Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 16, 2020

ሲሰርቁ የታዩት አምባሳደር ሥልጣን ለቀቁ



አምባሳደሩ መጽሃፍ ሰረቁበት የተባለው የመጽሃፍት መደብርImage copyrightGETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫአምባሳደሩ መጽሃፍ ሰረቁበት የተባለው የመጽሃፍት መደብር
በአርጀንቲና የሜክስኮ አምባሳደር የሆኑት ግለሰብ መጽሃፍ ሲሰርቁ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ከተለቀቀ በኋላ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ።
አምባሳደሩ ከዚህ ቀደምም ከአንድ መደብር ውስጥ እቃ ሲሰርቁ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተቀባብለውታል።
የ77 ዓመቱ ሪካርዶ ቫሌሮ፤ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ፤ የጤና መቃወስ ሥራቸው በአግባቡ ማከናወን እንዳላስቻላቸው ጠቅሰዋል።
ባሳለፍነው ወር በአርጀንቲና ቦነስ አየርስ አንድ መደብር ውስጥ መጽሃፍ ለመስረቅ ጥረት ሲያደርጉ የሚያሳይ ምስል ይፋ ከሆነ በኋላ የሃገራቸው መንግሥት ወደ ሜክሲኮች ጠርቷቸዋል።
በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ መጽሃፉን በያዙት ጋዜጣ ከጠቀለሉ በኋላ ከመደብሩ ለመውጣት ሙከራ አድርገው ነበር።
አምባሳደሩ ሊሰርቁት የነበረው የ10 ዶላር መጽሃፍ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ስለኖረ ጣሊያናዊ ጸሐፊ፣ ወታደር እና ሰላይ የሕይወት ታሪክ የሚዘክር ነበር ተብሏል።

ከዚያ በኋላ በሌላ አጋጣሚ ሪካርዶ ቫሌሮ አየር ማረፊያ ውስጥ ከሚገኝ ሱቅ ውስጥ ቲሸርት ለመስረቅ ሞክረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
ቫሌሮ ከቀረጥ ነጻ በሆነው መደብር ቲሸርቱን ለመስረቅ የሞከሩት የሜክሲኮ መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ቦነስ አየርስ አየር ማረፊያ ሳሉ ነበር።
የሜክሲኮ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የአምባሳደሩን የሥራ መልቀቂያ ተቀብሏል።
"ሪካርዶ መልካም ሰው ነው። የአእምሮ ህክምና እየተከታተለ ነው። በቶሎ እንዲሻለው እመኛለሁ" በማለት የሜክሲኮ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማርሴሎ ኤብራርድ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials