Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 31, 2019

ይድረስ ለሰብአ ትግራይ | ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም


ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
ታኅሣሥ 2011
1. በመጀመሪያ ራሴን ላስተዋውቅ፡ የተወለድሁት አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ ነው፤ ዘመኑም 1922 ዓ. ም. ነው፤ የአገዛዝ የመንግሥት ለውጥ የተደረገበት ዘመን ነበር፤ አባቴ አቶ ወልደ ማርያም እንዳለ (ከአንኮበር፣ ሸዋ፤) ፣ እናቴ ወይዘሮ ይመኙሻል ዘውዴ (ከየጁ፣ ወሎ፤) ናቸው፤ ሚስቴ የነበረችው በአባትዋ ሸዋ (መርሐቤቴ) በእናትዋ ትግራይ (አድዋ፣ እንትጮ፤) ነች፡፡
በሥራዬ አብዛኛው ዕድሜዬ ያለፈው በአስተማሪነት ነው፤ መጀመሪያ በእቴጌ መነን ትምህርት ቤት፣ በኋላ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ከዚያ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሳስተምር ነበር፤ በአጼ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ በፓርላማ ተመርጬ ለአንድ ዓመት ያህል በመርማሪ ኮሚስዮን ሠርቻለሁ፤ ጡረታ ከወጣሁ በኋላ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤን አቋቁሜ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስለሰብአዊ መብቶች ለማስተማር ሞክሬአለሁ፤ የመጨረሻ ሥራ የምለው በቅንጅት የፖሊቲካ ፓርቲ አባልነት ነው፤ ከዚያ በኋላ በመጻፍና በማሳተም ቆይቻለሁ፤
2. ከትግራይ ጋር የተዋወቅሁት በ1951 ነው፤ ክፉ ዘመን ነበረ፤ ገና ዕድሜዬ ሠላሳ ሳይሞላ በትግራይ የተመለከትሁት ስቃይና መከራ ልቤን ሰንጥቆ የገባ ነበር፤ በአገሬ በኢትዮጵያ፣ በወገኖቼ በኢተትዮጵያውያን ላይ የተጫነውን አገዛዝና ግፈኛነነቱን የተረዳሁበትና ከማናቸውም አገዛዛ ጋር በተቃውሞ ለመቆም የወሰንሁበት ዓመት ነበር፤ ያን ሁኔታ አይቼ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለቀስሁበት ዓመት ነበር፤ በችጋር ለተጠቃው ሰብአ ትግራይ መፍትሔ ልዑል ራስ ሥዩም ለትግራይ አውራጃዎች በሙሉ በየቀኑ ጸሎት እንዲደረግ አዝዘው ነበር፤ አገዛዙ ከጊዜው የዓለም ሁኔታ ጋር መራራቁን የተገነዘብሁበት ዓመት ነበር፤ ሁለት የትምህርት ቤት ጓደኞቼን (ነፍሱን ይማረውና) መንገሻ ገብረ ሕይወትንና ኃይለ ሥላሴ በላይን አግኝቻቸው ያየሁትን አ.ይተዋል፤ በዚያን ጊዜ ትግራይ አገሬ ነበር፤ የሰብአ ትግራይ ስቃይ የኔም ስቃይ ነበር፤ በሰብአ ትግራይ ላይ የደረሰው ችጋር የኢትዮጵያ ነበር፤ ስለዚህ የኔም ችጋር ሆኖ ተሰማኝ፤ በሕይወቴ ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ በመሳፍንትና መኳንንት ቤት እየዞርሁ ደጅ ጠናሁ፤ በዚያን ጊዜ የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩት ደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴ ‹‹እኔን ትግሬ ስለሆነ ነው ይሉኛልና ተወኝ፤›› ብለውኛል፡፡
3. ከሀያ አምስትና ከሠላሳ ዓመታት በኋላ በጉዳዩ ላይ ሁለት መጽሐፎችን (Rural Vulnerability to Famine in Ethiopia: 1958—1977. Suffering Under God s Environment: A Vertical Study of the Predicament of Peasants in North-Central Ethiopia) እስክጽፍ ድረስ ችግሩ ከአእምሮዬም ከልቤም አልወጣም ነበር፤ ትግራይን ከአክሱም ጽዮንና ከያሬድ ለይቼ አላይም፤ ኤርትራን ከደብረ ቢዘንና ከዘርአይ ደረስ ለይቼ አላይም፤ የኔ ኢትዮጵያዊነት የሚፈልቀው ከነዚህ ምንጮች ነው፤አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ወያኔና ሻቢያ እነዚህን ምንጮች ለማደፍረስ ሞክረዋል፤ በተለይ በአለፉት አርባ ዓመታት ኢትዮጵያ በገዛ ልጆችዋ በጣም ደምታለች፤ ጥቂት ልጆችዋ በባዐድ ፍልስፍና ተመርዘው ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ለመመረዝ ተደራጅተው ፍቅርን በጦር መሣሪያ፣ ኢትዮጵያዊነትን በዘር ለውጠው የታሪክ ቅርሳችንን ሊያሳጡን ሞክረው ነበር፡፡
4. የምንጮቹን ጥራት ለመጠበቅ አዲስ ትግል ተጀምሯል፤ በፍቅርና ይቅር ለእግዚአብሄር በመባባል በሰላማዊ መንገድ ኢትዮጵያን ለማደስ አዲስ ትውልድ ተነሥቷል፤ ይህ ትውልድ ድምጽና የፖሊቲካ ኃይል ያገኘው ወያኔ ከሥልጣን ከመገለሉ በኋላ ነው፤ ከሥልጣን (ከአድራጊ-ፈጣሪነት) የወረዱት የወያኔ ባለሥልጣኖች የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው በአለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያውያን (ሰብአ ትግራይን ጨምሮ) ላይ የደረሰውን ግፍ ሰብአ ትግራይ ሰርዘውታል ማለት ነው ወይስ የተፈጸመው ግፍ በጎሣ ሚዛን ታይቶ ተናቀ የሚሰረዝም የሚናቅም አይደለም፤ በዚያው በትግራይ ውስጥ ብዙ ግፍ እንደተፈጸመ የሚመሰክሩ የትግራይ ተወላጆች ሞልተዋል፡፡
5. ግፍንና ግፈኛን ለማውገዝ የግፍ ተቀባዩ ወገን መሆን አስፈላጊ አይደለም፤ አእምሮና ኅሊና ያለው ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው፤ ዛሬ የሰው ልጅ እንኳን ለሰውና ለእንስሳም በጣም የሚቀረቆርበትና ዘብ የሚያቆምበት ጊዜ ደርሰናል፤ ሰብአ ትግራይ እንዴት ከዚህ ውጭ ይሆናሉ በአለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ እንደሚካሄድ ሰብአ ትግራይ አላዩም አልሰሙም ለማለት ይቸግራል፤ በሌላ በኩል በወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ሰብአ ትግራይ በሙሉ ተጠቃሚዎች ነበሩ የሚል ሐሜት አለ፤ ስለዚህም የግፍ አሳላፊዎች እንጂ የግፍ ተቀባዮች አልነበሩም የሚባለው ልክ ነው ልንል ነው፤ በበኩሌ ይህንን የመጨረሻውን አስተያየት ለመቀበል በጣም ያዳግተኛል፤ ለማንኛውም ሰብአ ትግራይ በቅርቡ እውነተኛ መልሱን እንደሚሰጡን እተማመናለሁ፡፤
6. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣኖች ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸው ሳይጠበቅላቸው በአስከፊ ሁኔታ እየተጨፈጨፉ አልቀዋል፤ የደርግ አባሎች በፈጸሙት ግፍ ተከስሰውና ተከራክረው ተፈረደባቸው፤ በምሕረት ወጡ፤ አሁን ደግሞ የወያኔ ባለሥልጣኖች ተራ ሆነ፤ የወያኔ ተራ ሲደረስ ትግሬነታቸው ተነሣ፤ ሁሉም የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው ከተከሰሱበት ወንጀል አንዱ ይመስለኛል፤ ወያኔ የሥልጣን መሰላሉን ለመውጣት ትግሬነትን መሣሪያ አድርጎ እንደተጠቀመበት እውነት ነው፤ አሁን መውረድ ግዴታ ሲሆን የወጡበትን መሰላል መካድ አይቻልም፤ የወያኔ ባለሥልጣኖች ከአለፉት ሁለት አገዛዞች የሚለዩት በወያኔ ዘረኛነት ብቻ ይመስለኛል፤ ስለዚህም ዛሬ ለፍርድ የሚፈለጉት ትግሬዎች በመሆናቸው አይደለም፤ የሚፈለጉት ትግሬነትን የዘረኛነት ሥልጣን መሠረት አድርገው ፈጽመዋል በተባሉት ወንጀሎች ነው፤ ትግሬነት ከወያኔ ወንጀል ውጭ ነው፤ ፍርዱ በሥርዓት ከተካሄደ ከወያኔ ባለሥልጣኖች ጋር በወንጀል ተያይዘው የሚቆሙ የሌሎች ጎሣዎች አባሎች ይኖራሉ፤ የነሱ ድርሻ በፍርድ ካልታየ የዘር አድልዎ ተፈጸመ ለማለት እንችላለን፤ ይህ አድልዎ ሐቅ ቢሆንም የወያኔን ባለሥልኖች ወንጀል ወደትግሬነት አይለውጠውም፤ ስለማይለውጠውም አይሰርዘውም፤ ወንጀለኛነነት ከትግሬነት ተለይቶ ብቻውን ይቆማል፤
7. ሰብአ ትግራይ አክሱም ጽዮንን አቅፎ የወንጀል ምሽግ መሆን አይችልም፤ ሰብአ ትግራይ አክሱም ጽዮን የዕርቅና ይቅር የመባባል መንፈሳዊ ኃይል እንጂ የወንጀለኞች ምሽግ እንደማትሆን ያውቃሉ፤ በኢትዮጵያውያን መሀከል አለመግባባት ሲከሰት በሰላማዊ መንገድ በንግግርና በክርክር፣ በውይይትና በምክክር መፍትሔ ማግኘት ከከፍተኛ ጥፋትና ደም መፋሰስ እንደሚያድን ይታመናል፤ ስለዚህም የሰብአ ትግራይ ምርጫ ከወንጀል ተነጥሎ ከአክሱም ጽዮን ጋር መቆም ነው፡፡

Wednesday, January 30, 2019

ለምግብነት ሊውል የማይችል 55,000 ቶን የተበላሸ ስንዴ የጫነች መርከብ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ነው

ለምግብነት ሊውል የማይችል 55,000 ቶን የተበላሸ ስንዴ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ላይ ቆማ ሶስት ወር ድርድር ከተደረገበት በሁዋላ ስንዴው ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ነው ሲሉ አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ አጋለጡ::
‘አምባሳደሩ በፌስቡክ ገጾች እንዳሰፈሩት “ፕሮሚስንግ በተባለ አቅራቢ ድርጅት አማካይነት የቀረበው ይህ ስንዴ በስብሶ ለምግብነት ሊውል ስለማይችል ወደመጣበት እንዲመለስ የተወሰነ ቢሆንም የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከአስመጭው ድርጅት ጋር ባደረገው ድርድር ስንዴው ታክሞአል በሚል ምክንያት ተጭኖ ወደ ሀገር ቤት እንዲገባ ተደርጎአል።” ያሉት አምባሳደሩ :ስንዴው የበሰበሰው አንሶ መታከሚያ ኬሚካል ተጨምሮበት ሊያስከትለው ስለሚችለው የጤና ጠንቅ የታሰበበት ነገር ይኖር ይሆን?
ታክሞ መግባት የሚችል ከሆነ ከመጀመሪያው ወደ መጣበት እንዲመለስ ለምን ተወሰነ?
የተወሰነው ውሳኔ እንዴት በድርድር ሊሻር ቻለ?” ሲሉ ጥያቄዎቻቸውን አቅርበው “እንደኔ እምነት ድሮ በነበረው አሰራር ውሳኔው ተሽሮ ስንዴው እንዲገባ የተደረገው ጉቦ ተበልቶበት ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። ስለዚህ ለምግብነት በሚውሉ ገቢ ምርቶች ጥራት ላይ መንግስት በቂ ቁጥጥር ማድረግ ይኖርበታል። ፕሮሚስንግ የተባለ የስንዴ አቅራቢ ድርጅት ከ20 ዓመታት በላይ ከጨረታ ውጭ በብቸኝነት ስንዴ አቅራቢ የነበረ ከባለሥልጣኖች ጋር ጥብቅ ትሥሥር የነበረው ድርጅት ነው። ” ብለዋል::
በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ወደ ስቱዲዩ እስከገባንበት ጊዜ  የሰጠውን ምላሽ የለም::

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በተማሪዋች መኖሪያ ክፍሎች ጩቤ፣ ድንጋይ፣ ብረት እና ዱላ ተገኘ



በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በተማሪዋች መኖሪያ ክፍሎች ጩቤ፣ ድንጋይ፣ ብረት እና ዱላ ተገኘ::
ዩኒቨርስቲው ትላንት ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሰጠው የፅሁፍ መግለጫ የሚከተለውን ብሏል፡፡

Monday, January 28, 2019

የወልቃይት የአማራ ማንነት ወሰን አስመላሽ ኮሜቴ ህዝባዊ ስብሰባ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አዲስ አበባ

ለገሠ ወ/ሃና
የወልቃይት የአማራ ማንነት እና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ኮሚቴው ያለፈበትን አድካሚ ጉዞ እና ቀጣይ ለመስራት ያሰበውን የኮሚቴው አባላት አቶ አታላይ ዛፌ ፣ አቶ ጌታቸው አደመ ፣ መቶ አለቃ ደጀኔ ማሩ … በዝርዝር ለተሰብሳቢው አቅርበዋል ።

በመቀጠል የኮሚቴው አማካሪ እና ከወልቃይት ጋር በተያያዘ ታስረው ለነበሩ የኮሚቴው አባላት እና ለሌሎች በነጻ ሳይቀር ጥብቅና የሚቆሙት ጠበቃና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አለልኝ ምህረቱ ወልቃይት እና ሌሎች ከአማራ የተወሰዱ መሬቶችን ከህግ አንጻር ህጋዊ መሠረት የሌለው ንጥቂያ እንደሆነ በሰፊው አቅርበዋል ።
በመቀጠል ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት አቶ ውብሸት ሙላቱ ናቸው::

አቶ ውብሸት በርካታ የታሪክ ድርሳናትን እያጣቀሱ በማንበብ ወልቃይትም ሆነ ሌሎቹ የማንነት ጥያቄ የተነሳባቸው አካባቢዎች የአማራ ህዝብ ርስቶች መሆናቸውን የተወሰዱትም በጉልበት መሆኑን በማስረጃ አስደግፈው ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል ።

አቶ ውብሸት ሀገር ማለት ሰው ሳይሆን ሀገር ማለት መሬት መሆኑን በአሳማኝ አገላለጽ ለተሰብሳቢው አቅርበዋል ።

ከዚህ በመቀጠል የእድሜ ባለፀጋው የወልቃይት ተወላጅ ቀኛዝማች ፍትሃለው ደምሴ ዛሬ 87 ዓመት እድሜ ላይ ሆነው በአስገምጋሚ ድምጻቸው በእሳቸው እድሜ የሚያውቁትንና ከአባቶቻቸው ጀምሮ ከተገዜ ወዲህ ትግሬ ገዝቶም ኖሮም እንደማያውቅ ከተከዜ ወዲህ አይደለም ከተገዜ ማዶም ያለው መሬት በአማራ ጀግኖች ከጠላት ወራሪ ተጠብቆ የቆየ መሆኑና ወልቃይት ጠገዴ የአማራ ርስት መሆኑን አለም ያውቀዋል የዛሬው ውይይት ወልቃይት የአማራ ነው አይደለም ሳይሆን እንዴት ርስታችንን ይመለስ የሚለው ነው ጉዳዩ በማለት በሰፊው ገለጻ አድርገዋል::

ከዚህ በመቀጠል ከመድረክ በቀረበው ሀሳብ ላይ ጥያቄ ካለ እንዲቀርብ በተፈጠረው እድል ከተሰብሳቢው በርካታ ጥያቄዎች ቀርበው የኮሚቴው አባላት ለጥያቄዎቹ ማብራሪያ ሰጥጥተዋል ።

በመጨረሻም በቀድሞው አጠራር ሸዋ ክፍለሀገር በወያኔ አጠራር ሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ የተቋቋመው የአማራ ማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚት በተሰጠው እድል የኮሚቴው አባል አቶ ባሳዝነው ሞገስ ደራ ወረዳ ከዘመነ ወያኔ በፊት በአማራ አስተዳደር ስር እንደነበረ እና ህዝቡም ከ80 በመቶ በላይ አማራ እንደሆነ ገልፀው የደራ ወረዳ አዋሳኝ  በምስራቅ ሚዳ እና መርሃቤቴ፣ በሰሜን ደቡብ ወሎ ወግዲ (ቦረና ሳይንት)፣ በምዕራብ ምስራቅ ጎጃም፣ በደቡብ ጀማወንዝ ይዋሰናል ይህ ሆኖ ባለበት ሁኔታ ወረዳዋ ከ1983 ዓም ወዲህ መለስ አማራ ጠል የሆነ ህገመንግስቱን እንደመሳሪያ ተጠቅሞ ለኦህደድ(ለአባዱላ ) በስጦታ መልክ የሰጣት ትንሿ ወልቃይት የሆነች ነች ብለዋል ።

በጉልበት ወደ ኦሮምያ ክልል የተካለ መሆኑንና በዚህም ምክንያት በርካት በደል ደርሶብናል በቋንቋችን እንዳንማር ተደርገናል ኦሮምኛ ባለመቻላችን ስራ በየትኛውም የመንግስት መዋቅር ውስጥ ስራ አንቀጠርም በስደት ነው ኑሯችንን እየገፋን እንገኛለን ብለዋል አቶ ባሳዝነው በሁሉም አካባቢ የተቋቋመው የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮማቴ ጥያቄዎቻችንን እንዲመለሱ በጋር መስራት አለብን በማለት ጥሪ አቅርበዋል የራያና የመተከል የአማራ ማንነት እና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በጊዜ እጥረት ምክንያት ሀሳባቸውን ማቅረብ ሳይችሉ ቀርተዋል ።

በመጨረሻም ህዝባዊ ስብሰባው ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቋል ።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአቶ ሙስጠፋ ኡመርና የአቶ አህምድ ሽዴ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል::

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ኡመርና የኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አህምድ ሽዴ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል::

ዶ/ር አብይ ከሙስጠፋ ኡመር እና አህመድ ሺዴ ጋር ከስብሰባው በፊት የተነሱትን ፎቶ አድርጎ ባሰራጨው ዘገባው ዉይይቱም የተኮረው በሶማሌ ክልል ልማትና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ሲሄን ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም የክልሉን ልማት የበለጠ በማጠናከር ረገድ አቅጣጫ ሰጥተዋል ሲል ጽህፈት ቤቱ ጠቅሷል::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች በበኩላቸው ስብሰባው እንዳልተጠናቀቀና እስከነገ ድረስ እንደሚቀጥል ገልጸውልናል::  በዚህ ስብሰባ ላይ 11 አባላት ያሉት የሶማሌ ክልል ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን ስብሰባው እንዳለቀ መረጃ እንደሚያቀብሉን ቃል ገብተውልናል:: እንደደረሰን መረጃውን ለዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች እናደርሳለን::

Ethiopia, Eritrea to open four commercial border checkpoints




Ethiopia and Eritrea would soon open four commercial checkpoints to monitor and regulate cross border trade between the two countries, according to the Ethiopian Customs Commission.
The Commission has also prepared a commercial transit protocol, which has been referred to the relevant body at the Ministry of Foreign Affairs, the Ethiopian News Agency quoted Mulugeta Beyene, deputy commissioner as saying.
The commercial transit protocol would soon become a law and would help the regulation of commercial activities and import-export trade between the two countries, according to Mr. Beyene.
Ethiopia and Eritrea reopened their common borders at three fronts after a two decades enmity ended in July 2018 when the two countries signed a peace declaration.
The western border, Humera in Ethiopia and Oum Hajer in Eritrea, was reopened last week in the presence of the leaders of the two countries. Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed and Eritrean President Isaias Afwerki had also presided over the opening of the Zalambessa and Bure fronts in September.
But the Zalambessa front has been closed since last month until customs and other formalities had been completed.
The report said two of the four commercial checkpoints would be on Zalambessa and Rama.
According to a peace declaration signed in July, Ethiopia and Eritrea agreed to resume commerce and transportation, in addition to the resumption of diplomatic relations.

