ሲሰማ ነበር።
በአሁኑ ሰዓት በባህር ዳር ከተማ በርካታ ጸጥታ አስከባሪዎች ተሰማርተው እንደሚገኙ እና ከተማዋም ወደ የተረጋጋ እንቅስቃሴ መመለሷን ሪፖርተራችን ታዝቧል።
ከባህር ዳር ከተማ ውጪ ደብረማርቆስ፣ ወልዲያ፣ ቆቦ፣ዋድላ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ዱር ቤቴ፣ ዳንግላ፣ ደብረ ብርሃን፣ ፍኖተ ሰላም፣ እና በሬ የተቃውሞ ሰልፎቹ የተካሄዱባቸው ከተሞች ናቸው።
በተቃውሞ ሰልፎቹ የተሳተፉ ሰዎች መንግሥት የታገቱትን ተማሪዎች ጉዳይ ችላ ማለቱንና ተገቢውን መረጃ ባለመስጠቱ ወቀሳ ከማቅረባቸው በተጨማሪ፤ ታጋቾቹ ተለቀዋል ተብሎ የተሰጠው መግለጫን "ሐሰተኛ" በማለት ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።
ድርጊቱን ለማውገዝ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉት ሰዎች መንግሥት ስለታገቱት ተማሪዎች ተገቢውን መረጃ እንዲሰጥ፣ ተማሪዎቹ እንዲለቀቁ፣ መንግሥት በአጋቾች ላይ እርምጃ እንዲወሰድና በጉዳዩ ውስጥ እጃቸው አለበት የሚባሉ አካላትም በሕግ እንዲጠየቁ ጥሪ አቅርበዋል።
ሰልፈኞች በባህር ዳርImage copyrightAMMA
በሁሉም ቦታዎች በተካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች ላይ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩና ለወራት የደረሱበት ያልታወቁት ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ እንዲገለጽ እንዲሁም በቶሎ ተለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ በአጽንኦት ተጠይቋል።
ታግተዋል የተባሉት ተማሪዎች ቁጥር 17 እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ከመካከላቸው 13ቱ ሴቶች መሆናቸው ተጠቅሷል። በዚህም መሰረት ባለፉት ሳምንታት በማሕበራዊ የመገናኛ መድረኮች ላይ "እህቶቻችንን መልሱ" በሚል ርዕስ ዘመቻዎች ሲካሄዱ ቆይተዋል።
ቢቢሲ እስካሁን ባገኘው መረጃ ሰላማዊ ሰልፎቹ በባሕር ዳር፣ በወልዲያ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ብርሃን፣ በዱርቤቴ፣ ፍኖተሰላም፣ በራያ ቆቦ፣ በሸዋ ሮቢት፣ በዳንግላና በሌሎች ቦታዎች ተካሂደዋል።
ሰልፈኞቹ፤ "የታገቱት ተማሪዎች የት አሉ?"፣ "ደብተርና ስክርቢቶ የያዙ ተማሪዎችን ማገት ጀግንነት አይደለም"፣ "ለታገቱ ተማሪዎች መጮህ ፖለቲካ ሳይሆን ሰብዓዊነት ነው"፣ "መንግሥት ተለቀቁ ያላቸው ተማሪዎች የት አሉ?" የሚሉ ጥያቄዎችና መልዕክቶችን ማስተጋባታቸውን የቢቢሲ ዘጋቢ ከስፍራው ገልጿል።
በባህር ዳር በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ 6 የታጋች ተማሪ ወላጆች ተሳታፉ መሆናቸውን ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ አቶ መታገስ ገ/ሚካኤል ለቢቢሲ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials