በአሜሪካ ኔብራስካ ግዛት በእርሻ ሥራ ላይ ሳለ ሰብል መሰብሰቢያ መሣሪያ ውስጥ እግሩ የተቀረቀረበት አርሶ አደር በስለት የራሱን እግር ቆርጦታል።
የ63 ዓመቱ አርሶ አደር ኩርት ካሴር ምርት ለመሰብሰብ የሚረዳውን ማሽን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ እያዘዋወረ ነበር፤ ማሽኑ ልክ እንደ መብሻ (ድሪል) ዓይነት ሲሆን የሚሽከረከርም ነው።ግለሰቡ የግሉ በሆነው 607 ሔክታር መሬት ላይ ብቻውን እየሰራ ሳለ ነበር አደጋው ያጋጠመው። በአቅራቢያው ሰዎች ባለመኖራቸው የሚረዳው አላገኘም። ስልክ በመደወል የሰዎችን እርዳታ ለመጠየቅ ቢያስብም ተንቀሳቃሽ ስልኩን አጠገቡ ሊያገኘው አልቻለም።
ማሽኑ እግሩን እየከረከረ የበለጠ ወደ ውስጥ እየዘለቀና ከፍ እያለ መጣ።
በዚህ ጊዜ ደፋሩ ገበሬ የያዘውን ስለት ሳብ አድርጎ ከማሽኑ የተረፈውንና ከጉልበቱ በታች ያለው የራሱ እግር ላይ እርምጃ ወሰደ።
No comments:
Post a Comment