በነአቶ በረከት ስምዖን ላይ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ


በሌብነት ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣቸው፡፡
ጉዳዩ በአዲስ አበባ እንዲታይና ዋስትና እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄም በፍርድ ቤቱ ውድቅ ሆኗል፡፡

አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ በጥረት ኮርፖሬት ውስጥ አመራር በነበሩ ጊዜ በተጠረጠሩበት የሌብነት ወንጀል በባህር ዳር በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
ሁለቱም ተጠርጣሪዎች የጤና ችግርና የቤተሰብን ድጋፍ በቅርበት ለማግኘት በሚል የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩና ጉዳዩ አዲስ አበባ እንዲታይላቸውም ፍርድቤቱን ጠይቀው ነበር።
ተጠርጣሪዎቹ ካለባቸው የጤና ችግር አንጻር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ እንደሚመገቡ ገልጸው፤ ይሁንና በማረፊያ ቤቱ ምግብ በአግባቡ እና በሰዓቱ እንደማይቀርብላቸው ተናግረዋል፡፡
ለአብነትም ትናንት ምሳ በ10፡00 እንደቀረበላቸው ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የሰብአዊ መብት አያያዛቸው እንዲከበርም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባቸው እና ጡረታ በአግባቡ እንደማይወስዱም ነው ተጠርጣሪዎቹ የገለጹት፡፡
በባህር ዳር ቤት እና ዘመድ ስለሌለን ቤተሰቦቻችን ከአዲስ አበባ ተመላልሰው ምግብ ለማብሰልም ሆነ ለማገዘ አይመቻቸውም ነው ያሉት ፡፡
በተጨማሪ በማረፊያ ጣቢያው ዙሪያ የተሰበሰቡ ወጣቶች ‹‹ወንጀለኛ፣ ሌባ እና ነብሰ ገዳይ በማለት ክብራችንን እና ህገ መንግስታዊ መብታችንን የሚነካ ድርጊት ፈጽመውብናል:: በከተማዋ ያለው ድባብ ለደህንነታችን እና ጉዳያችንን በደንብ ተከታትሎ ለመከራከር እክል ይፈጥራል፤ ስለሆነም የክርክሩ ጉዳይ አዲስ አበባ ይታይልን›› ሲሉ ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡
‹‹የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና አመራሮች ወንጀለኛነታችን ሳይረጋገጥ ጉዳዩን በማራገብ የደቦ ፍርድ እንዲደርስብን አድርገዋል›› ብለዋል፡፡
ለአብነትም አቶ በረከት በደብረ ማርቆስ ከተማ በወጣቱ የደረሰውን ሁከት እና ግርግር አንስተዋል፡፡
የክልሉ ስነምግባርና ጸረ ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ‹‹ተመዘበረ›› ካለው የሃብት መጠን ከፍተኛነት አንጻር ዋስትና እንዳይሰጣቸውና እንዲሁም የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በአማራ ክልል በመሆኑ ጉዳያቸው በባህር ዳር እንዲታይ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
ምስክሮችን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ስለሚያቀርብም የጉዳዩን በባሕር ዳር መታዬት ተገቢነት ለፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ የዋስትና መብታቸውን ከልክሎ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ በመስጠት በጥብቅ ጥበቃ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ወስኗል፡፡
የተጠረጠሩበት ወንጀል ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ዋስትና የከለከለው ፍርድ ቤቱ የተመዘበረው ሃብት በአማራ ክልል ስለሆነ ጉዳዩ መታዬት ያለበት በባሕር ዳር ነው ሲል መወሰኑም ታውቋል፡፡
በጥብቅ ጥበቃ እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ የወሰነው ከነበራቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት አንጻር መሆኑንም ችሎቱ አስታውቋል፡፡
አቃቤ ሕግም የተጠረጠሩበትን ጉዳይ አጠናክሮ በ14 ቀናት እንዲያቅረብም ፍርድቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ችሎቱ ውሎውን አጠናቋል፡፡

በኢትዮጵያና ሶማሊያ ድንበር የተሻገረ የታጠቀ የውጭ ሃይል ጥቃት ከፍቶ 22 ኢትዮጵያውያንን ገደለ።



የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያ የድንበር ከተማ ገሃንዳሌ ላይ በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት 50 ሰዎች ቆስለዋል።

ትላንት ጠዋት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ወረራ በፈጸመው የውጭ ሃይል ከተገደሉትና ከቆሰሉት በተጨማሪ የገሃንዳሌ ነዋሪዎች አካባቢውን ጥለው መሰደዳቸው ታውቋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአቅራቢያው ቢኖርም ዜጎችን ከጥቃት መከላከል እንዳልቻለ ግን ተገልጿል።
እንደወትሮው የጎሳ ግጭት አይደለም። በኢትዮጵያውያን መካከል የተደረገም አይደለም።
ድንበር በተሻገረ በዘመናዊ መሳሪያና ተሽከርካሪዎች በታጀበ ሃይል የተፈጸመ መጠነ ሰፊ ጥቃት እንጂ።
በኢትዮጵያና በሶማሊያ የድንበር አካባቢ ወሰን ተሻጋሪ ግጭቶች እምባዛም ተከስተው እንደማያውቁ የሚገልጹት የኢሳት ምንጮች ከአንድ ሳምንት ወዲህ ግን የኢትዮያን ድንበር ተሻግረው ጥቃት ለመፈጸም የተዘጋጁ ሃይሎች መኖራቸው መረጃው ነበር።
ርምጃ ባለመወሰዱ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ድንበር በተሻገሩ የተደራጁ ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያ ላይ ጥቃት ተሰነዘረ። –በርካቶች ተገደሉ። በርካቶች ቆሰሉ።
ኢትዮጵያን ከሶማሊያ በሚያዋስነው ቀንድ በሚመስለው ክፍል ባለው የዋርዴር ዞን ገላዲ ወረዳ ገሃንዳሌ መንደር ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት ነው።
ከሶማሊያ ተነስተው የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው የገቡት ታጣቂዎች ከባድ መሳሪያ የታጠቁ መሆናቸውን የኢሳት ምንጮች ይገልጻሉ።
በቀላል መሳሪያ አማካኝነት የሚደረግ የጎሳዎች መለስተኛ ግጭት በአካባቢው የተለመደ ቢሆንም የዚህ ሰሞን የሆነው ግን የተለየና ጉዳቱ ከባድ ነበርም ይላሉ።
በበርካታ ተሸከርካሪዎች የተጫኑ በመቶዎች የሚቆጠሩት ታጣቂዎች የገሃንዳሌን መንደር በመውረር ለዘጠኝ ሰዓታት የዘለቀ ጥቃት ሰንዝረዋል።
22 ኢትዮጵያውያንን በመግደልና 50ዎቹን በማቁሰል ምሽት ከመምጣቱ በፊት አካባቢውን ለቀው ተመልሰው ወደ ሶማሊያ መግባታቸውን ነው ለማወቅ የተቻለው።
የውጭ ሃይል ድንበር አቋርጦ ጥቃት ፈጽሞ ኢትዮጵያውያንን ገድሎና አቁስሎ ሲወጣ የሚከላከል ሃይል አልነበረም።
የመከላከያ ሰራዊት በዋርዴር ዞን የሰፈረ ቢሆንም ርምጃ መውሰድ አለመቻሉን የገለጹት የኢሳት ምንጮች ቁጥሩ አነስተኛ ቢሆንም የተሰወነ ሃይል በገላዲ ወረዳ ገሃንዳሌ መንደር አቅራቢያ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
መከላከያ ሰራዊት የውጭ ሃይል ድንበር ተሻግሮ ጥቃት ሲፈጽም መከላከል ያልቻለበት ምክንያትን ለማወቅ ምንጮች ያደረጉት ጥረት አልተሳካም።
ጥቃት ፈጻሚዎቹ በተደጋጋሚ በገሃንዳሌ አካባቢ ያሉ ቦታዎች ይገባኛል የሚል ጥያቄ ያነሱ እንደነበር ታውቋል።
የመሬት መገፋፋት ለዘመናት የነበረ መሆኑን የሚገልጹት የኢሳት ምንጮች በዚህ መልኩ ጥቃት ተፈጽሞ እንደማያውቅም ይገልጻሉ።
ለአንድ ሳምንት ያህል ዝግጅት ሲደረግ መረጃው በክልሉ መንግስት እንደነበርም ታውቋል።
የተደራጁት የውጭ ሃይሎች ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸው እየታወቀ አስቀድሞ የመከላከል ርምጃ ያልተወሰደበት ምክንያንት ግራ የሚያጋባ ሆኗል።
የሶማሌ ክልል መንግስት ጉዳዩን በመመርመር ላይ እንዳለ የተገለጸ ሲሆን ከሰሞኑ መግለጫ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በጥቃቱ የቆሰሉት 50 ዜጎች በዋርዴርና በጂጂጋ ህክምና ላይ እንደሚገኙም ታውቋል።
ለጊዜው ወደ መነሻ ቦታቸው የተመለሱት የውጭ ሃይሎች ዳግም ይመጣሉ በሚል ስጋት የገሃንዳሌ ነዋሪዎች አካባቢውን በመልቀቅ በአቅራቢያ ወዳሉ ወረዳዎች መፈናቀላቸውንም ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

ከከምባታ ጠምባሮ ወደ ከፋ ዞን በገቡ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ

ከከምባታ ጠምባሮ ወደ ከፋ ዞን ከ15ዓመታት በፊት በሰፈራ የገቡ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ። ከመስከረም ወር ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ሲፈጸም የነበረው ጥቃት ተጠናክሮ ባለፈው ሳምንት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል።
ፋይል
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ታከለ ነጫ ለኢሳት እንደገለጹት በጥቃቱ 37 ሰዎች ተገድለዋል። ከ30ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
ለመንግስት ጥሪ ብናደርግም ቶሎ ባለመድረሱ አደጋው ሊከፋ ችሏል ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
ጥቃቱን የፈጸሙትን በተመለከተ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ከ15 ዓመት በፊት ነው። ምርጫ 97 አንድ ዓመት አስቀድሞ ኢህአዴግ የምርጫ ማሸነፊያ አንዱ ስትራቴጂ ያደረገው በብዙ ቁጥር የሰፈራ ፕሮግራም ማከናወን ነበር።
በዘመቻ ያለምንም ቅድመ ዝግጅት የሰፈራ ፕሮግራም ከተካሄደባቸው አካባቢዎች የከፋ ዞን ዋናው እንደነበረ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በተለይም ደረቃማ ከሆኑና በድርቅ ከሚጠቁ የከምባታ ጠምባሮ፣ ሲዳማና ወላይታ አካባቢዎች ከ10ሺ በላይ ሰዎች በሰፈራ ፕሮግራም የታቀፉ ሲሆን ወደ ካፋ ዞን ከ5ሺህ ያላነሱ ሰፋሪዎች ተጓጉዘዋል።
በወቅቱ ለኑሮ የሚመች አንድም የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሳይከናወን የሰፈሩ 2500 የሚሆኑ ከከምባታ ጠምባሮ ዞን የመጡ ነዋሪዎች በተለያዩ ወረርሽኝ በሽታ ተጠቅተው ብዙዎች እንደሞቱ ይነገራል።
የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳዳሪ ዶክተር ታከለ ነጫ ለኢሳት እንደገለጹት ያንን አስቸጋሪ ቦታ ለውጠው ሃብት አፍርተው ልጆች ያሳደጉና ለወግ ማዕረግ ያበቁ የያኔው ሰፋሪዎች የዛሬዎቹ ነባር ነዋሪዎች ህይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል።
ከ2005 ዓም ወዲህ በትንኮሳ የጀመረው ጥቃት ካለፈው መስከረም ወር አንስቶ ማንነትን መነሻ ወዳደረገ ጥቃት ተለውጧል ይላሉ አስተዳዳሪው ዶክተር ታከለ።
ዶክተር ታከለ እንደሚሉት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚህም 37 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ከተገደሉት መካከል በርካታ ህጻናት ይገኙበታል።
ጥቃቱ በስለትና በጥይት መሆኑን የሚጠቅሱት ተጎጂዎች የካፋ ዞን አስተዳደር ሊደርስልን አልቻለም ሲሉ በምሬት ይገልጻሉ።
ዶክተር ታከለ የተጎጂዎቹ ሁኔታ አስደንቃጭ መሆኑን በአካል ተገኝተው ማየታቸውን ይናገራሉ።
ከ30ሺህ በላይ የሚሆኑት በትምህርት ቤቶችና በአንዳንድ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙም ታውቋል።
ጉዳዩን በተመለከተ መንግስት አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስድ ተደጋጋሚ ጥሪ መደረጉን የሚገልጹት የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳዳሪ ዶክተር ታከለ ነጫ ምላሽ በመዘግይቱ ጉዳቱ ሊከፋ ችሏል ብለዋል።
ከዘገየም ቢሆን መከላከያ ሰራዊት መግባቱን ነው ዶክተር ታከለ የሚገልጹት።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የከምባታ ልማት ማህበር በደቡብ አፍሪካ ከካፋ ዞን ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ማድረጉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ማህበሩ በደቡቡ አፍሪካ ነዋሪ የሆኑ የአካባቢው ተወላጆችንንና ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጋበዝ የገንዘብ መዋጮ አድርጓል።
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር በተገኙበት በተካሄደው በዚሁ ስነስርዓት ኢትዮጵያውያኑ በከምባታ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ግድያና መፈናቀል አውግዘዋል።

ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡና ከሃገር እንዳይወጡ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ቁጥር 7 ሺ ያህል ነው ተባለ

ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡና ከሃገር እንዳይወጡ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ቁጥር 7 ሺ ያህል ነው ተባለ

    በቀደሞው የደህንነት ሃላፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ የስልጣን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡና ከሃገር እንዳይወጡ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ቁጥር 7 ሺ ያህል እንደነበር ተገለጸ።
          የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንደገለጹት እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ላይ ማጣራት እየተካሄደና ርምጃም እየተወሰደ መሆኑም ታውቋል።

          በዚህም በሶስት ሺ ዜጎች ላይ የተጣለው እገዳ መነሳቱ ተመልክቷል።
          ከሀገር መውጣትና ወደ ሀገር መግባት እንዳይችሉ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ቁጥር ሰባት ሺ እንደነበር ታውቋል።
ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ከ3ሺህ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያይውያን ላይ የተጣለው እገዳ ተጣርቶ እንዲነሳ መደረጉን ነው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ይፋ ያደረገው።
እገዳው ተጥሎ የነበረው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደነበርም ተገልጿል።
ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮችና የሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባላት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን በጎበኙበት ወቅት በተደረገው ገለጻ ላይ እንደተመለከተው ተቋሙ በፖለቲካ ወገንተኝነት ከህግ ውጭ ዜጎች ወደሀገር ቤት እንዳይገቡና ከሀገርም እንዳይወጡ እገዳ ሲጥል ቆይቷል።
በዚህም 7ሺህ ዜጎች የእገዳው ተጎጂ እንደሆኑ ተገልጿል። ተቋሙ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ድብቅ ሆኖ መቆየቱም ነው የተመለከተው።
           የፓርላማ አባላቱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤትን በጎበኙበት ወቅት ዋና ሃላፊው ጄኔራል አደም መሃመድ እንደገለጹት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት የሚስጥር መስሪያ ቤትነቱ የሐገር እንጂ የፓርቲ ወይንም የሆነ ቡድን አይደለም።
          በሌላ በኩልም መንግስታዊዎቹ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ባደረገው እንቅስቃሴ 2 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ ሐገራት ገንዘቦችንም በቁጥጥር ስር አውሏል።
          ከ32ሺ በላይ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውንም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊዎች ገልጸዋል።
          ይህ በእንዲህ እንዳለም የአዲስ አበባ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ 88ሺ የአሜሪካን ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ የውጭ ሃገራት ገንዘቦችን በ6 ወራት ውስጥ መያዙን ትላንት ገልጿል።
          2ሺ ያህል ሕገወጥ የጦር መሳሪያ መያዙንም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

Sunday, January 27, 2019

“በቤተክርስቲያን ውስጥ አፈና አለ” – አቡነ መቃርዮስ

ከ22 አመታት የአሜሪካ የስደት ህይወት በኋላ ወደአገራቸው ተመልሰው በገዛ ፈቃዳቸው በቅርቡ አደጋ በደረሰባት የኢትዮጵያ ሱማሌ ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት አቡነ መቃርዮስ ህዝቡ የተጎዱትን የጅግጅጋ አብያተ ክርስቲያናት መደገፍ እንዳለበት አሳሰቡ፡፡
ዛሬ ለንባብ ከበቃው ኢትዮጲስ ጋዜጣ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት አቡኑ ሲናገሩ በጅግጅጋ ለተቃጠሉት ቤተክርስቲያናት መልሶ ማቋቋሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊረባረብ እንደሚገባ ያሳሰቡት እስካሁን በአብዛኛው እየተረባረበ ያለው በውጭ አገር ያለው ምእመናን በመሆኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አሁን ስላለው ሁኔታ የተጠየቁት አቡነ መቃርዮስ ሲመልሱ ‹‹በቤተክርስቲያን ውስጥ አፈና አለ፡፡ ከስራ አባርርሀለሁ፣ ይህን አደርግሀለሁ የሚል ፉከራ ስላለ ቤተክርስቲያኗ መያዝ የሚገባትን በተለይ ወጣቱን መያዝ አልቻለችም፡፡›› ብለዋል፡፡
ጨምረውም ‹‹አማኙ ህዝብና የሀይማኖት አባቶች ተራርቀውና ተለያይተው ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንጋፋ ሀዋሪያት ቤተክርስቲያን ብትሆንም በአስተዳደሯ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ መንግስትን በመገሰፅ ቀዳሚ መሆን ሲገባት ራሷ ተመካሪ ሆናለች፡፡ ከዚህ አዘቅት በአስቸኳይ መውጣት አለባት›› በማለት አስረድተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በጅጅጋ በእሳት ከተቃጠሉት 10 አቢያተ ክርስቲያናት አንዷ የነበረችዉ የቀብ ዲሀር ማርያም እድሳቷ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል

Ethiopia: Spy agency expunges list of 3,000 people hitherto not allowed to leave or enter country


NISS headquarters, Addis Ababa
by Engidu Woldie
ESAT News (January 17, 2019)
Of the total 7,000 people blacklisted by former spy chiefs with the National Intelligence and Security Services (NISS), 3,000 of them have been expunged from the list by new bosses at Ethiopia’s spy agency.
Those in the list were not allowed to leave or enter the country, and would face arrest and imprisonment if they do so. The ban and the blacklist was done without the order and warrant of courts.
New bosses at NISS briefed members of the Foreign Affairs and Peace Committee with the House of Peoples Representatives today during a visit to the headquarters of the spy agency by members of the committee.
It was revealed that the blacklist was a politically motivated vengeance by former bosses at the spy agency against citizens who are politically active, dissenters and exiled activists and journalists.
The list was put together during the reign of Getachew Assefa, the former spy chief who is now a fugitive hiding in Tigray evading a court warrant.
Getachew Assefa has headed the security and intelligence arm of the TPLF controlled government until his removal by the government of Abiy Ahmed in June 2018.
He has been implicated in the disappearance, torture, imprisonment and extrajudicial killings of dissidents.
In August 2018, an Ethiopian court had issued an arrest warrant on the former spy chief. But he has been hiding in Tigray since he was removed from office. The regional government of Tigray refused orders by federal authorities to hand over the fugitive.
The blacklist that was put together by intelligence operatives of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), headed by Getachew Assefa. The group was in control of the agency for 27 years, until the government of Abiy Ahmed made changes at the leadership of agency while also making it transparent and accountable.
The new head of NISS, General Adem Mohammed told the Parliamentarians that the agency would no more be a political tool for one party but would work for the security of the people.

በሱዳን የተጀመረው ተቃውሞ መቀጠሉ ተሰማ


በሱዳን የተጀመረው ተቃውሞ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች መቀጠሉ ተሰማ።
6ኛ ሳምንቱን የያዘው ተቃውሞ እስካሁን በዝምታ ላይ የነበሩ ከተሞችንም መቀላቀሉ ተሰምቷል።

የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ተከትሎ በወሰዱት ርምጃም ሶስት ሰዎች ተገድለዋል።
ከሟቾቹ ውስጥ ሁለቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሆናቸውን ተቃውሞውን የሚያስተባብረው የሃኪሞች ቡድን አስታውቋል።
ከ29 አመታት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የያዙት የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄኔራል አህመድ አልበሽር ከስልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ታህሳስ 19 የተጀመረው ተቃውሞ ሌሎች አካባቢዎችንም በመቀላቀል መቀጠሉ ነው የተሰማው።
በእስካሁኑ ተቃውሞም መንግስት 30 ሰዎች መገደላቸውን ሲገልጽ፣የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ደግሞ የሟቾቹ ቁጥር በመንግስት ከተገለጸው በእጅጉ የላቀ ነው ሲሉ ይሟገታሉ።
የነዳጅና የዳቦ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ በሱዳን የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን በሃገሪቱ ያሉ የሙያ ማህበራት በጋራ እያስተባበሩት መሆኑም ታውቋል።
በሱዳን የተለያዩ ከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አደባባይ እየወጡ የአልበሽርን ስንብት እየጠየቁ በሚገኙበት ወቅት ትውልደ ሱዳናዊው ባለጸጋ መሐመድ ኢብራሒም ተቃውሞውን ደግፈው ድምጻቸውን ማሰማታቸው ይታወሳል።
ስልጣንን በሰላም ለሚለቁ የአፍሪካ መሪዎች በአለም ላይ ከፍተኛውን ሽልማት የሚሰጡት ባለጸጋው ዶክተር መሐመድ ኢብራሒም አልበሽር ስልጣናቸውን በሰላም ከለቀቁ በአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የተቆረጠው የእስር ማዘዣ እንዲቀርላቸው መጠየቃቸውም አይዘነጋም።

አቶ አህመድ ሽዴ ወንጀል ለሰሩ የቀድሞ አመራሮች ከለላ ሲሰጡ ነበር ተባለ



የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በሶማሌ ክልል ወንጀል የሰሩ የቀድሞ አመራሮች ለህግ እንዳይቀርቡ ከለላ ሲሰጡ እንደነበር የሶማሌ ክልል መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ መንግስት ፕሬዝዳንት የሚዲያ አማካሪ አቶ አብዱላሂ ሁሴን ለኢሳት እንደገለጹት በአቃቤ ህግ የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸውን አመራሮችን ጭምር በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገውን እንቅስቃሴ ያስቆሙት አቶ አህመድ ሽዴ ናቸው።

በሌላ በኩል በአቶ አህመድ ሽዴ እህት ኩባንያ ስም ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የሚያሳይ ሰነድ ወጥቷል።
በሰነዱ እንደተመለከተው በሁለት ዙር ክፍያው የተፈጸመ በድምሩ የ52 ሚሊየን ብር ኮንትራት ከሶማሌ ክልል የመስኖ ቢሮ ጋር ስምምነት ተደርሷል።
ስራው ሳይጠናቀቅ ገንዘቡ ሙሉ በሙሉ መከፈሉን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የሚዲያ አማካሪ እንደሚሉት ሰሞኑን ሁከትና ብጥብጥን አስታከው ወደ ስልጣን ዳግም ለመምጣት የሞከሩት የቀድሞ አመራሮችን በህግ ለመጠየቅ ተደጋጋሚ ሙከራ ተደርጓል።
እነዚህ ግለሰቦች በሰሯቸው ወንጀሎች ተጠርጥረው በጠቅላይ አቃቤ ህግ ሳይቀር የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው እንደነበር የሚገልጹት የሚዲያ አማካሪው አቶ አብዱላሂ ሁሴን ህጋዊ ርምጃውን ሲገድቡት የነበሩት አቶ አህመድ ሽዴ ናቸው ብለዋል።
ለክልሉ የጸጥታ ቢሮ ሃላፊ በመደወል ጭምር ለተጠርጣሪዎቹ ከለላ ሲሰጡ ቆይተዋል ሲሉም ገልጸዋል።
በአቶ አህመድ ሽዴ ከለላ ሲሰጧቸው ከነበሩት አመራሮችና ወደ ውጭ ሃገራት ከሸሹት ጋር በመሆን ክልሉን የማተራመስ ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረጋቸውን የገለጹት አቶ አብዱላሂ የህግ የበላይነትን በማስከበር ክልሉን ለማረጋጋት በተደረገው እንቅስቃሴ የአቶ አህመድ ሸዴ ሚና አሉታዊ ነበር ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በአቶ አህመድ ሸዴ እህት በወይዘሮ ካድራ ሸዴ ስም የሚንቀሳቀሰው ተቋራጭ ኩባንያ ከክልሉ መስኖ ልማት ቢሮ ጋር ተፈራርሞ ያላስረከበው የ52 ሚሊየን ብር ኮንትራት መኖሩ ተጋልጧል።
ኢሳት ያገኘው ሰነድ ላይ እንደተመለከተው በሁለት ዙር ክፍያ የወይዘሮ ካድራ ድርጅት ለሆነው ዋርሳሜ ጠቅላላ ተቋራጭ ኩባንያ ሙሉ ገንዘብ ወጪ ተደርጓል።
ስራው ሳይጠናቀቅ ገንዘቡ ወጪ ተደርጎ እንዲከፈል የአቶ አህመድ ሽዴ እጅ እንዳለበት ነው የኢሳት ምንጮች የገለጹት።
ወይዘሮ ካድራ ሽዴ የክልሉ ጤና ቢሮ ሰራተኛ ሲሆኑ በየወሩ የመንግስት ደሞዝ እንደሚከፈላቸውም ታውቋል።
ይህንን በተመለከተ ምርመራ ስለመጀመሩ የክልሉ ፕሬዝዳንት የሚዲያ አማካሪ ማረጋጋጫ ባይሰጡም ጉዳዩ እንደሚታወቅ ግን ለኢሳት ገልጸዋል።
አቶ አህመድ ሽዴ በሶማሌ ክልል መንግስት በኩል የሚቀርብባቸው ክስ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ዛሬ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ሊሳካልን አልቻለም።

Saturday, January 26, 2019

መከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብሱን ሊቀይር ነው

መከላከያ ሰራዊት የመለያ ደንብ ልብስ በመልበስ በሰራዊቱ ስም ወንጀል የሚፈፅሙ አካላትን ለመቆጣጠር የአባላቱን የመለያ ደንብ ልብስ የቀለምና የዲዛይን ለውጥ ሊያደርግ ነው፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጀር ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል ለመንግስት ሚዲያዎች ዛሬ እንደተናገሩት ደረጃውን የጠበቀ የደንብ ልብስ ለመለወጥ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ፋውንዴሽኑ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለሰራዊቱ አልባሳትና ሌሎች ወታደራዊ ግብዓቶችን አምርቶ ወይም ገዝቶ የሚያቀርብ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ የሚለወጠው የደንብ ልብስ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚወዱት፣ በጥራት፣ በቀለምና በዲዛይን የተሻለ የመለያ ልብስ እንዲሆን ከተለያዩ አገሮች ተመክሮ መወሰዱን ገልጸዋል። የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ሃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ተሾመ ገመቹ በበኩላቸው የመከላከያ ሰራዊቱን አልባሳት መልበስ የሚችለው የሰራዊቱ አባል ብቻ መሆኑን ጠቁመው ይሁንና ተገቢ ቁጥጥር ባለመደረጉ የማይመለከታቸው ግለሰቦች ሲለብሱት መታየቱን ጠቁመዋል፡፡ አዳዲስ አልባሳት በሚቀርቡበት ወቅት አሮጌዎቹ በአግባቡ ሳይወገዱ በመቅረታቸው ልብሱ በማይመለከታቸው አካላት እጅ እየገባ የሰራዊቱን ስምና ክብር የሚያጎድፉ የተለያዩ ወንጀሎች እየተፈጸሙበት መሆኑን ገልጸዋል። የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈጽሙ አካላት ካሉ በወንጀል እንደሚጠየቁ ተናግረዋል።

በአፋርና ኢሳዎች መካከል ዕርቅ ለማውረድ የሰላም ውይይት ተካሄደ


 በአፋርና ኢሳዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማስቆምና ዕርቅ ለማውረድ በአዲስ አበባ የሰላም ውይይት መካሄዱ ተገለጸ።
በሰላም ሚኒስቴር አማካኝነት የተካሄደው ውይይት ላይ የሁለቱም ወገኖች የሃገር ሽማግሌዎች መገኘታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

ሽማግሌዎቹ በሰላም ችግሩን ለመፍታት መስማማታቸውም ተገልጿል።
የሰላም ውይይቱ ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት እንዳይሆን ስጋታቸውን የሚገልጹ ወገኖች መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።
በሁለቱ ወገኖች መካከል በተፈጠረው ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ነው።
በአፋርና በኢሳ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት በሁለቱም ወገኖች ያሉ የሃይምናኦት መሪዎችና የሃገር ሽማግሌዎች ከሰላም ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ ውይይት ማስረጋቸው ተሰምቷል።
ከውይይቱም በኋላ በሁልቱ ወገኖች መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት ከስምምነት መድረሳቸውን ነው የደረሰን መረጃ የሚያመለክተው።
በውይይቱ ላይ የሁለቱ ወገኖች የሃይማኖት አባቶች፣የሃገር ሽማግሌዎች፣የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታና የሃገር ሽማግሌዎች መገኘታቸው ታውቋል።
በስምምነቱ መሰረትም የግጭቱን መንስኤ ለማጣራትና ግጭቱ ዳግም እንዳይከሰት ያደርጋል የተባለ የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙም ታውቋል።
ከስምምነቱ ባሻገርም የሃይማኖት አባቶቹና  የሀገር ሽማግሌዎቹ ወደ ህብረተሰቡ ወርደው ሰላም ማምጣት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንዲሰሩም ተጠይቋል።
ጉዳዩ ይመለከታናል የሚሉ ሌሎች ወገኖች ግን ስምምነቱን በመረጃ ላይ ያልተመረኮዘና ህዝብ ምንም አይነት እምነት እንዳይኖረው ያደረገ ስምምነት ነው ሲሉ አጣጥለውታል።
ለዚህም ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት የሰላም ስምምነት ሊያደርጉ የተቀመጡ ወገኖች በመጀመሪያ ስለግጭቱ ትክክለኛ መረጃ የሌላቸው ናቸው።
ከስምምነቱ በኋላም ለህዝብ ይፋ የሆነው መረጃ ግጭቱ የተፈጠረው በሶማሌና በአፋር ክልል አዋሳኝ መካከል አስመስሎና ስምን ቀይሮ ማቅረብ በራሱ ለጉዳዩ ምንም አይነት ትኩረት አለመሰጠቱን ያሳያል ሲሉም ይወቅሳሉ።
በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ሁኔታ አሁንም አረገበም ይላሉ።
በአፋርና በኢሳ ጎሳዎች መካከል ያለው ግጭት የቆየና ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነው።ይህ መሆኑ ደግሞ ማንኛውም አካል በግልጽ ወቶ ትክክለኛውን መግለጫ እንዳይሰጥ አድርጎታል ሲሉም ይናገራሉ ኢሳት ያነጋገራቸውና የአፋርን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉ አካላት።
አሁንም በሰላም ሚኒስቴር አማካኝነት ውይይት ስለማደረጋቸው ከመገናኛ ብዙሃን ከመዘገባቸው የዘለለ መረጃ የሰጠ አካል የለም ይላሉ።
መንገዶች ተከፍተዋል የሚለው መረጃም ቢሆን ለተሽከርካሪ ክፍት መሆኑን እንጂ ያለውን እውነታ የሚያሳይ አይደለም።
ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የአካባቢው ተወላጆች ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ በሰላም መንቀሳቀስ የማይችሉ መሆኑን በማሳያነት ያቀርባሉ።
ለኢሳት አስተያየታቸውን የሰጡት አካላት እውነተኛ የሰላም ስምምነት ከሆነ መጀመሪያ የግጭቱ መንስኤ ከስር መሰረቱ መጣራት አለበት ባይ ናቸው።
ትክክለኛውን መረጃ ሳይዙ የሰላም ስምምነት ላይ ደርሰናል ማለት ህዝብን ማታለል ነው ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

Thursday, January 24, 2019

Dozens killed in ethnic attack in Kaffa zone as over 30,000 people displaced




At least 37 people, including children, have been killed in southwestern Ethiopia in what a zonal administrator said was an attack against the people of Kembata and Tembaro, who settled in Keffa zone to escape from drought.
The victims had settled in Kaffa in a government program 15 years ago and have worked hard to prosper themselves and the area they had called home.
The administrator of Kembata and Tembaro, Dr. Takele Necha, told ESAT that the attack was blamed on people who raise livestock in Kaffa. He said arrows and guns were used in the attack.
The crisis began six years ago and since last September, it had become clear that the attack was ethnic motivated and resulted in high number of casualties and displacement. According to the administrator, who said he had personally visited the victims, the last few weeks have been the deadliest.
At least 30,000 people have been displaced since September and are sheltered in schools and government institutions. The displaced makes up between 80 to 90 percent of the Kembata and Tembaro people who called Kaffa home.
The administrator said calls for the government to intervene to stop the deadly attack hasn’t gotten a quick response. Slow response by the government is to blamed for the high number of casualties, he said.
Dr. Necha told ESAT’s Mesay Mekonnen that the defense forces have now been deployed to the area, although too little too late.
“It would be difficult to settle the displaced back to their homes unless peace and normalcy is restored in the area and people feel they would be safe,” the administrator said.

በሶማሌ ክልል ለውጥ ቀልባሾች እያንሰራሩ ነው ተባለ


በሶማሌ ክልል ለውጥ ቀልባሾች እያንሰራሩ መሆናቸው ተገለጸ።
ከቱርክ ኢስታንቡል ጂጂጋ ድረስ የተዘረጋው የቀድሞ ካቢኔ አባላት ኔትወርክ አዲሱን አመራር ለመጣል እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የኢሳት የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

ሰሞኑን  ጅጅጋ ላይ ቦምብ ለማፈንዳት የታቀደውን የክልሉ የጸጥታ ሃይል ማክሸፉም ታውቋል።
ከሀገር የኮበለሉት የቀድሞ ካቢኔ አባላት ክልሉን ለማተራመስ ከፍተኛ ገንዘብ መድበው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።
የፌደራል መንግስቱ በሶማሌ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ትኩረት እንዲሰጠው ተጠይቋል።
የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት በሶማሌ ክልል ለውጡን ለመቀልበስ በተዘጋጁት የቀድሞ የክልል አመራሮች አንጻር የፌደራል መንግስትና የክልሉ አስተዳደር አፋጣኝ ርምጃ ካልወሰዱ ቀውስ ሊከሰት የሚችልበት እድል ሰፊ ነው።
የሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሶህዴፓ መዋቅር በቀድሞ የአብዲ ዒሌ ካቢኔ ሊዋጥ ይችላል የሚለው ስጋት እየተጠናከረ መቷል።
ከፓርቲው ውጭ በሆኑት በአቶ ሙስጠፋ ዑመር የሚመራው የሶማሌ ክልል ባለፉት አራት ወራት ሰላምና መረጋጋቱ የተሻለ ቢሆንም ውስጥ ለውስጥ እየተሰራ ያለው የለውጥ ቅልበሳ ተግባር መጪውን ጊዜ የከፋ ሊያደርገው እንደሚችል ነው የኢሳት ምንጮች የገለጹት።
በቱርክ ኢስታንቡልና በተለያዩ ጎረቤት ሃገራት ኮብልለው ያሉት የአብዲ ዒሌ ካቢኔ አባላት ከያሉበት በኔትወርክ በመገናኘት ዳግም የሶማሌ ክልልን መቆጣጠር ስለሚችሉበት ሁኔታ ሲመክሩ መቆየታቸውም ታውቋል።
የቀድሞ የሶማሌ ልዩ ሃይል ኮማንደር አብዲራህማን ላባጎሌ በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘውንና የተወሰኑ አመራሮች የሚገኙበትን ቡድን በመያዝ ከፍተኛ ገንዘብ ወደ ሶማሌ ክልል በመላክ የአቶ ሙስጠፋ ዑመርን አስተዳደር የማወክ መጠነ ሰፊ ተግባራትን አቅዶ በመስራት ላይ ነው ተብሏል።
የቀድሞ የአብዲ ዒሌ ጠባቂ ሚስትና የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ወይዘሮ ሱአድ ፋራህም ከኢስታንቡል ጂጂጋ በመላለስ ይህንኑ ለማወክና ለመበጥበጥ የተዘጋጀውን ገንዘብ ለሚመለከታቸው አካላት ሲያደርሱ እንደቆዩና ሰሞኑንም ለዚሁ ተግባር ወደ ሃገር ቤት መግባታቸውን ነው የመረጃ ምንጮች የሚገልጹት።
በአጠቃላይ 12 የሚሆኑትና መቀመጫቸውን ኢስታንቡል ቱርክ ያደረጉት የቀድሞ ካቢኔ አመራሮች ሀገር ውስጥ ካሉትና አሁንም በሶህዴፓ መዋቅር ውስጥ ስልጣን ይዘው ከሚገኙት አጋሮቻቸው ጋር ሆነው የአቶ ሙስጠፋ ዑመርን ክልላዊ መንግስት በማፍረስ የቀድሞውን አስተዳደር መልሶ ለመትከል መዘጋጀታቸው ታውቋል።
ለዚህም በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ አቶ ሙስጠፋን  ከስልጣን የማስወገድ እቅድ ተይዞ በመከናወን ላይ መሆኑንም ከምንጮች መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ካለፈው ዓርብ ጀምሮ በጅጅጋና በአንዳንድ ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገንዘብ ሲበተን እንደነበርና በተለይም ከቶጎ ውጫሌ መነሻውን ያደረገው የገንዘብ ምንጭ ሲሰራጭ መቆየቱም ታውቋል።
የጥምቀት በዓልን ለማወክ ብሎም የፈንጂ ጥቃት በመፈጸም ክልሉን ወደ ለየለት ቀውስ ለመክተት እቅድ ተይዞ እንደነበር የገለጹት ምንጮች በክልሉ መንግስት የደህንነትና ጸጥታ ሃይል ሊከሽፍ ችሏል።
ጉዳዩን በተመለከተ የአቶ ሙስጠፋ ዑመር አስተዳደር የለውጥ ቀልባሾችን እንቅስቃሴ በቅርበት የሚከታተል ቢሆንም ተመጣጣኝ ርምጃ እየወሰደ ባለመሆኑ የለውጡ አካሄድ እየደፈረሰ መምጣቱ ተገልጿል።
የፌደራል መንግስቱም ከአቶ አብዲ ዒሌ መታስር በኋላ ለሶማሌ ክልል ጉዳይ ትኩረት አልሰጠውም በሚል ትችት ይቀርብበታል።
አፋጣኝና ተመጣጣኝ የሆነ ርምጃ በእነዚህ ለውጥ ቀልባሾች ላይ ካልተወሰደ የሶማሌ ክልል ወደ ትርምስ ሊገባ ይችላል ሲሉ ምንጮቹ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ የክልሉን አመራሮች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

Tuesday, January 22, 2019

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ከመንፈቅ በፊት ተግባራዊ ያደረገው የምህረት አዋጅ ትናንት ማብቃቱ ተገለጸ።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ከመንፈቅ በፊት ተግባራዊ ያደረገው የምህረት አዋጅ ትናንት ማብቃቱ ተገለጸ። ከ13 ሺ በላይ ሰዎች በዚህ የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ መሆናቸውም ተመልክቷል።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዳስታወቀው ከሀምሌ ወር ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው በዚህ የምህረት አዋጅ በወህኒ የሚገኙ 250 እስረኞች ሲፈቱ በሌሉበት የተፈረደባቸው 430 ዜጎችም የምህረት ሰርተፊኬት ማግኘታቸውን የጠቅላይ አቃቤ ህግ ሃላፊዎች ለመንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
2 ሺ 131 የፌደራል ፖሊስ አባላት እና   6ሺ 655 የመከላከያ ሰራዊት አባላት በምህረት አዋጁ ተተቃሚ መሆናቸውም ተገልጿል።
ምህረት ካገኙት ውስጥ 160 የሚሆኑት በኦንላይን ማመልከቻ አቅርበው ምላሽ ያገኙ መሆናቸውም ተመልክቷል።
በክልል ደረጃ ምህረት ካገኙ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት በአማራ ክልል ሲሆን፣ለ 2 ሺ 923 ሰዎች ምህረት ተደርጓል።
ትግራይ ክልል 144 ፣ደቡብ ክልል 108 ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 94 ኦሮሚያ ክልል 62 እንዲሁም ሀረሪ ክልል 50 ሰዎች በምህረት አዋጅ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።
በምህረት አዋጁ ተጠቃሚ የሆኑት አብዛኛው በፌደራል ደረጃ ያመለከቱ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በ 6 ወራት ውስጥ ምህረት ያገኙት 13 ሺ ዜጎች ናቸው።
ይህ  የምህረት አዋጅ ተጠቃሚዎች  ቁጥር የሶስት ክልሎችንና የመከላከያ ሰራዊት የተወሰኑ  ክፍሎችን እንዳላካተተም መረዳት ተችሏል።
የምህረት አዋጁ በዘር ማጥፋት እንዲሁም በሙስና እና መሰል ወንጀሎች የተከሰሱትን እንደማይመለከት መገለጹ ይታወሳል።
የምህረት ግዜ ገደቡ የተጠናቀቀ ቢሆንም ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖች ካሉ ጉዳዩ ለመንግስት ቀርቦ ውሳኔ እንደሚሰጥበትም የጠቅላይ አቃቤ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ለኢዜአ ገልጸዋል።

አቶ በረከት ስምኦን በቁጥጥር ስር ዋሉ

አቶ በረከት ስምኦን በቁጥጥር ስር ዋሉ። የአማራ ክልል የጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዳስታወቀው አቶ በረከት ስምኦን የታሰሩት በሌብነት ተጠርጥረው ነው።

የብአዴን አመራር አባል  የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳም በተመሳሳይ ሰዓት ከመኖሪያ ቤታቸው መያዛቸውንና ወደ ባህርዳር መወሰዳቸው ታውቋል።
አቶ በረከት ስምኦንን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤታቸውን የከበቡ የአማራ ክልል ፖሊሶች ወደ ባህርዳር  እንደወሰዷቸውም ታውቋል።
ባህርዳር 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ለምርመራ መታሰራቸውንም የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል።
የብአዴን አመራር አባል  የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳም በተመሳሳይ ሰዓት ከመኖሪያ ቤታቸው መያዛቸውንና እንደ አቶ በረከት ወደ ባህርዳር መወሰዳቸውን መረዳት ተችሏል።
አቶ በረከት ስምኦን የፌደራል ፖሊስ እንጂ የአማራ ክልል ፖሊስ ሊይዘኝ አይገባም በማለት ቢያንገራግሩም ፖሊሶቹ ጠንከር ሲሉባቸው ትዕዛዙን ተቀብለው መኪናው ውስጥ መግባታቸውን የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ጥረት ከተባለው የብአዴን ኩባንያ ጋር በተያያዘ በፈጸሙት ምዝበራ ተጠርጥረው መታሰራቸውንም የአማራ ክልል ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር  አቶ ዝግአለ ገበየሁ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
የብአዴን አመራር አባላት የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን  እና አቶ ታደሰ ካሳ ከዚሁ ከተጠረጠሩበት ሌብነት ጋር በተያያዘ በነሐሴ ወር ከፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት  መታገዳቸውም ይታወሳል።
የአቶ በረከትን መታሰር ተከትሎ የባህርዳር ነዋሪዎች በአደባባይ  ደስታቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ፖርቹጋላዊቷ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ወ/ሮ አና ጎሜዝም የአቶ በረከት መታሰር ለብዙዎች እፎይታ ነው ብለዋል።
በምርጫ 1997 የአውሮፓ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድን መሪ የነበሩት አና ጎሜዝ በምርጫ 1997 በአዲስ አበባ ጎዳና ለፈሰሰው ደም ተጠያቂ ከሚያደርጓቸው የኢሕአዴግ  ባለስልጣናት አንዱ አቶ በረከት ስምኦን ናቸው።

በኢትዮጵያ ከ500 የሚበልጡ የሶሪያ ስደተኞች አሉ ተባለ


በኢትዮጵያ ከ500 የሚበልጡ የሶሪያ ስደተኞች እንደሚገኙ ተገለጸ።
እ ኤ አ ከ2011 ጀምሮ በጦርነት ከምትታመሰው ሃገር ሶሪያ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ስደተኞች በልመና እና በመለስተኛ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙም አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል።

የኢትዮጵያ የስደተኞችና የዜግነት ጉዳይ መምሪያ ቃል አቀባይ አቶ የማነ ገብረመስቀል ለአልጀዚራ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ደሃ ሃገር ብትሆንም ከ20 ከሚበልጡ ሃገራት ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች ብለዋል።
ከሐምሌ መጨረሻ እስከ ታህሳስ መጀመሪያ በ4ወር ከ15 ቀን ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሶሪያውያን ቁጥር በአጠቃላይ 560 ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 157ቱ በስደተኝነት ተመዝግበዋል።
50 የሚሆኑት ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ሲሰጣቸው የቀሩት በትራንዚትና በቱሪስት ቪዛ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ገልጸዋል።
ስደተኞቹ በሱዳን በኩል እንደሚመጡም አክለዋል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ሶሪያውያን ቁጥር ግን አልተገለጸም።
ግጭቱ እንደተነሳ የተሰደደውና ከ5 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ የገባው አብዱላሂ መሃመድ የተባለው የ20 ዓመቱ ሶሪያዊ አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ደማስቆ በተባለ ምግብ ቤት ውስጥ በአስተናጋጅነት ያገለግል የነበረው አብዱላሂ ሙሃመድ በሱዳን በኩል በ15 ዓመቱ ኢትዮጵያ መግባቱን ለአልጄዚራ ገልጿል።
ለርሱ ኢትዮጵያ የተረጋጋች ሃገር ስትሆን ህዝቧም ለጋስ ነው ሲል ተናግሯል።
ብዙ ሶሪያውያን በቅዱስ ቁርዓን ውስጥ ኢትዮጵያ የሙስሊም ስደተኞች መጠጊያ እንደነበረች ያውቃሉ ያሉት የኢትዮጵያ የስደተኞችና የዜግነት ጉዳይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ የማነ ገብረመስቀል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስና በሶሪያ መካከል ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ግንኙነት ብዙ ሶሪያውያን ሙሉ በሙሉ የባዕድነት ስሜት እንዳይሰማቸው ያደርጋል ሲሉም አክለዋል።
በአዲስ አበባ ጉዳዮች በተለይም በቤተክርስቲያንና በመስጊድ አካባቢ እየለመኑ የሚኖሩት ሶርያውያን በአማርኛ ቋንቋ የተጻፈ “እርዱኝ” የሚል ምልክት እንደሚይዙም ከአልጀዚራ ዘገባ መረዳት ተችሏል።
እውነተኛ ስሙን መናገር ያልፈለገውና ራሱን አህመድ በማለት የገለጸው የ18 ዓመቱ ሶሪያዊ በአዲስ አበባ ጎዳና ለልመና የተሰማራው የወንድሙን ልጅ ይዞ ሲሆን ከርሱ ጋር ከወጡት ወንድሙና እህቱ ውጭ መላ ቤተሰቡ በጦርነትቱ አልቀዋል።
“እግዚአብሔር ታላቅ ነው ኢትዮጵያውያን እየተንከባከቡን ነው” ያለው የ18 ዓመቱ አህመድ ሶሪያ ሰላሟ እስኪመለስ በኢትዮጵያ ስራ ማግኘት ካልቻልኩ ያለሁበት ሁኔታ አስቸጋሪ ነው ብሏል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በታህሳስ ወር 2011 በቱኒዚያ በመሃመድ ቡአዚዝ በተለኮሰው የአረቡ ዓለም አብዮት ከተናወጡት የአረቡ ሃገራት አንዷ የሆነችው ሶሪያ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2011 እስከ የካቲት 2016 በጦርነቱ 470 ሺህ  ያህል ሰው እንዳለቀባት የሶሪያ የፖሊስ ምርምር ተቋም አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ይፋ ባደረገው መረጃ ባለፍት 8 ዓመታት 7.6 ሚሊዮን ያህል ህዝብ ከሃገሪቱ ሲፈናቀል 5 ሚሊዮን ያህሉ ተሰደዋል።
ሶሪያ 18 ሚሊየን ያህል ህዝብ የሚኖርባት ሃገር ነች።
ከጥንታዊ የዓለም ሃገራት አንዷ የሆነችው 5 ደማስቆና አሌፓ በሚባሉት ጥንታዊ ከተሞች የምትታወቀው ሶሪያ በዋናነት ማለትም 87 በመቶ የሙስሊም ሃገር ብትሆንም ስልጣን የያዙት ከአናሳዎቹ ሺአ ሙስሊሞች የወጡ አሊዊት የሚባለውን ዘርፍ የሚከተሉ የሃገሪቱን መሪነትና የወታደሩን ክፍል መቆጣጠራቸው ለችግሩ መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉም ተመልክቷል።

በአፍሪካ የቢሊየነሮች ቁጥር ከ23 ወደ 20 መውረዱን ፎርብስ ዘገበ።


የባለጸጎቹን የሃብት መጠን በተመለከተ በየዓመቱ ደረጃ የሚያወጣው ፎርብስ በሳምንቱ መጨረሻ በለቀቀው ሪፖርት ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጉቴ በ10.3 ቢሊየን ዶላር አሁንም የአፍሪካ ግንባር ቀደም ሃብታም ቢሆኑም ሃብታቸው ከቀደመው ዓመት ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ ተገኝቷል።

አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የሚገኘው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለቤት መሆናቸውም ይታወቃል።
ከዓመት በፊት የዚሁ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅና ሌሎች የድርጅት ሰራተኞች ባልታወቁ ታጣቂዎች አዲስ አበባ አቅራቢያ መገደላቸው አይዘነጋም።
አሊኮ ዳንጎቴ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ባለጸጋ ሲሆኑ ሁለተኛ ባለጸጋ የሆኑትም ናይጄሪያዊው ማይክ አዶንጋ ሲሆኑ የሃብታቸው መጠንም 9.2 ቢሊየን ዶላር ነው።
ማይክ ኦዶንጋ አምና የነበራቸውን የ5.3 ቢሊዮን ዶላር ሃብት በዓመት ግዜ ወደ 9.2 ቢሊየን ዶላር ማሳደጋቸውም ተመልክቷል።
የአፍሪካ ባለጸጋነትን ደረጃ በ3ኛነት የያዙት ደቡብ አፍሪካው ኒኪ ኦፕንሒሟር ሲሆኑ የሃብታቸው መጠን 7.3 ቢሊየን ዶላር እንደሆነም ተጠቅሷል።
በአጠቃላይ ከ20ዎቹ የአፍሪካ ቢሊየነሮች 5ቱ ግብጻውያን እንዲሁም ሌሎች 5 ደቡብ አፍሪካውያን ናቸው።
ናይጄሪያ 4 እንዲሁም ሞሮኮ 2 ቢሊየነር ሲኖራት አልጄሪያ፣ አንጎላ እንዲሁም ታንዛኒያና ዚምባቡዌ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ቢሊየነር አስመዝግበዋል።
አምና በቢሊየነር ዝርዝር ውስጥ የነበሩትና ዘንድሮ ከስረው ሃብታቸው ቢሊየን ዶላር መጠጋት ያልቻለው ባለሃብቶች ሶስቱም የደቡብ አፍሪካ ተወላጆች መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል።
ይህ የአፍሪካ ቢሊየነሮች ዝርዝር በትውልድ ሱዳናዊ በዜግነት እንግሊዛዊ የሆኑትን ዶ/ር መሃመድ ኢብራሂም (ሞ ኢብራሂም) እንዲሁም በዜግነት ሳውዲ አረቢያ የሆኑትን ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሺህ መሃመድ አልአላሙዲንን በአፍሪካ ዝርዝር ውስጥ አላስገቡም።
ላለፉት 15 ወራት ያህል በሳውዲ አረቢያ በእስር ቤት የሚገኙት መሃሙድ አላሙዲና የሌሎቹ የሳውዲ ባለጸጎች የሃብት ሁኔታ በቂ መረጃ ባለመኖሩ ከቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ መሰረዛቸው ታውቋል።
በዓለማችን ያሉ ቢሊየነሮች በአጠቃላይ 2ሺህ 208 መሆናቸውም ተመልክቷል።
እነዚህ የ72 ሃገራት ዜጎች ሲሆኑ 585 ቢሊየነር በመያዝ አሜሪካ ቀዳሚ ስትሆን ቻይና በ373 ቢሊየነሮች ሁለተኛውን ስፍራ ይዛለች።
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ጄፍ ቢዞ በ136 ቢሊየን ዶላር በቁንጮነት ተቀምጧል።

Monday, January 21, 2019

በአለም በከባድ ድህነት ውስጥ ያሉ ዜጎች በአምስት ሃገራት ይኖራሉ ተባለ

በአለም እጅግ ከፍተኛ በሚል ድህነት ውስጥ ካሉ ዜጎች ግማሽ የሚሆኑት የሚኖሩት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት ሃገራት መሆኑ ተገለጸ። እንደጥናቱ ቢሊየን ከሚበልጠው የዓለም ህዝብ 736 ሚሊየኑ በተጎሳቆለ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ መሆኑ ታውቋል።

ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ግማሹ ማለትም 368 ሚሊየኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት የአፍሪካ ሃገራት የሚገኙ ናቸው።
የአለም ባንክ ባላፈው ቅዳሜ ይፋ ባደረገውና እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 በተደረገው ጥናት መሰረት በዓለማችን ከፍተኛ የድሃ ቁጥር የያዙ ሃገራት በሚል የተዘረዘሩት 5 ሃገራት ሕንድ፣ ናይጄሪያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሁም ባንግላዴሽና ኢትዮጵያ ናቸው።
እነዚህ 5 ሃገራት በ2015 ከተመዘገቡ 736 ሚሊዮን መናጢ ድሃዎች 368 ሚሊየኑን ይዘዋል።
የዓለማችንን ከፍተኛ የድሃ ቁጥር የያዙት 5 ሃገራት በደቡብ ኢስያና ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሲሆን በእነዚህ ክፍለ ዓለማት ያሉት አጠቃላይ የተጎሳቆሉ ድሆች በጠቅላላ 629 ሚሊየን መሆናቸውም ተመልክቷል።
በአለም ባንክ መመዘኛ ከፍተኛ ድሃ በሚል የሚጠቀሱት የቀን ገቢያቸው በአሜሪካ ዶላር ከ1 ብር ከ90 ሳንቲም ያነሰ የሚያገኙት ናቸው።
ይህም በኢትዮጵያ 54 ብር ማለት ነው።
ሕንድ 1 ቢሊየን 3 መቶ ሚሊየን ከሚሆነው ህዝቧ በፍጹም ድህነት የሚኖረው 13.4 በመቶ ብቻ ቢሆንም በህዝብ ቁጥሯ ትልቅነት ከፍተኛውን ድርሻ ይዛለች።
ያም ሆኖ ግን ህንድና ባንግላዴሽ ከ10 ዓመት በኋላ ዜጎቻቸውን ከፍጹም ድህነት ሙሉ በሙሉ እንደሚያወጡና እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 ፍጹም ደሃ የሌለባቸው ሃገራት እንደሚሆኑ ባለሙያዎች ተንብየዋል።
በኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ግን ድህነቱ እየጨመረ እንደሚሄድ ነው ጥናቱ ያመለከተው።
ይህም የሃገራቱን እንቅስቃሴ መሰረት ባደረገ ጥናት ላይ የተመረኮዘ እንደሆነም መረዳት ተችሏል።

Sunday, January 20, 2019

በድሬዳዋ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ


በድሬዳዋ ከተማ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።
በተቃውሞው የተገደለ ሰው ባይኖርም በርካታ ሰዎች በጥይት ተመተው መቁሰላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

