Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 26, 2020

በባግዳድ የአሜሪካ ኤምባሲ የሮኬት ጥቃት ደረሰበት


በኢራቅ ጸረ አሜሪካ ተቃውሞዎች ሲደረጉ ነበር
Image copyrightREUTERS
አጭር የምስል መግለጫበኢራቅ ጸረ አሜሪካ ተቃውሞዎች ሲደረጉ ነበር
በትንሹ ሦስት ሮኬቶች ተወንጭፈው ባግዳድ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲን ትናንት እሑድ እንደመቱ ተገለጸ።
የመጀመርያው ሮኬት የኤምባሲው ካፍቴሪያ ላይ ሲወድቅ የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ በቅርብ ርቀት ወድቀዋል ይላል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው።
ሮይተርስ በበኩሉ በጥቃቱ በትንሹ ሦስት ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ሲል ዘግቧል። አሜሪካ ኤምባሲዋ ላይ ጥቃት ሲደርስ ይህ በረዥም ዓመታት ውስጥ የመጀመርያው ነው ተብሏል።
እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ባይኖርም አሜሪካ ግን ኢራን የምትደግፈው የኢራቅ ወታደራዊ ክንፍ ነው ድርጊቱን የፈጸመው ብላለች።
የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲል አብዱል መሐዲ ጥቃቱን ያወገዙ ሲሆን እንዲህ አይነት ጥቃቶች ኢራቅን ዳግም ወደ ወታደራዊ አውድማነት ይቀይራታል ብለዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ "የኢራቅ መንግሥት የአሜሪካ ጥቅሞችን በማስጠበቅ ግዴታውን ሊወጣ የግድ ይለዋል" ብሏል።
በቅርብ ጊዜ የአሜሪካ ወታደራዊ ማዕከል ጥቃት ደርሶበት እንደነበር ይታወሳል።
ይህም የሆነውን አሜሪካ ቁጥር አንድ ኢራናዊውን ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒን በሰው አልባ አውሮፕላን ተኩሳ ከገደለችው በኋላ ነው።
በዚያ ጥቃት ከሱለይማኒ ጋር የነበረው ኢራቃዊው የካታቢ ሂዝቦላህ ክንፍ መሪ አብዱ መሐዲ አልሙሐንዲስም ተገድሏል።
እጅግ ተጽእኖ ፈጣሪ የሚባሉት የሺዓው ሼክ ሙቅታድ አልሳድር አሜሪካ አካባቢው ለቃ እንድትወጣ ሰፊ የተቃውሞ ሰልፎች እንዲደረጉ ጥሪ አቅርበው ነበር።
የሳድር ደጋፊዎች ጸረ አሜሪካ ተቃውሞ ማድረግ ከመጀመራቸው በፊት የኢራቅ አስተዳደር ፈርሶ በአዲስ እንዲዋቀር በጎዳና ላይ ነውጥ ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials