በህንዷ ዋና ከተማ ዴልሂ ባጋጠመ የአየር ብክለት ምክንያት ሃላፊዎች የማህበረሰብ ጤና ድገተኛ አደጋ አዋጅ ለማወጅ ተገደዋል። በተጨማሪም በከተማዋ ለሚገኙ 5 ሚሊየን ተማሪዎች አፍ መሸፈኛ ማስክ ሲያከፋፍሉ ውለዋል።
በዚህ ምክንያት እስከ መጪው ማክሰኞ ድረስ ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን በዴልሂ አየር ላይ የሚገኙት በካይ ንጥረ ነገሮች የዓለማቀፉ የጤና ድርጅት ካስቀመጠው ቁጥር በ 20 እጥፍ ይበልጣል ተብሏል።
በከተማዋ የሚካሄዱ ግንባታዎችም ቢሆን ሳምንቱን በሙሉ ሲስተጓጎሉ ነበር ተብሏል። ከመኪናዎች የሚወጣውን ብክለት ለመቀነስም በጣም የተመረጡና ልዩ ፈቃድ ያላቸው መኪናዎች ብቻ በጎዳናዎች ላእ እንዲሽከረከሩ የሚያስገድድ ጊዜያዊ ሕግም ተግባራዊ ተደርጓል።
የዴልሂ ዋና አስተዳዳሪ ሚኒስትር አርቪንድ ኬጅሪዋል እንዳሉት ከተማዋ ''ወደ ጋዝ ማከማቻ ተቀይራለች።''
ለተማሪዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተከፋፈሉት 5 ሚሊየን አፍ መሸፈና ማስኮችንም ዜጎች በተቻለ መጠን ሁሌም እንዲጠቀሟቸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የዓለማቀፉ የጤና ድርጅት ባስቀመጠው መለኪያ መሰረት ጎጂ ጥቃቅን አካላቱ በአንድ ቀን ውስጥ ከ 25 ማይክሮግራሞች መብለጥ የሌለበት ሰሆን በዴልሂ ኤር ውስጥ ግን 533 ማይክሮግራሞች የበለጠ ጎጂ ንጥረነገር ወደ ሳንባ ይገባል።
አንዳንድ የመንግስትና የግል ድርጅት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸውን በቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ የተነገራቸው ሲሆን ዜጎች ከዓመት ዓመት በተመሳሳይ ችግር መጠቃታችን ተገቢ አይደለም፤ መንግስት የሆነ መፍትሄ ይፈልግ ሲሉ ምሬታቸውን በማህበራዊ ሚዲያዎች እየገለጹ ነው።
እ.አ.አ. በ2017 የህንድና የስሪላንካ የክሪኬት ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታቸውን እያደረጉ በቦታው በነበረው ከፍተኛ ብክለት ምክንያት የስሪላንካ ተጫዋቾች ሜዳ ውስጥ ሲያስመልሱ እንደነበር ይታወሳል።
በዴልሂ እንደዚህ ላስቸገረው የአየር ብክለት ምክንያት ነው የሚባለው ከወርሃ ጥቅምት እስከ ታህሳስ ድረስ በጎረቤት ግዛቶች ፑንጃብ እና ሃርያና የሚገሡ ገበሬዎች ማሳቸውን ለአዲስ የግብርና ዓመት ለማዘጋጅ በጣም ሰፋፊ እርሻዎችን ስለሚያቃጥሉ ነው ተብሏል።
No comments:
Post a Comment