ባለፈው ሰኞ ታቦት ወደ ቤተክርስቲያን በሚያመራበት ጊዜ በተወሰኑ አካላት ድንጋይ መወርወሩን ተከትሎ በቁጣ ለተቃውሞ የወጣው ህዝብ የተጠራቀመ ብስሶቱን በማሰማት ላይ እንደሆነም ተገልጿል።
ነዋሪውን ያገለለው የድሬዳዋ ከተማ መዋቅር እንዲፈርስ በህዝቡ ተጠይቋል።
ተቃውሞ ወደ አመጽ የተቀየረው የከተማው ከንቲባ ህዝቡን ለማነጋገር የጠሩትን ስብሰባ በመቅረታቸው እንደሆነም ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በከተማዋ ባሉ ሁለት መንደሮች መንገዶች በተቃጠለ ጎማ ተዘግተው የተጠናከረ ተቃውሞ እየደረገባቸው ነው።
በተቃውሞው በእሳት የወደሙ መንግስታዊ ተቋማት መኖራቸውም ተመልክቷል።
መነሻው የአንድ ቀን አጋጣሚ ቢሆንም የተጠራቀመና ዓመታትን የዘለቀ የህዝብ ጥያቄና ብሶት አደባባይ የወጣበት ክስተት ሆኗል።
ባለፈው ሰኞ የጥምቀት በዓል ታቦት ለማስገባት የወጣው ህዝብ ላይ ካልታወቀ አቅጣጫ፣ ባልታወቁ ሰዎች ድንጋይ ውርወራ ይጀመራል።
ሁኔታው አለመረጋጋትን ቢፈጥርም በወቅቱ ታቦታቱን ወደ ማደሪያቸው የማስገባቱ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቀቀ።
ይህ መነሻ የሆነው ተቃውሞ ባለፉት ሶስት ቀናት የድሬዳዋ ከተማን በቀውስ እንድትቆይ አድርጓታል።
ነዋሪው ወደ አመጽ ከመግባቱ በፊት የዓመታት ጥያቄዎቹን በሰላማዊ መንገድ በማቅረብ ላይ እንደነበረ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።
ጥያቄዎቹ የከተማዋን ነዋሪዎች ባይተዋር ያደረገው፣ እንደሁለተኛ ዜጋ እንዲታይ ያስገደደው የከተማዋ አስተዳደር መዋቅር ላይ ያተኩሩ ናቸው።
ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት 40 40 20 በሚል የተዋቀረው የከተማዋ አስተዳደር የነዋሪውን መብት መሉ በሙሉ የገፈፈ ነው።
ሰላም ያጣንበት፣ የከተማው ወጣት በስደት ሀገር የለቀቀበት መዋቅር መፍረስ አለበት ወደ ሚል ተቃውሞ የተለወጠ ሲሆን መንገዶችን በድንጋይና በተቃጠሉ ጎማዎች በመዝጋት ዛሬን ጨምሮ ላለፉት ሶስት ቀናት ድሬዳዋ በተቃውሞ ላይ መሆኗን ነው ነዋሪዎች የሚገልጹት።
የተከማቸ ብሶት ፈንቅሎ የወጣበት አጋጣሚ ተፈጥሯል የሚሉት ነዋሪዎች መፍትሄ እንዲሰጠውም ጠይቀዋል።
በሰላም እየተካሄደ የነበረው ተቃውሞ ወደ አመጽ የተቀየረውም የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ህዝቡን ለማነጋገር ከጠሩ በኋላ ከስብሰባው በመቅረታቸው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
በከተማዋ አዲስ ከተማ በሚባል አካባቢ በርካታ ወጣቶች  ከታጣቂዎች ጋር መጋጨታቸውን ቀስ እያለም ወደሌሎቹ የከተማዋ ክፍሎች መዛመቱን ነው የደረሰን መረጃ ያመለከተው።
ደቻቱ፣ ሳቢያን፣ ገንደ ቆሬና ዲፖ በተባሉ አካባቢዎች መንገዶች በተቃጠሉ ጎማዎችና በድንጋይ ተዘግተው ውለዋል።
በህዝብ ቁጣ የተቃጠሉ የቀበሌ ህንጻዎች እንዳሉም ተገልጿል።
በግጭቱ በጥይት የተመቱ ወጣቶች መኖራቸውን የገለጹት ነዋሪዎች በመንግስትና ህዝብ ንብረት ላይ ጥቃት እንዳይደርስ ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

Saturday, January 19, 2019

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በናፍቆት ይጠብቁትና ሲመኙት የቆዩትን የጥምቀት በዓሉን በጎንደር እንዳያከብሩ ለምን ተፈለገ?

ቅዱስ ፓትሪያርኩን በጎንደር
እንዳይቆዩ ያደረጋቸው ማነው ?
*★★★*
~ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በናፍቆት ይጠብቁትና ሲመኙት የቆዩትን ጥምቀትን በጎንደር የማክበር ዕቅዳቸው ለምን ተሰረዘ? በዓሉን በጎንደር እንዳያከብሩ ለምን ተፈለገ?
~ "በጎንደር የጸጥታ ችግር ስላለ መንግሥት በአስቸኳይ ይዛችኋቸው ተመለሱ ስላለን ነው የመለስናቸው።" ፕሮቶኮላቸው።
~ "የለም የለም የቅዱስነታቸው ጤንነት አስጊ በመሆኑና የሰሜን ጎንደር የሀገረ ስብከቱ ሰዎችም ይዛችኋቸው በቶሎ ተመለሱ ስላሉን ነው።" ወንድማቸው አቶ ገብረመስቀል።
~ እኛ "ከፓትሪያርኩ ጋር የመጡ ሕገወጥ የልዑካን ቡድኖች በአንድ ቀን ከ100 ሺህ ብር በላይ ስላስወጡን ከእንግዲህ የእናንተ በጀት አይመለከተንም ነው ያልነው። " የሀገረ ስብከቱ ሰዎች "
 Image may contain: one or more people and people sitting
#ETHIOPIA | ~ የቅዱስ ፓትሪያርኩን ደኅንነት በተመለከተ ከስደት ያመጣቸው መንግሥት ከወዲሁ ትኩረት ሰጥቶና ጣልቃ ገብቶ በቅርበት ቢከታተላቸው መልካም ነው።
የቅዱስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ደኅንነት በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች ቢደርሱኝም እስከ አሁን ድረስ በቅዱስነታቸው ሕይወት ዙሪያ ምንም ነገር ላለማለት፤ ምንም ዓይነት አስተያየትም ላለመስጠት ራሴን በማግለል ቆይቻለሁ። ወደፊትም በዚህ ጉዳይ ምንም ዓይነት አስተያየት ባልሰጥ ፈቃዴ ነው። የሆነው ሆኖ ግን አንዳንድ ሾልከው የሚደርሱኝ መረጃዎች አስደንጋጭ ሲሆኑብኝ ጉዳዩን ለህዝብ ይፋ ከማድረግ በማለት ዓይኔን በጨው አጥቤ መደወል ያሉብኝና ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት ጋር ሁሉ ደውያለሁ። እናም ከበቂ በላይ መረጃም አግኝቻለሁ።
የቅዱስ ፓትሪያርኩ ዘመነ ፕትርክና በአስቸጋሪ ውጣ ውረድዶች የተሞላ እንደሆነ ይታወቃል። ከደርግ ሥርዓት መውደቅ በኋላ መጀመሪያ በኬንያና ኋላ በሀገረ አሜሪካ በግዞት እንዲኖሩም የተፈረደባቸው አባት መሆናቸውም ይታወቃል። በተለይ በውጭ የሚገኙት የቀድሞው የስደተኛው ሲኖዶስ አባቶች ቅዱስነታቸውን እንደመያዣ በማድረግ ከቁም እስር ባልተናነሰ መልኩ ከሰው ሳያገናኟቸው በዝግ ቤት ከርቸመውባቸው እንዳቆዩዋቸው የሚናገሩ አሉ። ከካናዳ አሜሪካ ድረስ መኪና እያሽከረከሩ በብዙ ድካም ቅዱስነታቸውን አግኝተው የመጨዋወት አጋጣሚን ያገኙ ሁለት ወዳጆቼም የነገሩኝ ይሄንኑ ነበር። በዚህ ምክንያት ግልጥ ያሉ ጴንጤ መነኮሳት ኢየሱስ አማላጅ፣ ታቦት አያስፈልግም የሚሉ አፍቃሬ ዘርፌና በጋሻው መነኮሳት በእስረኛው፣ በታጋቹ ፓትሪያርክ አማካኝነት ለማዕረገ ጵጵስና በቅተው ይኸው ዛሬ እንደ ደህና ሰው ይፍቱኝ ይባርኩኝ የሚባሉ ጳጳሳት ሆነው እያየናቸው ነው። እኛም ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ ብለን ጮጋ ብለን ተቀምጠናል። በእውነት የስዊዲኑ ሊቀጳጳስ አረጋዊው ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ብዙውን ችግር ያውቃሉ። ለብዙ ቀናትም በስልክ ያወሩኝም ይሄንኑ ነበር።
ቅዱስነታቸው በሀገረ አሜሪካ በስደት ሳሉ ልብሳቸው በላያቸው ላይ እስኪቆሽሽ፣ ከተቀመጡበት ወንበር ላይ ሳይነሱ ኩርምት ብለው ይውሉም ያድሩም ስለነበር አሁን ለገጠማቸው ችግር መንስኤ የሆኗቸውም ይኸው ነው ይባላል። የችግራቸው ምንጩ እነዚሁ ፓትሪያርኩን አግተው እንደያዙና መጠቀሚያ እንዳደረጉዋቸው የሚነገርላቸው የቅርብ ሰዎቻቸው ነን ባይ ግለሰቦች አማካኝነት እንደነበር ይናገራል። " ልጆቼ በእኔ ቲተርና ፊርማ የሚወጣው ደብዳቤ ሁሉ እኔ አላውቀውም። አይመለከተኝምም። እኔን ለሀገሬ አፈር እንዲያበቃኝ ብቻ ጸልዩልኝ " እንዳሏቸው እነዚሁ በሀገረ ካናዳ ኗሪ የሆኑ ወዳጆቼ የነገሩኝንም አልረሳም።
በፈቃደ እግዚአብሔር፣ በተለይ በዲያቆን ዳንኤል ጎትጓችነትና አሳሳቢነት፣ በኮሚቴዎች ጥረት፣ በጠሚዶኮ ዐቢይም ጉትጎታ ቀኑ ደርሶ፣ የቅዱስነታቸውም የስደት ዘመን አብቅቶ በፈቃደ አምላክ ቅዱስነታቸው ከስደት ተመልሰው በክብር ለሀገራቸው በቅተዋል። እነ ዲያቆን ዳንኤል ተጋድለው ቅዱስ ፓትሪያርኩን ወደ ሀገራቸው ባይመልሷቸው ኖሮ አይበለውና ፓትሪያርኩ እረፍተ ዘመን ቢገታቸው ቀሪዎቹ ሌላ አዲስ ፓትሪያርክ ከመካከላቸው መርጠው የቤተክርስትያንን የመከራ ዘመን ለማርዘም እንደ ነበር ይነገራል። ለማንኛውም እግዚአብሔር ያለው ሆኖ አሁን የሚታየው ሁሉ ሆነ።
#ብዥታን_ስለማጥራት
የቅዱስ ፓትሪያርኩን የአቡነ መርቆሬዎስን መመለስ ጨጓራ ያስነሳባቸው ሰዎች የሉም ማለት አይደለም። በተለይ የህወሓት ታጋይ የነበሩ ጳጳሳትና የዘመነ ህወሓት ፈላጭ ቆራጭ የቤተክህነቱ አድራጊ ፈጣሪዎች የያዘ ይዟቸው እንጂ ልክ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የመጣባቸው ያህል ነው ነስር በነስር ያረጋቸው። በስጭቷቸዋል። ነገር ግን ምንም ማድረግ የማትችሉት ነገር ሆኖባቸው እህህህ እንዳሉ ይኸው እስከ አሁን ድረስ አሉ።
ከዚህ የተነሳ ብዙው ጫና የራያ ሰው በሆኑት በጠቅላይ ቤተክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ትከሻ ላይ ነው የወደቀው። ትግሬ ጠሎቹ ግሩፖች አቡነ ዲዮስቆሮስ ትግርኛ ስለሚናገሩና አሁን ባለው አከላል ራያ በትግራይ ስር ስለሆነች እሳቸውን በትግሬነት መድበው ፓትሪያርኩን እየበደሏቸው ነው የሚል ስሞታ ያቀርባሉ። አይደለም አቡነ ዲዮስቆሮስ ዐማራ ናቸው የሚሉ የትግሬ ሰዎች ደግሞ በበኩላቸው ሊቀጳጳሱን ይኮንናሉ። በመሃል አቡነ ዲዮስቆሮስ የገና ዳቦ ሆነው ተገኝተዋል። በተለይ የቅዱስነታቸው ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ ዘመዶች ነን የሚሉ አካላት ያደረሱኝን መረጃ መነሻ አድርጌ በቀጥታ ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ደውዬ ረዘም ላሉ ሰዓታት በዚህ ዙሪያ አውርቼአቸዋለሁ።
በዚህም ምክንያት የብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስን ስቃይ ለመረዳትም ችያለሁ። " ይኸውልህ ዘመድኩን ለቅዱስነታቸው የሚደረገውን ነገር በሙሉ ማንም አያዝበትም። እሳቸው በመረጡት ወንድማቸው በኩል የጠየቁንን ከማሟላት በቀር ሌላ ነገር ውስጥ መግባት አንችልም። ጉዳዩ ስስ ነው። የእኔ ሥራ ይህን እንፈልጋለን ሲሉኝ ማሟላትና ማቅረብ ብቻ ነው። ምክንያቱም ደግሞ የታወቀ ነው። ስለዚህ ሁሉ ነገር የሚሆነው በወንድማቸው በኩል በሚቀርብ ጥያቄ መሠረት ነው የሚፈጸመው በማለት ነበር ያስረዱኝ።
አሁን ምን ተፈጠረ?
የአክሱም ካህናት በጠየቁት ጥያቄ መሠረት ቅዱስ ፓትሪያርኩ የመጀመሪያ የሀገር ውስጥ ሐዋሪያዊ ጉዞአቸውን ወደ አክሱም ጽዮን ለማድረግ ነበር ተዘጋጅተው የነበሩት። የክልሉ ፕሬዘዳንትም ተጠይቀው ዶር ደብረ ጽዮን ከ20 መኪኖች በላይ ለአቀባበሉ ፈቅደው በክብር ተቀብለው ለማስተናገድ ፈቃደኞች እንደነበሩ ይነገራል። ከአክሱም መልስ ደብረ ታቦርና ባህርዳር፣ ከባህር ዳር ጥር 9 ጎንደር ገብተው እስከ ጥር 12 ቆይተው ጥር 13 የኔታ ጥበቡ ጋር ዛራ ሚካኤል ገብተው የአብነት ትምህርት ቤቱን ጎብኝተው ከዚያም የጣና ሐይቅ ላይ የሚገኙ ገዳማትን ጎብኝተው ሊሚለሱ ነበር ዕቅድ የተያዘው ይላሉ የውስጥ አዋቂዎች።
ለዚሁ የቅዱስነታቸው ጉዞ ሲባል የተቋቋመ ኮሚቴ ቅዱስነታቸው በሚጎበኟቸው ሥፍራዎች በሙሉ ሲደርሱ ለገዳማቱና ለአብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ይሆን ዘንድ በስማቸው የሚያበረክቱት ወደ 500 ሺ ብር የሚጠጋ ገንዘብም ከባለሃብቶች እንደተሰበሰበም ይነገራል።
ነገር ግን ጉዳዩ እስከአሁን ለማንም ግልጽ ባልሆነ መልኩ ሙሉ በሙሉ ታቀደው የነበሩት ዕቅዶች ሳይፈጸሙ እንዲሰረዙ ተደርገዋል። ብሩ ተሰብስቦ የተዋቀረው ኮሚቴም ፈረሰ። የተዋጣው ገንዘብ በእነ አቶ ወርቁ እጅ ይገኛል የሚሉ አሉ። የአክሱም ጉዞም ተሠረዘ። የመርጦ ለመማርያም፣ የጣና ደሴትና የዛራ ሚካኤል ጉዞም ተሰረዘ። ከሁሉ ከሁሉ ሰፊ ዝግጅት የተደረገበት የጎንደሩ ጉዞአቸው ያለ ሀገረ ስብከቱ ፈቃድ ፕሮቶኮላቸውና የቅዱስነታቸው ወንድም ብቻ በሚያውቁት ምክንያት ተሰርዟል። ጉዳዩን ቅዱስነታቸው ባያውቁትም በመጨረሻ ለጉዳዩ ቅርበት እንዳላቸው የሚናገሩ ወገኖች እንደሚናገሩት ከሆነ በፕሮቶኮሉ ፈቃድ የመጡና ሃገረ ስብከቱ በማያውቃቸው ሰዎች #ውስኪ እንደውኃ በሚጠጡ ግለሰቦች ምክንያት ነው ቅዱስነታቸው ጎንደር በዓለ ጥምቀትን ማክበር እየፈለጉ ሳይወዱ በግዳቸው አንጠልጥለው ወደ አዲስ አበባ የመለሷቸው ተብሏል።
ለቅዱስነታቸው በጎንደር በዓለ ጥምቀትን እንዳይውሉ ምክንያት ነው ተብሎ የጠቅላይ ቤተክህነቱ የሕግ ክፍል በሆኑትና አሁን የቅዱስነታቸው ፕሮቶኮል በሆኑት በአፈ መምህር አባ ገብረሥላሴ በኩል የቀረበው ምክንያት "በጎንደር የጸጥታ ችግር ስላለ መንግሥት በአስቸኳይ ይዛችኋቸው ኑ ስላለን ነው" እንዳሉ የተነገረ ሲሆን። በወንድማቸው በአቶ ገብረ መስቀል በኩል ለቅዱስነታቸው ከጎንደር በዓል መመለስ ምክንያት ነው ብለው ያቀረቡት ነው የተባለው ደግሞ የቅዱስነታቸው ጤንነት አስጊ መሆንና የሰሜን ጎንደር የሀገረ ስብከቱ ሰዎች በአስቸኳይ ከተማውን ለቃችሁ ውጡ ብለው ስለነገሩን ነው ማለታቸው ተነግሯል።
በሀገረ ስብከቱ በኩል ደግሞ የሚቀርበው ምክንያት እኛ ቅዱስነታቸውንና ከእርሳቸው ጋር የሚመጡ ልኡካንን ለመቀበልና ለማስተናገድ አቅቶንም ቸግሮንም አይደለም ይላሉ። የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ እንደሚባለው ከሆነ ልዑካኑ ከጠቅላይ ቤተክህነት በጀት አስበጅተው አልመጡም። ከቅዱስ ፓርትሪኩ ጋር የመጡት 5 ሊቃነ ጳጳሳት እዚያው ያሉ 2 ሊቃነ ጳጳሳት በአጠቃላይ 7 አባቶችን ማስተናገዱ አልከበደንም። የከበደን ቤተክህነቱ በጀት በጅቶ መላክ የነበረባቸው የእነ ፋንታሁን ሙጬ እና የእነ እስክንድር፣ የእነ ገብረ ጻዲቅ እና ሌሎች የማይታወቁ፣ በፕሮቶኮሉና በፓትሪያሪኩ ወንድም በአቶ ገብረ መስቀል በኩል የተዘጋጁ ግለሰቦች ወጪ ነው ከዕቅዳችን ውጪ ናላችንን ያዞረው ይላሉ።
በተለይ 10 አለቃ ፋንታሁን ሙጬ ቅዱስነታቸውን ከፍ ዝቅ አድርጎ አባ ሊባኖስ እያለ ሲያላግጥባቸውና መጽሐፍ ሲጽፍባቸው የከረመን ሰው የቅዱስነታቸው አጃቢ አድርጎ ማምጣቱ ሳይንስ በአንድ ቀን መስተንግዶ ብቻ ከመቶ ሺህ ብር በላይ በማውጣታቸውም ጭምር መከፋፈል መፈጠሩንና ከዚህም የተነሳ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በእናንተ የተነሳ እኔ ልወቀስ አይገባም። እኔ ለእናንተ በጀት መመደብም አልችልም። የራሳችሁን በጀት ከጠቅላይ ቤተክህነቱ አስመድባችሁ መምጣት ነበረባችሁ በማለት ውስኪ አውርደው በመጠጣት ላይ የነበሩትን የቅዱስ ፓትሪያርኩ ፕሮቶኮልና እነ አጃቢዎቹን እነ ፋንታሁን ሙጬን መውቀሳቸው ለፓትሪያርኩ መመለስ እንደ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ መቅረቡም ተነግሯል።
እነ ፋንታሁን ሙጬም የጎንደር ሃገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን "ጠብቅ እናሳይሃለን" በማለት እንደዛቱባቸውም እኒሁ የመረጃ ምንጮቼ ይነገራሉ። ሥራ አስኪያጁም መልሰው የሚመጣውን ሁል ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። በአንድ ቀን 100 ሺህ ብር ለውስኪ አላወጣም። ፓትሪያርኩና ሊቃነ ጳጳሳቱ አይከብዱንም። የእናንተ ግን ከ ሕግ አግባብ ውጪ ነው ከማለታቸውም በተጨማሪ እኛ ይሄን ብር የምናመጣው እኮ በየገጠሩ ዞረን ከምስኪን አብያተ ክርስቲያናት ሰብስበን በስንት ስቃይ የምናመጣው ብር ነው። ስንት ጧፍ ዕጣንና ዘቢብ ያጡ አብያተክርስቲያናት እያሉ እኔ ለቸበር ቻቻ ውስኪ የሙዳየ ምጽዋት ገንዘብ ዝምብዬ በዘፈቀደ አላወጣም። ራሳቸውን ፓትሪያርኩን ሰድቦ መጽሐፍ ላወጣባቸው ግለሰብ የቤተክርስቲያንን ብር አውጥቼ ሜዳ ላይ አልበትንም። ካህናቱም ህዝቡም ይጠይቁኛል። ይወቅሱኛልም። በማለት የግለሰቦቹን በጀት ከለከሉ ይላሉ ጉዳዩን በቅርበት ስንከታተል ነበርን የሚሉት የመረጃ ምንጮቼ።
ከዚህ በኋላ የሆነው ምንድነው ሀገረ ስብከቱ፣ የቅዱስነታቸው ፕሮቶኮልና የቅዱስነታቸው ወንድም ከእነ ፋንታሁን ሙጬ ጋር ያለመስማማት ሆን ተብሎና ፀብ ያለሽ በዳቦ የሆነ ምክንያት አገኘን በማለት ቅዱስ ፓትሪያርኩ በጉጉትና በናፍቆት ከሚጠብቁት የጎንደር የጥምቀት በዓል ከማክበር አሰናክለው፤ በቅዱስነታቸው እጅም ለመባረክ ከሚጠብቋቸው በብዙ ሺ ከሚቆጠር ምእመናን ለይተውና አጣድፈው ወደ አዲስ አበባ እንደመለሷቸውም ተነግሯል።
ከሁሉ ከሁሉ ግር የሚለው ነገር ግን ቅዱስ ፓትሪያርኩ አዲስ አበባ እንደደረሱ የጠቅላይ ቤተክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ለውስኪና ለሕገወጥ ልዑካኑ የህዝብና የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በከንቱ ሜዳ ላይ አልበትንም ብለው ሕገ ወጥነትን እንደተከላከሉ የሚነገርላቸውን የጎንደሩን ዋና ሥራ አስኪያጁ በፋክስ በተጻፈ ደብዳቤ ከሥራ አስኪያጅነታቸው እንዳስነሷቸው መሰማቱ ነው። ይሄን ለማረጋገጥ ባደረኩት ጥረት ደብዳቤውን አይተናል የሚሉ እማኞች " ደብዳቤው ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቦታ ሲገኝላቸው ይመደባሉ፣ እስከዚያው ግን ከሥራ አስኪያጅነትዎ ተነስተዋል" ይላልም ተብሏል ለሥራ አስኪያጁ የደረሰው የሞት ደብዳቤ።
እነ ፋንታሁ ሙጬም እንደዛቱት ጉዞውንም አበላሹት፣ አሰረዙት፣ ሥራ አስኪያጁንም አስነሱት። የሆነው ይሄው ነው ተብሏል።
አሁን ጎንደር ባነር አሠርቶ ዛሬ ጠዋት በማለዳ ቅዱስ ፓትሪያርኩን ለመቀበል በጉጉት እየጠበቀ ነው። እስከ አሁን ቅዱስነታቸው መመለሳቸውን የሚያውቅ የለም። ወጣቶች የሚገርም ሠረገላ አዘጋጅተው ቅዱስነታቸውን በዚያ ላይ አስቀምጠው ጎንደርን ለማስባረክ እስኪነጋ ድረስ እየጠበቁ ነው። ነገር ግን ሁሉም ነገር ጎንደሮች እንደፈለጉት አልሄደም። ቅዱስነታቸውም ከጀርባቸው በሚሠራ ቁማር ምክንያት በናፍቆትና በስስት ይጠብቁት ከነበረው የጎንደር የጥምቀት በዓል ሳይፈልጉ በግድ ተገፍተው ነገ በጃንሜዳ ለማክበር በዚያ ይገኙ ዘንድ ተፈርዶባቸዋል።
አሁን እኔ የምፈራው በመሃል ፓትሪያርኩን በማበሳጨት የሞት ጊዜያቸውን ለማፋጠን በሚጥሩ የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎችና በሌሎች ወገኖች ሽኩቻና ፍትጊያ እንዲሁም ቅዱስነታቸውን ተጠግቶ ለመበልፀግ በቋመጠ ኃይል ምክንያት በመሃል ስህተት እንዳይፈጠር ነው የምሰጋው።
ጠሚዶኮ ዐብይ ቅዱስነታቸውን ከመንበረ ፓትሪያርኩ ጊቢ አውጥቶ ካዛንችስ ቪላ ቤት ውስጥ ማስቀመጡንም አልወደድኩትም። የደኅንነታቸውም ነገር ቢታሰብበት መልካም ነው። ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እኩልም ቢከበሩ ለሁሉም መልካም ነው ባይ ነኝ። ያለ በለዚያ ግን የቅዱስነታቸው እንባ እሳት ሆኖ ብዙዎችን እንዳይበላ እሰጋለሁ።
ጠቅላይ ሚንስትሩም አካልቦ ወዳመጣቸው ፓትሪያርክ ዐይኑን መለስ ቢያደርግ አይከፋም። አለበለዚያ ግን በሆነ ስህተት፣ በድንገት በሚፈጠር ችግር ምክንያት ሁለት ብሔሮች ለዘለዓለሙ እንዳይቆራረጡ እሰጋለሁ። አበቃሁ።
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጥር 11/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።

የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ በመጪው ሚያዚያ ሊካሄድ ነው


(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2011)በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት የነበረው የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ በመጪው ሚያዚያ ሊካሄድ መሆኑን ኤጀንሲው አስታወቀ።
የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የሕዝብና የቤት ቆጠራን ለማካሄድ አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊየን ብር እስካሁን ድረስ ወጭ ተደርጓል።

የሕዝብና የቤት ቆጠራው በሕገ መንግስቱ መሰረት በየ10 አመቱ መካሄድ ቢኖርበትም በኢትዮጵያ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት መካሄድ ከነበረበት ጊዜ ሁለት አመት አልፎታል።
የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የሕዝብና የቤት ቆጠራውን ባለፈው አመት ሕዳር ለማካሄድ ታቅዶ ሁኔታዎች ባለመመቻቸታቸው ለመጋቢት ተቀጥሮ ይህም ሳይሳካ ቀርቷል።
ይህም የሆነው በሃገሪቱ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት የፈጠረው ችግር ነው ብሏል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ለ4ኛ ጊዜ ይካሄዳል የተባለው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ታዲያ ከ2 አመታት መዘግየት በኋላ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 14/2011 እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል።
ይህም ሆኖ ግን አስቸጋሪ ነገር ከተፈጠረና ቅድመ ዝግጅቱ ካልተጠናቀቀ ቆጠራው ሊራዘም እንደሚችል በኤጀንሲው የኢንፎርሜሽንና የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሰፊ ገመዲ ገልጸዋል።
እንደ አቶ ሰፊ ገለጻ እስካሁን ባለው ቅድመ ዝግጅት የሕዝብና የቤት ቆጠራ ካርታ እንዲሁም የጥያቄና የመረጃ ግምገማ ሰነዶች ተዘጋጅተዋል።
ለዚሁም 150ሺ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ካርታ ለገጠርና ለከተሞች ተዘጋጅቷል ነው ያሉት እስካሁን ለስራው የወጣው ገንዘብ ደግሞ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ደርሷል ብለዋል።
ስራውን ለማከናወን ለሚያስፈልገው የሰው ሃይል ደግሞ 148ሺ ቆጣሪዎችና 37ሺ ተቆጣጣሪዎች እንደሚያስፈጽሙት ሃላፊው ገልጸዋል።
ይህን ስራ ለመስራት የቴክኒክ ብቃት ባላቸው የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ላይ ምልመላው ትኩረት እንደሚያደርግም ነው የገለጹት።
ቆጠራው የሚካሄደውም 663 ሚሊየን ብር በታገዙ 180ሺ ታብሌቶች እንደሚሆንም አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ፓርላማ ባለፈው ጊዜ ብሔራዊ የሕዝብና የቤት ቆጠራ ኮሚሽን አቋቁሟል።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ኮሚሽነርነት የሚመራው ይህው ተቋም 20 አባላት ያሉት ሲሆን በስሩም ዘጠኝ ሚኒስትሮችና ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንዲሁም ከክልል የተውጣጡ ተወካዮችን አካቷል።
የሕዝብና የቤቶች ቆጠራው በመጭው ሚያዚያ መጀመሪያ ላይ ይካሄዳል ቢባልም በአሁኑ ጊዜ ባለው የሃገሪቱ ሁኔታ አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
ምርጫው ካልተላለፈም ቆጠራውን ለማካሄድ አስቸጋሪ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል።
በኢትዮጵያ በስራ ላይ ባለው ሕገ መንግስት የሕዝብና ቤት ቆጠራው በየ10 አመቱ መካሄድ ነበረበት።

Friday, January 18, 2019

በቄሌም ወለጋ የኦነግ ታጣቂዎች ባንኮችን ዘረፉ።


የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውም ተሰምቷል።

የቄሌም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ቀናት በኦነግ ታጣቂዎች ስድስት ባንኮች ተዘርፈዋል። ሁለት የወረዳ የመንግስት መስሪያቤቶች ተቃጥለዋል።
በመንግስትና በግል ባንኮች ላይ በተፈጸመው ዝርፊያ ምን ያህል ገንዘብ መወሰዱን ማወቅ አልተቻለም።
ኦነግ በዞኑ ግድያን ጨምሮ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን መፈጸሙን የሚያመለክቱ መረጃዎች በመውጣት ላይ ናቸው።
በሌላ በኩል አየር ሃይል የኦነግን ካምፖች በአውሮፕላን መምታቱን በመግለጽ የወጡ ዘገባዎችን የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች የተሳሳተ ሲሉ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የቄሌም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታመነ ሃይሉ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ቀናት በኦነግ ታጣቂዎች 3 የመንግስትና 3 የግል ባንኮች ዘረፋ ተፈጽሞባቸዋል።
ባንኮቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የህብረት ስራ ባንኮች ሲሆኑ በተለያዩ የቄሌም ወረዳ ቅርንጫፍ ከፍተው የሚንቀሳቀሱ እንደሆኑ አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
የተዘረፈው የባንኮቹ ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ ለጊዜው እንደማይታወቅ የገለጹት አቶ ታመነ በሂሳብ ሰራተኞች ምርመራ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ጥቃት የደረሰባቸው ሌሎች ተቋማት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ናቸው።
በቄሌም ወለጋ ዞን የተለያዩ የወረዳ ጽሕፈት ቤቶችን ማቃጠል የኦነግ ስትራቴጂ መሆኑ እየተነገረ ነው።
የቄሌም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታመነ ሃይሉ እንደገለጹት በሰሞኑ ጥቃት ሁለት የወረዳ የመንግስት ጽሕፈት ቤቶች በኦነግ ታጣቂዎች በተወሰደባቸው ርምጃ ተቃጥለዋል።
በአካባቢው የመንግስት ሃይል በሚደርስበት ጊዜ የኦነግ ታጣቂዎች በመሸሽ ሌላ አካባቢ እንደሚሄዱና ተመሳሳይ የዘረፋና የማውደም ርምጃ እንደሚወስዱ ነው አቶ ታመነ የሚገልጹት።
አፈናና ግድያ ለወራት በአካባቢያቸው እንደነገሰም አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
መንግስት ርምጃ መውሰድ በመጀመሩ በግድያና አፈና ላይ የኦነግ አቅም እንደቀድሞ አለመሆኑ ተመልክቷል።
አቶ ታመነ እንደሚሉት ቀሪ ባንኮችን ከዘረፋ ለማስጣል የመንግስት ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው በመግባት ጥበቃ እያደረገ ነው።
ህብረተሰቡን በማስተባበር የመከላከል ርምጃ በመወሰድ ላይ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
በዚሁ ሰሞን የኦነግ ታጣቂዎች ከምዕራብ ወለጋ ዞን 11 ባንኮች ላይ ዘረፋ መፈጸማቸው መዘገቡ ይታወሳል።
በድምሩ ባለፉት አራት ቀናት በወለጋ ከ17 በላይ ባንኮች ላይ ዘረፋ የተፈጸመ ሲሆን የገንዘቡ መጠን እንደማይታወቅ ነው የተገለጸው።
ከሶስት ሳምንት በፊት በጉጂ ዞን ከሻኪሶ 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ጭኖ በሚሄድ የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ አጀብ ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት የፈጸመው የኦነግ ቡድን ተሽከርካሪዎቹን የሚጠብቁ ሁለት የመንግስት ወታደሮች መግደሉ የሚታወስ ሲሆን ገንዘቡ በአንደኛው ተሽከርካሪ ሾፌር አማካኝነት ከዘረፋ መትረፉ ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮጵያ አየር ሃይል አውሮፕላኖች በወለጋ የኦነግ ወታደራዊ ካምፖችን መደበደባቸውን በተመለከተ የወጣውን ዘገባ የተሳሳተ ነው ሲሉ የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች ገልጸዋል።
የአየር ሃይል አዛዥ ዙሪያ ያሉ ምንጮች እንደገለጹት የተለመደ መደበኛ የቅኝት በረራ ከማድረግ ያለፈ በአውሮፕላን የተፈጸመ ጥቃት የለም።
ይህን የምንጮችን መረጃ ወታደራዊ ባለሙያዎችም ይደግፉታል።
የቀድሞ የአየር ሃይል አብራሪና የበረራ መመህር ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ ለኢሳት እንደገለጹት ዘገባው የተጋነነ፣ ከወታደራዊ ሳይንስና አሰራር ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ ነው።
የኦነግን አቅም ለማግዘፍ የተደረገ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

Thursday, January 17, 2019

Ethiopia: Police seize thousands of illegal weapons, amos, cash



ESAT News (January 17, 2019)
The Addis Ababa Police Commission said it has seized over 2,000 weapons, about 55,000 amos as well as thousands of cash in the last six months of crackdown against scoundrels.
The statement by the capital police commission said 2,383 various types of weapons and 55,615 ammunitions have been seized in a joint operation with the National Intelligence and Security Services and other relevant law enforcement bodies.
68,322,344 cash in birr (2.5M USD), 88,151USD, 9,480 Euros, 12,620 Pounds and other currencies have been caught in the crackdown, according to Deputy PR Director, Commander Fasika Fanta.
The illegal weapons were mostly hidden in vehicle parts while the money was changing hands under the guise of legitimate businesses. Thousands of fake currency notes were also caught.
Tips from the community and collaboration with other law enforcement agencies had led to the arrest of suspects and exhibits, according to the police commission.

