ከ17 ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታውን የሆነ ነበር፤ የነርስ ልብስ የለበሰች ሴት ከጎሮቲ ሹር ሆስፒታል የሦስት ቀን ህፃንን በእቅፏ አድርጋ የወጣችው።
ህፃኗ እንቅልፍ ከጣላት እናት የተሰረቀች ነበረች። የዚያን ጊዜዋ የሦስት ቀን ህፃን የዛሬዋ የ21 ዓመት ወጣት ሁለት እናቶቿን፤ ከሆስፒታል የሰረቀቻትንና ትክክለኛ ወላጅ እናቷን ልታውቅ የቻለችው በአጋጣሚ ተነስታ በማህበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ በለጠፈቸው በሞባይሏ እራሷ ባነሳችው (ሰልፊ) ፎቶግራፍ እንደሆነ ትናገራለች።
በኬፕታውኑ ዝዋንስያክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነቸው የ21 ዓመቷ ሚቺ ሶሎሞን ማንነቷን የገለጠውን ሰልፊ ፎቶ የለጠፈችው እንደ አውሮፓዊያኑ በ2015 አዲስ የትምህርት ዓመት መጀመሩን በማስመልከት ነበር።
ሚቺ ፎቶውን እንደለጠፈች ተማሪዎች ግር ብለው መጥተው ከእሷ በሦስት ዓመት የምታንስ ነገር ግን ቁርጥ እሷን የሆነች ካሲዲ ነርስ የምትባል አዲስ ተማሪ እንዳለች ይነግሯታል።
መጀመሪያ ላይ ሚቺ ነገሩን ችላ ብትለውም አንድ ቀን ከተባለችው ልጅ ጋር አንድ ቦታ ላይ ሲተላለፉ ልተገልፀው የማትችለው ስሜት ይሰማታል።
"የማውቃት ያህል ነው የተሰማኝ ለምን እንደዛ እንደተሰማኝ አላውቅም። በጣም አስደንጋጭ አጋጣሚ ነበር" ትላለች ሚቺ ከማታውቃት እህቷ ጋር በተላለፉበት ቅፅበት የተሰማትን ስትገልፅ።
ከዚያም እህትማማቾቹ አብረው ጊዜ ማሳለፍ ጀመሩ፤ ከዚያም አንድ ላይ የተነሱትን ሰልፊ ሁለቱም ለጓደኞቻቸውና ለወላጆቻቸው አሳዩ።
አንዳንድ ጓደኞቿ ለሚቺ "ምናልባት ለወላጆችሽ የማደጎ ልጅ እንዳትሆኚ?" የሚል ጥያቄ አነሱ።
የካሲዲ ወላጆም ሚቺን መጠየቅ የሚፈልጉት ነገር እንዳለ ለልጃቸው ካሲዲ ነገሯት። ካሲዲም የተወለድሽው በዚህ ቀን በዚህ ዓመት ነው ወይ? ስትል ሚቺን ጠየቀቻት። "ፌስቡክ ላይ ስትሰልይኝ" ነበር በማለት መጀመሪያ በነገሩ በስጨት ብትልም በትክክልም በተባለው ጊዜ እንደተወለደች ሚቺ አረጋገጠች።
ከሳምንታት በኋላ ሚቺ የትምህርት ቤታቸው ዳይሬክተር ቢሮ ተጠርታ ከ17 ዓመታት በፊት በኬፕታውኑ የጎሪቲ ሆስፒታል የሦስት ቀን ህፃን መሰረቅን የሚያመለክት ታሪክ በህበራዊ ሰራተኞች ይነገራታል።
'ይህን ታሪክ ለእኔ የሚነግሩኝ ለምንድን ነው?' በሚል ግራ ስትጋባ እሷ ያቺ ህፃን ለመሆኗ ማስረጃዎች መኖራቸው ተገለፀላት።
ሚቺም የተወለደችው ሌላ ሆስፒታል እንደሆነና የልደት ሰርተፊኬቷን ማየት እንደሚቻል በመግለፅ ለመከራከር ብትሞክርም እሷ የጠቀሰችው ሆስፒታል ስለመወለዷ ሆስፒታሉ ምንም ማስረጃ እንደሌለው አስረዷት።
በመጨረሻ የዲኤንኤ ምርመራ ማድረግ ግድ ሆነ። ሚቺና ከ17 ዓመታት በፊት ከጉሪቲ ሆስፒታል ልጇ የተሰረቀችባት ዜፋኒ ነርስ (የካሲዲ እናት) ምርመራውን አደረጉ። በማያጠራጥር ሁኔታ የምርመራ ውጤታቸው አንድ አይነት ሆነ።
"ባሳደገችኝ እናቴ ላይ ትልቅ እምነት ነበረኝ። በተለይም ስለማንነቴ በፍፁም ዋሽታኝ አታውቅም ብዬ አስቤ ምርመራው በጭራሽ ሊመሳሰል አይችልም ብዬ እርግጠኛ ሆኜ ነበር" ብላ ነበር ሚቺ።
ነገሮች እንዳላሰበችው ሆነው እሷ ያሳዳጊዋ ሳትሆን በድንገት ያወቀቻት የካሲዲ እናት ልጅ ሆኗ ራሷን አገኘችው።
No comments:
Post a Comment