Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, September 17, 2017

የኦሮምያና የሶማሌ ችግር ሶማሊላንድ ላይ ጥቃት አስፈፀመ – ሰሎሞን አባተ(ቪኦኤ)



በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች ወሰኖች ባሉ ወረዳዎች ውስጥ እየተካሄደ ካለው የጥቃት እርምጃዎችና ግጭቶች ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር ተያይዞ ከሰማሌ ክልል የተፈናቀሉ ከአርባ ሺህ እስከ ሃምሣ ሺህ የሚሆኑ የኦሮሞ ተፈናቃዮች ምሥራቅ ሃረርጌ መግባታቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ማምሻውን ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ — በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች ወሰኖች ባሉ ወረዳዎች ውስጥ እየተካሄደ ካለው የጥቃት እርምጃዎችና ግጭቶች ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር ተያይዞ ከሰማሌ ክልል የተፈናቀሉ ከአርባ ሺህ እስከ ሃምሣ ሺህ የሚሆኑ የኦሮሞ ተፈናቃዮች ምሥራቅ ሃረርጌ መግባታቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ማምሻውን ለቪኦኤ ገልፀዋል።በሌላ በኩል ደግሞ ጭናቅሰን ውስጥ ዛሬ በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰው ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚሁ የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ቀውስ ጋር ተያይዞ ጎረቤት ሶማሌላንድ ውስጥ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወት ያጠፋ ጥቃት እየተፈፀመባቸው መሆኑና ከፍተኛ ሥጋት ላይ እንደሚገኙ እየገለፁ ናቸው።

ሃርጌሣ ላይ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተገድለው አንደኛው ላይ ጉዳት እንደደረሰት የሶማሊላንድ የፀጥታ ሚኒስትር ዴኤታ አስታውቀዋል።

ሶማሊያዊያኑ በኢትዮጵያዊያን ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ ጥሪ ያስተላለፉት ሚኒስትር ዴኤታው ሞሐመድ ሙሣ ዴሬ ለኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ጥበቃ እንዲያደርጉ ኃይሎቻቸውን ማዘዛቸውን አመልክተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
  00:14             12:48  


No comments:

Post a Comment

wanted officials