አሜሪካ ወህኒ ቤት የ8 አመቱ ታዳጊ ሕይወቱ አለፈ


 በአሜሪካ ወህኒ ቤት የ8 አመቱ ታዳጊ ስደተኛ ትላንት ሕይወቱ ማለፉ ተሰማ።
በፈረንጆቹ የገና በአል ሕይወቱ ያለፈው የ8 አመቱ ታዳጊ የጓቲማላው ተወላጅ ፍሊፕ ጎሜዝ በዚህ ወር በአሜሪካ ወህኒ ቤት ሕይወታቸው ያለፈውን ታዳጊዎች ቁጥር ወደ 2 ከፍ አድርጎታል።

የታዳጊውን ሕልፈት ተከትሎ የአሜሪካ የጉምሩክና የድንበር ጥበቃ አሰራሩን በመከለስ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ አድርጓል።
ሆስፒታል ቆይቶ ሲመለስ ህመሙ የተባባሰበት የ8 አመቱ ታዳጊ በአሜሪካ የድንበር ጠባቂዎች ከአባቱ ጋር የታሰረው በህገወጥ መንገድ አሜሪካ ገብታችኋል በሚል ነው።
ሕጻኑ ፍሊፕ አሎንዞ ጎሚዝ እሁድ እለት የህመም ምልክት እንደታየበት ያስተዋሉት የእስር ቤቱ ሃላፊዎች ወደ ሃኪም ቤት ወስደውታል።
ሃኪሞቹ በሕጻኑ ላይ የጉንፋን በኋላም የትኩሳት ምልክት ማግኘታቸውን ተከትሎ ለአንድ ሰአት ከ30 ደቂቃ ሆስፒታል ውስጥ ከቆዩ በኋላ አሞክስሊንና አይፕሮፊን መድሃኒት ሰጥተው እንዲሸኙት ከሲ ኤን ኤን ዘገባ መረዳት ተችሏል።
ሰኞ ምሽት የ8 አመቱ ታዳጊ በተደጋጋሚ ሲያስመልሰው ወደ ሆስፒታል በድጋሚ የተወሰደ ሲሆን ከሰአታት በኋላም ሕይወቱ ማለፉ ተመልክቷል።
የሕጻኑ ሞት መንስኤ ያልታወቀ ሲሆን ጉዳዩ ተመርምሮ ይፋ እንደሚደረግ የጉምሩክና የድንበር ጥበቃ ባለስልጣናቱ ይፋ አድርገዋል።
የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ጥበቃ ኮሚሽነር ኤቪን ማክሌናን በሰጡት መግለጫ የታዳጊውን ፍሊፕ ጎሜዝን ሞት ተከትሎ የፖሊሲ ለውጥ መደረጉን አስታውቀዋል።
በሕገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው በሚገኙት ልጆች በተለይም ከ10 አመት በታች በሆኑት ላይ ሁለተኛ ዙር የጤና ምርመራ ማድረግ እንዲሁም የሕክምና እርዳታ ከሚያደርጉ አካላት ጋር በትብብር መስራትና የቤተሰብ ማቆያ ስፍራዎችን ማመቻቸትን ጨምሮ ርምጃዎችን ለመውሰድ መዘጋጀቱን ገልጿል።
በዚህ በታህሳስ ወር መጀመሪያም የ7 አመት ታዳጊ ጓቲማላዊት በተመሳሳይ ሕይወቷ አልፏል።
የ7 አመቷ ጓቲማላዊት ጃክሊን ማክዊን ከአባቷ ጋር የ2000 ማይል ጉዞ አድርጋ በአሜሪካ ግዛት ኒው ሜክሲኮ ስትደርስ ከአባቷ ጋር ተይዛለች።
ታስራ 48 ሰአት ሳይሞላ ሕይወቷ ማለፉ ተሰምቷል።
በስደት ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሰዎችን ለመቆጣጠር የትራምፕ አስተዳደር ያወጣውን ጥብቅ መመሪያ ተከትሎ የአሜሪካን ምድር የረገጡ ስደተኞች በብዛት ወደ ወሕኒ ማጋዙ ተጠናክሮ መቀጠሉ ይታወሳል።

U.S. refuses to discuss Iranian TV anchorwoman's detention


marzieh-hashemi-press-tv-iran.jpg
An undated photo published online by Iran's state-run English language TV network Press TV shows its news anchor, Marzieh Hashemi, born Melanie Franklin of New Orleans, whom the network said on Jan. 16, 2019, was detained in the U.S. Press TV
The U.S. Justice Department and the FBI continued on Thursday to refuse comment on the alleged detention of an American woman who has worked for years as an anchorwoman on Iran's state-run television. Marzieh Hashemi was arrested by the FBI during a visit to the U.S. on Sunday, Iran's English-language broadcaster Press TV reported Wednesday. Her son has said she is being held in a prison, apparently as a material witness.
Hashemi was detained in St. Louis, where she had filmed a Black Lives Matter documentary after visiting relatives in the New Orleans area. She was then taken to Washington, according to her elder son, Hossein Hashemi.
Contacted by CBS News, both the FBI and the Justice Department have declined to comment on the case.
Hashemi, 58, was born Melanie Franklin in New Orleans but has worked for Iran's state TV network for 25 years now.
Hossein Hashemi told The Associated Press that his mother lives in Tehran, the capital of Iran, and comes back to this country about once a year to see her family, usually scheduling documentary work somewhere in the U.S. as well.

"No idea what's going on"

"We still have no idea what's going on," said Hossein Hashemi, a research fellow at the University of Colorado whom the AP interviewed by phone from Washington. He also said he and his siblings had been subpoenaed to appear before a grand jury.
The incident comes as Iran faces increasing criticism of its own arrests of dual citizens and other people with Western ties. Those cases have previously been used as bargaining chips in negotiations with world powers.
Federal law allows judges to order witnesses to be arrested and detained if the government can prove their testimony has extraordinary value for a criminal case and that they would be a flight risk and unlikely to respond to a subpoena. The statute generally requires those witnesses to be promptly released once they are deposed, however.
She apparently was unable to call her daughter until Tuesday night. The family is trying to hire an attorney, but it has been difficult because she has not been charged with a crime, her son said.

Hashemi's detention and the material witness law

Hashemi, an American citizen, had not been contacted by the FBI before she was detained and would "absolutely" have been willing to cooperate with the agency, her son said.
Asked whether his mother had been involved in any criminal activity or knew anyone who might be implicated in a crime, Hossein Hashemi said, "We don't have any information along those lines."
Iran US Journalist Detained
Hossein Hashemi, from Denver, son of American-born news anchor Marzieh Hashemi, who works for Iranian state television, speaks during an interview with the Associated Press in Washington, Jan. 16, 2019.  AP
Hashemi said his mother was arrested as she was about to board a flight from St. Louis to Denver. A spokesman for St. Louis Lambert International Airport declined to comment and referred questions to the FBI.
The constitutionality of the material witness law has "never been meaningfully tested," said Ricardo J. Bascuas, a professor at the University of Miami School of Law. "The government only relies on it when they need a reason to arrest somebody but they don't have one."
No matter the reason for Marzieh Hashemi's detention, she should have been granted a court appearance by now, Bascuas said.

Iran uses case to blast U.S. justice

Iran's state broadcaster held a news conference and launched a hashtag campaign for Hashemi, using the same techniques families with loved ones held in the Islamic Republic use to highlight their cases.
"We will not spare any legal action" to help her, said Paiman Jebeli, deputy chief of Iran's state IRIB broadcaster. Iran's Press TV aired footage of her anchoring news programs and discussing the war in Syria, set to dramatic music.
There were no references to any case against Hashemi in U.S. federal courts, nor in Missouri.
Iranian Foreign Ministry spokesman Bahram Ghasemi told state TV that Hashemi's arrest showed the "apartheid and racist policy" of the Trump administration. "We hope that the innocent person will be released without any condition," he said.

Americans held in Iran

At least four American citizens are being held in Iran, including Michael White, a U.S. Navy veteran whose detention was only confirmed last month. Also held are Iranian-American Siamak Namazi and his 82-year-old father, Baquer, both serving 10-year sentences on espionage charges.
Iranian-American art dealer Karan Vafadari and his Iranian wife, Afarin Neyssari, received 27-year and 16-year prison sentences, respectively. Chinese-American graduate student Xiyue Wang was sentenced to 10 year in prison.
Also in an Iranian prison is Nizar Zakka, a permanent U.S. resident from Lebanon who advocated for internet freedom and has done work for the U.S. government. He was sentenced to 10 years on espionage-related charges.
Former FBI agent Robert Levinson, who vanished in Iran in 2007 while on an unauthorized CIA mission, remains missing as well. Iran says that Levinson is not in the country and that it has no further information about him. His family holds Tehran responsible for his disappearance.

Wednesday, January 16, 2019

የወልዲያ ከተማ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ወጣቶች የታቦታት ማረፊያ ቦታዎችን የማፅዳት እና የማስዋብ ስራ ሰርተዋል




ሙስሊሞቹ አንድነታቸውን ወልድያ ላይ በተግባር አሳዩ፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 10/2011 ዓ.ም(አብመድ) የወልዲያ ከተማ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ወጣቶች የታቦታት ማረፊያ ቦታዎችን የማፅዳት እና የማስዋብ ስራ ሰርተዋል፡፡ በሰላም እና በድምቀት እንዲከበር እንደሚያግዙም ተናግረዋል ሙስሊም ወጣቶቹ፡፡


በወልዲያ ከተማ የጥምቀትን በዓል በሰላም እና በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል፡፡ የወልዲያ ከተማ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ወጣቶች ዛሬ ጠዋት የታቦታቱን ማለፍያ እና ማረፍያ ቦታዎች የማፅዳት እና የማስዋብ ስራ ሰርተዋል፡፡ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ወጣቶቹ የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ እና ከተማዋ ለምዕመናኑ ምቹ እንድትሆን እንደሚሰሩ ነው የተናገሩት፡፡

ሌሎች ወጣቶችም ዘጠኝ ታቦታት የሚያልፉባቸውን መንገዶች አጽድተዋል፤ አስውበዋልም፡፡

የወልዲያ ከተማ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ መላከፅሐይ አማረ ጌጡ ‹‹የአሁኑ ወጣቶች የቀደምት የእስልምና እና የክርስትና ኃይማኖቶች ተከታይ አባቶች ሲያደርጉት የነበረውን መከባበር በተግባር በማሳየታቸው ምስጋና ይገባችኋል፤ የአባቶቻችሁን ትውፊት በመጠበቃችሁም ለሌሎች አርአያ ያደርጋችኋል›› ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ባለ ዓለምዬ- ከወልድያ

በምዕራብ ኦሮሚያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው


በምዕራብ ኦሮሚያ በወለጋ የተለያዩ ዞኖች 18 ባንኮችን በመዝረፍ፣መንገድ በመዝጋትና ንብረት በማቃጠል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ባለፉት 6 ወራት በሕገወጥ መንገድ አዲስ አበባ የገቡ ከ2ሺ በላይ የጦር መሳሪያዎች እንዲሁም 70 ሚሊየን ያህል የኢትዮጵያ ብርና ከመቶ ሺ ዶላር በላይ የውጭ ገንዘብ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተመልክቷል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ በወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች መሳሪያ አነስተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተዋጊዎች በከተሞች ጭምር ችግር መፍጠራቸው ሲገለጽ ቆይቷል።
መንግስት ችግሩን በንግግር ለመፍታት ከኦነግ ጋር ያደረኩት ጥረት አልተሳካም ማለቱን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ስፍራው ተንቀሳቅሷል።
የመንግስት ሃይሎች ይዞታቸውን እያሰፉ መሄዳቸውን ተከትሎ መከላከያ ሰራዊቱ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች 18 የመንግስትና የግል ባንኮች መዘረፋቸው ይፋ ሆኗል።
ድርጊቱ በኦነግ ታጣቂዎች እንደተፈጸመ ቢገለጽም ኦነግ ዘረፋውን አልፈጸምኩም ሲል አስተባብሏል።
ባንክ የዘረፉት ታጣቂዎች ንብረት ጭምር በማውደም እንዲሁም መከላከያ ሰራዊቱ እንዳይከተላቸው አስፋልት መንገድ በመቁረጥ ተጨማሪ ጉዳት ማድረሳቸው ይፋ ሆኗል።
መንግስት እነዚህን ባንክ የዘረፉና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦችን በሕዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር እያዋላቸው መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
የተዘረፈውን ገንዘብ ስለመመለሱ ግን የተገለጸ ነገር የለም።
መንግስት ከዘረፋውና ከሕገወጥ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎችን በማሰር ላይ መሆኑ ተገልጿል።
ከታሳሪዎቹ ውስጥ የኦዴፓ አባላት የሆኑ የአካባቢው ባለስልጣናት እንደሚገኙበትም ሪፖርቶቹ አመልክተዋል።
18ቱ ባንኮች የተዘረፉት በጠቅላላ በወለጋ ውስጥ እንደሆነም ታውቋል።
በጉጂ ዞን ሲንቀሳቀስ የነበረው የኦነግ ሃይል ከነመሪው በአባገዳዎች ጥሪ ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሱን ትላንት መዘገባችን ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በሃገሪቱ ውስጥ የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ ህገወጥ የጦር መሳሪያና ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ተበራክቷል።
በዚህም ባለፉት 6 ወራት ከሐምሌ 1/2010 እስከ ታህሳስ 30/2011 2 ሺ 383 የጦር መሳሪያ አዲስ አበባ ላይ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
ከመሳሪያዎቹ ውስጥ 2 ቦምብና አንድ መትረየስ እንደሚገኙበትም ተመልክቷል።
ከዚህም በተጨማሪ 68 ሚሊየን 322ሺ 344 ብር እንዲሁም 88ሺ 151 የአሜሪካን ዶላር በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
በተጨማሪም 9 ሺ 480 ዩሮ፣12 ሺ 620 ፓውንድና የሌሎች ሀገራት ገንዘቦችም በተመሳሳይ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተመልክቷል።
ከዚህም በተጨማሪ 163 ሺ 600 የሃሰተኛ ብር ኖቶች እንደተያዙም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ሪፖርት መረዳት ተችሏል።

የአማራና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ሰላም ለማምጣት እንሰራለን አሉ


 የአማራና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የሁለቱ ክልል ሕዝብ ወደ ግጭት እንዳይገባ እንደሚሰሩ በሃይማኖት አባቶችና በሃገር ሽማግሌዎች ፊት ቃል ገቡ።
የአማራና የትግራይ ክልል ህዝብ አንዱ ለአንዱ ስጋት ሳይሆን አንዱ በሌላው እየኮራ ተከባብሮ የሚኖርበት ታሪክ ነበረው ሲሉ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገልጸዋል።

የአማራና የትግራይ ህዝብ በመካከላቸው ችግር የለም ችግሩ ያለው እኛ ፖለቲከኞቹ ዘንድ ነው ያሉት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የፖለቲካ ልዩነት ሰላማችንን እንዲያውከው አንፈቅድም ሲሉም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ባደረጉት ጥሪና ተማጽኖ አዲስ አበባ ላይ ተገኝተው የጋራ መግለጫ የሰጡት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ችግራቸውን በውይይት ለመፍታትም ቃል ገብተዋል።
“የአማራ ህዝብ የተለያዩ አጀንዳዎች አሉት እነዚህ አጀንዳዎቹ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እንጂ ከወንድሙ ከትግራይ ህዝብ ጋር እንዲጋጭ አንፈልግም “ በማለት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሲገልጹ።
ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው በአማራ ላይ ምንም የምናነሳው ጥያቄ የለም ብለዋል።
የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው ወገኖች ሊያበጣብጡን ነው የሚሞክሩት ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የወሰንን ጉዳይ በተመለከተ እንኳን የውስጣችንን የውጭ ሃገር መፍታት ይቻላል ሲሉም ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሁለቱ ክልል ፕሬዝዳንቶች በጋራ የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ የሃይማኖት አባቶቹና የሃገር ሽማግሌዎች ሁለቱን የክልል መሪዎች አመስግነዋል።
አርአያነት ያለው ተግባር ፈጽማችኋል ሲሉም አሞግሰዋል።

Tuesday, January 15, 2019

Concern over increasing violence in Amhara region




The council of the Amhara regional government says the security situation in the region has gotten worse and resulted in the loss of several lives and destruction of properties.
The statement by the council said western and central Gondar are areas that have specially been beset by deadly violence as a result of conflict between the Qimant and Amhara groups. The council blamed third parties for fomenting clashes between the two groups but did not identify them by name.
The regional government said security forces have been given orders to swing into action to stop ongoing violence in the region that has seriously affected the day-to-day lives of peaceful citizens.
The availability of massive number of illegal weapons in the hands of many has also been a real concern to the safety of the people, the council said, and added that those who use weapons for their ill intent would be prosecuted to the fullest extent of the law.
Recent spate of deadly violence between the Qimant and Amhara groups in Gondar has resulted in loss of lives. Several people were also injured while hundreds of houses set on fire, according to reports filed by ESAT stringers.

Sunday, January 13, 2019

በጣና በለስ ከሦስት ሺህ በላይ ሰዎች ለከፋ ረሀብ መጋለጣቸው ተሰማ

)በጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት ሳቢያ ከሦስት ሺህ በላይ ሰዎች ለከፋ ረሀብ መጋለጣቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።
በምትክ መልክ የተሰጣቸው የእርሻ መሬትም ከመኖሪያቸው 60 ኪሎ ሜትር በመራቁ በእጅጉ መቸገራቸውን አስታወቀዋል።
ፋይል

በጣና በለሰ ይሰራሉ የተባሉት ስኳር ፋብሪካዎችም እስካሁን ባለመጠናቀቃቸው ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸው መገለጹ ይታወሳል።
በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ በጣና በለስ ተፋሰስ ወስጥ ከስምንት ዓመታት በፊት አካባቢው ለስኳር ልማት በመፈለጉና ከልማቱ ተጠቃሚዎች  ትሆናላችሁ በሚል  ለነዋሪዎቹ ተስፋን በመስጠት እንዲነሱ መደረጉን አስተያየታቸውን ለበኩር ጋዜጣ የሰጡ ሰዎች ተናግረዋል።
ለፕሮጀክቱ ከ70 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የተከለለ ሲሆን በፌደራል ደረጃ በስኳር ኮርፓሬሽን የበላይ ጠባቂነት ስራው ሲከናወን ቆይቷል።
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሥራውን እንዲያከናውን ኃላፊነት ቢሰጠውም ከተባለው ግብ ላይ እስካሁን አልደረሰም፡፡
ባለፈት 7 አመታት ለስኳር ልማት ተተከለ የተባለው ሸንኮራ አገዳም ከጥቅም ውጭ በመሆኑ ከ 7 ቢሊየን ብር በላይ የተፈጥሮ ስኳር ሳይመረት ባክኗል።
የተበላሸውን ሸንኮራ አገዳ ለማስወገድም ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ አስወጥቷል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከነበራቸው ይዞታ በልማቱ ምክንያት ከተደላደለ ኑሯቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ለከፋ ርሀብ  ተጋልጠዋል ነው የተባለው።
ሰሞኑን በአካባቢው የተገኙት የበኩር ጋዜጣ ባልደረቦች  በስኳር ፕሮጀክቱ ምክንያት የተፈናቀሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ራሳቸውን መመገብ አቅቷቸዋል ብለዋል።
በዚህም የስኳር ልማት ፕሮጀክቱና ነዋሪው ሆድና ጀርባ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡
የተሰጣቸው ምትክ የእርሻ መሬት እስከ ሁለት ቀን ድረስ የሚያስኬድ በመሆኑ በረሃብ ምክንያት ውድ ህይወታቸውን እስከመነጠቅ የደረሱ እንዳሉም የጋዜጣው ዘገባ አስረድቷል፡፡
ችግሩን በሚመለከት ቅሬታ ሲያቀርቡም ፀረ-ልማት በማለት እንደሚያሸማቅቋቸው ያስረዳሉ፡፡
በስኳር ፕሮጀክቱ ምክንያት ከመሬታቸው የተነሱ ነዋሪዎች በሚኖሩበት አልኩራንድ ቀበሌ በዕድሜ የገፉ ነዋሪዎች ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር የተወሰኑት ነዋሪዎች ምትክ የእርሻ መሬት አልተሰጣቸውም፤ የእንስሳት የግጦሽ ቦታም አላገኙም፡፡
ይህን በተመለከተ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊና በነዋሪዎቹ ላይ የተከሰተውን ችግር የሚያጠናው ቡድን አባል አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ሶስት ሺህ 200 ሰዎች ራሳቸውን መመገብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አረጋገጠዋል፡፡
የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ በበኩሉ የተነሳውን ቅሬታ ትክክል ነው ብሏል፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መለሰ ዳምጤ የልማቱ ተነሽዎች “60 ኪሎ ሜትር ነው ለማረስ የሚሄዱት፤ አፈናቅሎ ማቋቋም ተገቢ አይደለም፡፡
መንገድ፣ ውኃ፣ መብራትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች መሟላት ነበረባቸው” ነው ያሉት፡፡
በወቅቱ ጥናቱ ሲካሄድ መሰረተ ልማቶች እንደሚሟሉ ታሳቢ መደረጉን ያስታወሱት አቶ መለሰ “በተግባር ሲታይ ግን በጥናቱ መሰረት አልተከናወነም”ብለዋል።
አቶ መለሰ “የስኳር ልማት ኮርፓሬሽን የአመራር ደካማነት ለዚህ ውድቀት አብቅቶናል” ብለዋል፡፡
ፈንድቃ ከተማ አካባቢ ለቱርኮች ተሰጥቶ የነበረ ሁለት ሺህ 500 ሄክታር እና ለባለሀብቶች ደግሞ 900 ሄክታር መሬት ባለመልማቱ መመለሱን ምክትል ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
በመሆኑም ምትክ መሬት ላልተሰጣቸውና ቅሬታ ላላቸው ተነሽዎች ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን አቶ መለሰ ተናግረዋል፡፡

