Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 16, 2019

የወልዲያ ከተማ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ወጣቶች የታቦታት ማረፊያ ቦታዎችን የማፅዳት እና የማስዋብ ስራ ሰርተዋል




ሙስሊሞቹ አንድነታቸውን ወልድያ ላይ በተግባር አሳዩ፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 10/2011 ዓ.ም(አብመድ) የወልዲያ ከተማ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ወጣቶች የታቦታት ማረፊያ ቦታዎችን የማፅዳት እና የማስዋብ ስራ ሰርተዋል፡፡ በሰላም እና በድምቀት እንዲከበር እንደሚያግዙም ተናግረዋል ሙስሊም ወጣቶቹ፡፡


በወልዲያ ከተማ የጥምቀትን በዓል በሰላም እና በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል፡፡ የወልዲያ ከተማ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ወጣቶች ዛሬ ጠዋት የታቦታቱን ማለፍያ እና ማረፍያ ቦታዎች የማፅዳት እና የማስዋብ ስራ ሰርተዋል፡፡ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ወጣቶቹ የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ እና ከተማዋ ለምዕመናኑ ምቹ እንድትሆን እንደሚሰሩ ነው የተናገሩት፡፡

ሌሎች ወጣቶችም ዘጠኝ ታቦታት የሚያልፉባቸውን መንገዶች አጽድተዋል፤ አስውበዋልም፡፡

የወልዲያ ከተማ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ መላከፅሐይ አማረ ጌጡ ‹‹የአሁኑ ወጣቶች የቀደምት የእስልምና እና የክርስትና ኃይማኖቶች ተከታይ አባቶች ሲያደርጉት የነበረውን መከባበር በተግባር በማሳየታቸው ምስጋና ይገባችኋል፤ የአባቶቻችሁን ትውፊት በመጠበቃችሁም ለሌሎች አርአያ ያደርጋችኋል›› ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ባለ ዓለምዬ- ከወልድያ

No comments:

Post a Comment

wanted officials