ለገሠ ወ/ሃና
የወልቃይት የአማራ ማንነት እና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ኮሚቴው ያለፈበትን አድካሚ ጉዞ እና ቀጣይ ለመስራት ያሰበውን የኮሚቴው አባላት አቶ አታላይ ዛፌ ፣ አቶ ጌታቸው አደመ ፣ መቶ አለቃ ደጀኔ ማሩ … በዝርዝር ለተሰብሳቢው አቅርበዋል ።
በመቀጠል የኮሚቴው አማካሪ እና ከወልቃይት ጋር በተያያዘ ታስረው ለነበሩ የኮሚቴው አባላት እና ለሌሎች በነጻ ሳይቀር ጥብቅና የሚቆሙት ጠበቃና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አለልኝ ምህረቱ ወልቃይት እና ሌሎች ከአማራ የተወሰዱ መሬቶችን ከህግ አንጻር ህጋዊ መሠረት የሌለው ንጥቂያ እንደሆነ በሰፊው አቅርበዋል ።
በመቀጠል ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት አቶ ውብሸት ሙላቱ ናቸው::
አቶ ውብሸት በርካታ የታሪክ ድርሳናትን እያጣቀሱ በማንበብ ወልቃይትም ሆነ ሌሎቹ የማንነት ጥያቄ የተነሳባቸው አካባቢዎች የአማራ ህዝብ ርስቶች መሆናቸውን የተወሰዱትም በጉልበት መሆኑን በማስረጃ አስደግፈው ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል ።
አቶ ውብሸት ሀገር ማለት ሰው ሳይሆን ሀገር ማለት መሬት መሆኑን በአሳማኝ አገላለጽ ለተሰብሳቢው አቅርበዋል ።
ከዚህ በመቀጠል የእድሜ ባለፀጋው የወልቃይት ተወላጅ ቀኛዝማች ፍትሃለው ደምሴ ዛሬ 87 ዓመት እድሜ ላይ ሆነው በአስገምጋሚ ድምጻቸው በእሳቸው እድሜ የሚያውቁትንና ከአባቶቻቸው ጀምሮ ከተገዜ ወዲህ ትግሬ ገዝቶም ኖሮም እንደማያውቅ ከተከዜ ወዲህ አይደለም ከተገዜ ማዶም ያለው መሬት በአማራ ጀግኖች ከጠላት ወራሪ ተጠብቆ የቆየ መሆኑና ወልቃይት ጠገዴ የአማራ ርስት መሆኑን አለም ያውቀዋል የዛሬው ውይይት ወልቃይት የአማራ ነው አይደለም ሳይሆን እንዴት ርስታችንን ይመለስ የሚለው ነው ጉዳዩ በማለት በሰፊው ገለጻ አድርገዋል::
ከዚህ በመቀጠል ከመድረክ በቀረበው ሀሳብ ላይ ጥያቄ ካለ እንዲቀርብ በተፈጠረው እድል ከተሰብሳቢው በርካታ ጥያቄዎች ቀርበው የኮሚቴው አባላት ለጥያቄዎቹ ማብራሪያ ሰጥጥተዋል ።
በመጨረሻም በቀድሞው አጠራር ሸዋ ክፍለሀገር በወያኔ አጠራር ሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ የተቋቋመው የአማራ ማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚት በተሰጠው እድል የኮሚቴው አባል አቶ ባሳዝነው ሞገስ ደራ ወረዳ ከዘመነ ወያኔ በፊት በአማራ አስተዳደር ስር እንደነበረ እና ህዝቡም ከ80 በመቶ በላይ አማራ እንደሆነ ገልፀው የደራ ወረዳ አዋሳኝ በምስራቅ ሚዳ እና መርሃቤቴ፣ በሰሜን ደቡብ ወሎ ወግዲ (ቦረና ሳይንት)፣ በምዕራብ ምስራቅ ጎጃም፣ በደቡብ ጀማወንዝ ይዋሰናል ይህ ሆኖ ባለበት ሁኔታ ወረዳዋ ከ1983 ዓም ወዲህ መለስ አማራ ጠል የሆነ ህገመንግስቱን እንደመሳሪያ ተጠቅሞ ለኦህደድ(ለአባዱላ ) በስጦታ መልክ የሰጣት ትንሿ ወልቃይት የሆነች ነች ብለዋል ።
በጉልበት ወደ ኦሮምያ ክልል የተካለ መሆኑንና በዚህም ምክንያት በርካት በደል ደርሶብናል በቋንቋችን እንዳንማር ተደርገናል ኦሮምኛ ባለመቻላችን ስራ በየትኛውም የመንግስት መዋቅር ውስጥ ስራ አንቀጠርም በስደት ነው ኑሯችንን እየገፋን እንገኛለን ብለዋል አቶ ባሳዝነው በሁሉም አካባቢ የተቋቋመው የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮማቴ ጥያቄዎቻችንን እንዲመለሱ በጋር መስራት አለብን በማለት ጥሪ አቅርበዋል የራያና የመተከል የአማራ ማንነት እና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በጊዜ እጥረት ምክንያት ሀሳባቸውን ማቅረብ ሳይችሉ ቀርተዋል ።
በመጨረሻም ህዝባዊ ስብሰባው ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቋል ።

No comments:
Post a Comment