የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አስክሬን ሽኝት ተደረገ።
ህይወታቸው ባለፈበት ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ዛሬ በተካሄደ የሽኝት ፕሮግራም ከተለያዩ የጀርመን ከተሞችና ከሌሎች ሀገራት የመጡ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች መገኘታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል ።
በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በተዘጋጀው የስንብትና የሽኝት ፕሮግራም የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የቅርብ ጓደኞችና አብሮ አደጎች ምስክርነቶችን ሰተዋል።
በሃይማኖታዊ ዝማሬና ጸሎት ሽኝቱ የተከናወነ ሲሆን የተለያዩ እምነት አባቶችም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አስክሬን በነገው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ አስታውቋል።
የቀብር ስነስርዓቱም የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል ።

No comments:
Post a Comment