Saturday, January 12, 2019

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአፍሪካ አህጉር ታሪክ የሰሩ ተባሉ

እየተገባደድ ባለው 2018 በአፍሪካ አህጉር ታሪክን ከሰሩ ሰዎች የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግንባር ቀደም መሆናቸውን ቢቢሲ ዘገበ። ጋናዊቷ ጋዜጠኛ ኤልዛቤት ኦህኒ ዛሬ ቢቢሲ ላይ ባቀረበችው ዘገባ ዶክተር አብይ አህመድ ጸሃይን በምዕራብ የማውጣት ያህል አይቻልም የተባለውን በአጭር ጊዜ ከውነዋል በማለት ምስክርነቷን ሰጥታለች።

በለየለት አምባገነን ስርዓት የምትተቻቸውንና ከኤርትራ ጋር በፍጹም ጠላትነት ውስጥ የቆየችውን ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደሌላ ምዕራፍ ወስደዋል ስትል በጽሁፏ አስፍራለች።
ጋናዊቷ ኤልዛቤት ኦህኔ በአፍሪካ በዕድሜ ትንሹ የሃገር መሪ የ42 ዓመቱ አብይ አህመድ በማለት የጠቀሰቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስለሚከውኗቸው ተግባራትና እንዴት እንደሚከወኑም አስቀድሞ ለመገመት አይቻልም ብላለች።
በለየለት አምባገነን ስርዓት በምትተቸው ኢትዮጵያ በሚያዚያ ወር ወደ ስልጣን የወጡት አብይ አህመድ በአጭር ጊዜ ከወኑ ያለቻቸውን ውጤቶችም ዘርዝራለች።
የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በማንሳት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት እንዲሁም የመብት ተሟጋቾች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ በማድረግ የተዘጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ድረገጾችንና ቴሌቭዥን ጣቢያዎችን በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ በመፍቀድ ተገኙ ያለቻቸውን ውጤቶች ዘርዝራለች።
በሃገር ውስጥ እየተከናወነ ባለው የለውጥ ሁኔታ ህዝቡ እየተደመመ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ጸሃይ በምዕራብ እንድትወጣ የማድረግ ያህል የማይቻለውን የኤርትራን ጉዳይ በአጭር ጊዜ ዕልባት ማስገኘታቸውን ቢቢሲ ላይ ዛሬ በቀረበው ጽሁፏ ዘርዝራለች።
በጥቂት የአውሮፕላን በረራና የስልክ ግኑኝነት ከኤርትራ ጋር ሰላም ወርዶ ጤናማ ግንኙነት መጀመሩንም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የስኬት ጉዞ ነው ስትል ገልጻለች።
ሴቶችን ወደ ስልጣን በማምጣት ረገድ ጉልህ ርምጃዎች መታየታቸውን ዘርዝራለች።
የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የሚኒስትሮቹ ቁጥር በግማሽ ሴቶች መሆናቸውን ጠቅሳለች።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ፣ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርትኳን ሚደቅሳ የመንግስት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ሁሉም እንስቶች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የስልጣን ዘመን ወደ ሃላፊነት መውጣታቸውን ጽፋለች።
አምና በሙስና ከስልጣን በወረዱት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ምትክ ሲሪል ራምፎሳ ወደ ስልጣን መምጣታቸው በአፍሪካ ሌላው ትልቅ ክስተት ነው ያለችው ኤልዛቤት ኦህኔ የቀድሞ የተባበሩት መንግስት ዋና ጸሃፊ ኮፊ አናን ህልፈትና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አፍሪካውያንን ውዳቂ ሲሉ መጥራታቸው በጉልህ ክስተትነት ተዘርዝሮ በጽሁፍ ውስጥ ተካቷል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የመጣውን ለውጥ በተመለከተ ታላላቅ የምዕራብ ሚዲያዎች ዋሽንግተን ፖስት፣ ኢኮኖሚስት፣ ብሉምበርግ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ርምጃዎቹን በማድነቅና ስጋቶቹን በመጠቆም ጽሁፍ አቅርበዋል።

Friday, January 11, 2019

በኢትዮጵያ የተከሰተው የለውጥ ሂደት ስጋቶችንም ያዘለ ነው ተባለ



በኢትዮጵያ የተከሰተው የለውጥ ሂደት ተስፋን ይዞ የመምጣቱን ያህል በተቃራኒው ስጋቶችንም ያዘለ እንደሆነ በአፅንኦት መገምገሙን የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ኢሕአዴግ በመግለጫው እንዳለው ለዉጡ አሁንም ህዝባዊ መሰረት ይዞ በኢህአዴግ እየተመራ ያለ ቢሆንም በፀረ ለውጥ አስተሳሰብ አራማጆች በተቀናጀ መንገድ እየተመሩ ተግዳሮት እየፈጠሩ ናቸው።

የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ላለፉት 3 ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በድርጅቱ ውስጥም ሆነ በለዉጡ ሂደት የተሟላ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት የለም።
የታችኛው መዋቅርም ለውጡን በተሟላ መልኩ አለመደገፉ እና በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ያሉ የአካሄድ ዝንፈቶችና የእርስ በርስ መጠራጠር በግልፅ ተነስተው ትግል ተደርጎባቸዋል ብሏል።
እናም እነዚህን ችግርች በቀጣይ እንዲስተካከሉ ለማድረግና ለውጡን ለማስቀጠል የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላቱ  መግባባት ላይ መድረሳቸውን መግለጫው አመልክቷል ።
መግለጫው እንዳለው ከለውጡ በተቃራኒ ያሉ ሃይሎች ህዝቡን ለማደናገርና ድጋፍ ለማግኘት እንዲያመቻቸው ለውጡን ተከትሎ ያሉ የአመራር ግድፈቶችን፤ እንዲሁም ማንነትንና ሌሎች አጀንዳዎችን ምክንያት በማድረግ ፅንፈኛ አካሄድ እየተከተሉ ናቸው።
የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈፀም ሲሉም በዜጎች ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስና ዜጎች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረጉ ናቸው ሲልም ወንጅሏል።
የለውጡ አደናቃፊ ሃይሎች በህገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር በመታገዝ ግጭትና መፈናቀል እንዲፈጠር፣ ኮንትሮባንድና ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር በመሰሉ የኢኮኖሚ አሻጥሮች በመሳተፍ ለውጡን ለመግታት እየተረባረቡ እንደሚገኙም ገምግሟል።
አንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ፅንፈኝነትን በመስበክ የቆየውን የህዝቦች አንድነት በመሸርሸርና የህግ የበላይነትን ባለማክበር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ነው ያለው።
እናም ከዚህ ተግባራቸው በመቆጠብ በሃሳብ ልዕልና እና በውይይት ለመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ መጎልበት ገንቢ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።
በሀገሪቱ አሁን ላይ ጎልተው የሚታዩት ተግዳሮቶች የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ችግር፣ የስራ ተልዕኮ አፈፃፀም መዳከም እና በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ እሴት መታጣት መሆናቸውን የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስምሮበታል።
የመገናኛ ብዙሃንም የህዝቦች አንድነት የሚያጠናከርበትንና የተሻለች ሀገርን ለመገንባት የሚያስችል አተያይ በመፍጠር በኩል ተዓማኒነታቸውን የሚፈታተን የስርጭት ችግር እንዳለባቸው ኮሚቴው ገምግሟል።
ለዉጡ ያስፈለገው በትናንቱ ለመቆዘም ሳይሆን ወደፊት ለመወንጨፍ ቢሆንም ሚዲያው የህዝቡን አተያይ በመቅረፅ ረገድ ግን ብዙ ይቀረዋል ብሏል- የኢሕአዴግ መግለጫ።
በተለይ ደግሞ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃኑ አሉታዊ ሚናው እየጎላ መምጣቱን ገምግሞ ከለውጡ ጋር በተዛመደ መልኩ የሚታረምበትን አካሄድ መከተል እንደሚገባ አመላክቷል።
በኢኮኖሚው መስክ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ  መኖሩን የገለጸው ኢሕአዴግ ይህም  ከፍተኛ የስራ አጥነት፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት፣ የብድር ጫና ማስከተሉንና አሁንም መዋቅራዊ ችግሩ ያልተፈታ መሆኑንም ገምግሟል።

Wednesday, January 9, 2019

ኦነግ የአየር ድብደባ ተፈጽሞብኛል አለ


 በምዕራብ ኦሮሚያ ምንም አይነት የአየር ድብደባ አለተፈጸመም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ያወጣውን መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አስተባበለ።
በቄለም ወለጋ ዞን ለሁለት ተከታታይ ቀናት የአየር ድብደባ ተፈጽሟል ሲል ኦነግ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በትናንትናው ዕለት  በቃል-አቀባዩ ብልለኒ ስዩም በኩል በምዕራብ ኦሮሚያ ጦሩ ያካሄደዉን የአየር ድብደባ  የለም በሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር።
ይህም ሆኖ ግን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) መግለጫው እጅጉን ከእዉነት የራቀ ነዉ ሲል የማስተባበያ መግለጫ አውጥቶታል።
ይህ የአየር ድብደባ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ጥር 4 እና ጥር 5 /2011 ዓም በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሚ ወረዳ በቄለም ከተማና አካባቢዋ በሶስት የተለያዩ ቦታዎች ለይ ተካሂዷል ብሏል።
በዚህ ደረጃ የተካሄደዉን የአየር ድብደባ ለመካድ መሞከር  “ግመል ሰርቆ አጎምብሶ” እንደመሄድ ይቆጠራል ብሏል ኦነግ ባወጣው መግለጫ።
ከዚሁ የአየር ድብደባ በተጨማሪም የኢሕአዴግ እግረኛ ጦር ሠራዊት በዚሁ አካባቢ ሰላማዊዉን ሕዝብ በመግደል፣ መኖሪያ ቤቶቹን በማቃጠል፣ ንግድ ቤቶቹን በማፈራረስና ንብረት በመዝረፍ እንዲሁም ሰዎችን በጅምላ በማሰርና በማሰቃየት እኩይ ድርጊቶች ፈጽሟል ሲል ክስ አቅርቧል።
እንደ ኦነግ መግለጫ በጊዳሚ ወረዳ ዉስጥ በአየር ሃይልና በእግረኛ ጦር በተካሄደዉ በዚህ ጥቃት እስካሁን  የሰባት  ሰላማዊ  ዜጎች ሕይወት አልፏል፣ 8  መኖሪያ ቤቶች በእሳት ሲጋዩ 20 የንግድ ቤቶችም በኢሕአዴግ ወታደሮች ተዘርፈው ፈራርሰዋል ነው ያለው።
እነዚህ በጊዳሚ ወረዳ ዉስጥ የአየር ጥቃቱ በተካሄደበት ኣካባቢ ብቻ የተፈጸሙ ናቸዉ።
ግድያና ጦርነት እየተካሄደባቸዉ ባሉት በአራቱ የወለጋ ዞኖችም በነዚሁ የኢሕአዴግ ወታደሮች የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች፣ የተቃጠሉ ቤቶች፣ የተዘረፉና የወደሙ ንብረቶች በርካታ ሲሆኑ ለወደፊቱ ተጣርተው ይቀርባሉም ብሏል መግለጫው ።

Tuesday, January 8, 2019

የኢራኑ ፕረስ ቲቪ ጋዜጠኛ በቁጥጥር ስር ዋለች


የኢራኑ ፕረስ ቲቪ ጋዜጠኛ በቁጥጥር ስር መዋሏን የቴሌቭዥን ጣቢያው አስታወቀ።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ርምጃውን አውግዟል።

ዕሁድ ዕለት በሴንት ሉዊስ ከተማ ሴንት ሉዊስ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በቁጥጥር ስር የዋለችው የ59 ዓመቷ አሜሪካዊት ማርዚ ሐሺሚ በምን ምክንያት እንደታሰረች አልታወቀም።
በትውልድ አሜሪካዊት የሆነችውና ዕምነቷን ወደ እስልምና ከመቀየሯ በፊት ሜላት ፍራንክሊን በመባል የምትታወቀው ማርዚ ሐሺሚ ለአራት መንግስታዊ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ፕሮግራም ውስጥ በመሳተፍ ላይ ትገኛለች።
ቤተሰቿን ለመጎብኘት ከቴህራን ወደ ሴይንት ሉዊስ ያቀናችው ማርዚ ሐሽሚ ሴንት ሉዊስ አውሮፕላን ማረፊያ ከተያዘች በኋላ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ወህኒ መዛወሯ ተመልክቷል።
የምትሰራበት የኢራኑ ፕሬስ ቴቪን ጠቅሶ አልጀዚራ እንደዘገበው የ59 ዓመቷ ማርዚ ሐሽሚ ከተያዘችበት ግዜ ጀምሮ ከቤተሰቦቿ ጋር እንድትገናኝ አልተፈቀደም ሆኖም ከሁለት ቀናት በኋላ ልጇን እንድታገኝ ተደርጓል።
ጋዜጠኛዋ በካቴና እና በሰንሰለት መታጠሯን ለልጇ የገለጸች ሲሆን እያስተናገዱኝ ያሉት እንደወንጀለኛ ነው ማለቷም ተመልክቷል።
ከእሁድ ጀምሮ በእስር ቤት ስትቆይ በእስልምና የማይፈቀደው የአሳማ ስጋ እንደቀረበላትና በዚህም ሳቢያ ደረቅ ምግቦችን ብቻ ለመብላት መገደዷን ከዘገባው መረዳት ተችሏል።
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የጋዜጠኛዋን እስርና አያያዟን በማውገዝ መግለጫ ሰጥቷል

Sunday, January 6, 2019

በቅማንትና በአማራ ህዝብ መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች ተገደሉ


(ኢሳት ዲሲ–ጥር 6/2011) በቅማንትና በአማራ ህዝብ መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ።
ባለፉት ሁለት ቀናት ሽንፋ በተባለ የመተማ ወረዳ አካባቢ ሁለቱ ወገኖች ከፍተኛ ሰብዓዊ ጥፋት ካደረሰ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ለኢሳት ገልጸዋል።

ሃላፊው አቶ አሰማህኝ አስረስ የሁለቱ ወገኖች ግጭት በሶስተኛ ወገን የተጠነሰሰና እንዲባባስ የሚደረግ ነው ብለዋል።
ይህን በስም ያልጠቀሱትን ሶስተኛ ወገን እጁን ክልሉን ከማተራመስ እንዲቆጠብ ጠይቀዋል።
የቅማንትና የአማራ ህዝቦችም የዘመናት አብሮነታቸውን በደም እንዳይጨቀይ የሚችሉትን ትዕግስት በመውስድ ራሳቸውን ለሌላ ወገን መጠቀሚያ ከማድረግ እንዲርቁ ጥሪ አድርገዋል።
በቅማንትና አማራ ህዝብ መካከል የተፈጠረው ግጭት የሁለቱም ወገኖች ፍላጎት ባለመሆኑ እጁን ያስገባው አካል ከድርጊቱ እንዲቆጠብ የአማራ ክልል መንግስት አስታወቋል።
የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አሰማህኝ አስረስ ለኢሳት እንደገለጹት የቅማንትና የአማራ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ያልነበረ ቅራኔ በመፍጠር፣ በመሳሪያና በገንዘብ በመደገፍ ግጭቱ የከፋ መልክ እንዲይዝ ያደረገው አካል በአስቸኳይ እጁን ሊሰበስብ ይገባል ብለዋል።
አቶ አሰማህኝ እጁን አስገብቷል ያሉትን አካል በስም ከመጥቀስ የተቆጠቡ ሲሆን በተደጋጋሚ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ የተገለጸለት መሆኑን ነገር ግን የአማራ ክልልን ለማመስ ካለው እቅድ የተነሳ በእኩይ ተግባሩ መቀጠሉን ገልጸዋል።
በቅማንትና በአማራ ህዝብ መካከል የተጀመረው ግጭት ከሰሞኑ መበርታቱንና በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ገልጸዋል።
የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር ለመግለጽ የሚቻልበት ሁኔታ የለም ያሉት ሃላፊው አቶ አሰማህኝ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውንና ንብረት መውደሙን ገልጸዋል።
ባለፉት ሁለት ቀናት በሽንፋና ገንዳውሃ አካባቢዎች በሁለቱ ወገኖች መካከል የከረረ ግጭት እንደነበርም ሃላፊው ለኢሳት በሰጡት ቃለመጠይቅ ላይ አስታውቀዋል። ዛሬ አንጻራዊ የሆነ ሰላም መኖሩንም ጭምር።
የተከሰተውን ግጭት ለማብረድ የአማራ ክልል መንግስት የጸጥታ ሃይሉን በማሰማራት ሁኔታውን በመቆጣጠር ላይ መሆኑን አቶ አሳማሀኝ አስረስ ገልጸዋል።
የቅማንትና የአማራ ህዝቦች ያነሱትን መሳሪያ እንዲያስቀምጡ ጥሪ ያደረጉት አቶ አሰማህኝ የዘመናት አብሮነትን ለሌላ ቡድን መጠቀሚያ በማድረግ እንዳይሸረሽሩት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወደ ገንዳውሃ ያመሩት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም በጉዳዩ ዙሪያ ከአካባቢው ህዝብ ጋር ተወያይተዋል ብለዋል።

Tuesday, January 1, 2019

በአሜሪካ ኒዮርክ የሚገኘው ክላርሰን ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ታታሪ ውሻ የክብር ዲፕሎማ ሰጠ !

ክላርሰን ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ታታሪ ውሻ የክብር ዲፕሎማ ሰጠ !
.
በአሜሪካ ኒዮርክ የሚገኘው ክላርሰን ዩንቨርሲቲ ለአንድ ታታሪ ውሻ የክብር ዲፕሎማ ሰጥቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የክብር ዲፕሎማውን የሰጠሁት ውሻው በግቢው ውስጥ ለአንድ አካል ጉዳተኛ ተማሪ ያደረገውን ድጋፍ በማድነቅ ነው ብሏል፡፡
.
ብሪታኒ ለተባለችው ተማሪ ውሻው ያደረገው እርዳታ ፍቅርና እንክብካቤ ዩኒቨርስቲውን ማስገረሙ ተነግሯል ፡፡ ዩፒአይ እንዳስነበበው ክላርሰን ዩኒቨርስቲ ግሪፊን ለተባለው ውሻ በዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አማካይነት የመመረቂያ ቆብና ጋውን በማልበስ እንዲሁም ስርተፍኬት በመስጠት የክብር ዲፕሎማውን አበርክቷል ፡፡
.
እናም ወዳጆቼ ግሪፊን የተባለው ውሻ ለአሳዳጊው የሰጠው ፍቅርና እንክብካቤ እኛ ሰዎች ለወገኖቻችን አብልጠን እንድንሰጥ ፈጣሪ ልቦናችንን ያብራልን ፤ አሜን !!

wanted officials