Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, November 4, 2019

የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው


ኳስ በጭንቅላቱ የሚመታ ልጅImage copyrightGETTY IMAGES
የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ከአንጎል ጤንነት ጋር በተያያዘ የወጣ ሪፖርትን ተከትሎ ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ እገዳ ለመጣል እያሰበ መሆኑ ተነገረ።
በግላስጎው ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ባለሙያዎች እንደደረሱበት የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንጎልን እያዳከመ ለሞት በሚያበቃ የአንጎል በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ከሦስት ጊዜ በላይ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
የስኮትላንድ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ከህክምና ባለሙያዎች ጋር ከተነጋገረ በኋላ ያሉ አማራጮች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተነግሯል።
አሜሪካ ውስጥ ከአምስት ዓመት በፊት ጀምሮ ታዳጊ ህጻናት ኳስ በጭንቅላታቸው እንዳይመቱ እገዳ ተጥሏል።
በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በጭንቅላት (በቴስታ) ኳስ መምታት በአንጎል ደህንነት፣ በተለይም በህጻናት ላይ የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር ተከትሎ ስኮትላንድ ውስጥ ክልከላ ሊቀመጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው።
አንድ ውስጥ አዋቂ እንዳሉት "ጉዳዩ ታዳጊዎች በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ኳስ በጭንቅላታቸው የመግጨት አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን በልምምድ ወቅት በተደጋጋሚ ኳስን በጭንቅላት መምታትን ይመለከታል" ብለዋል።
የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ዋና የህክምና አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጆን ማክሊን ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ ኳስን በጭንቅላት በመምታት በታዳጊ ተጫዋቾች ላይ የሚፈጠረውን ጫና ለመቀነስ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
ዶክተሩ እንዳሉት "ከስኮትላንድና ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ጋር በመሆን ተቀባይነት ያለው መመሪያ ለማዘጋጀት ሥራ ጀምረናል። "
"ለምሳሌም ለታዳጊዎች የሚሰጠውን ኳስ በጭንቅላት የመምታት ልምምድ የተወሰነ እንዲሆንና አንጎላቸው ለማገገም እንዲችል በሳምንት የሚሰጣቸው ስልጠና አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሆን ማድረግን የመሰለ ቀላል እርምጃ ሊሆን ይችላል" ብለዋል።
የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ውስጥ አዋቂ እንዳሉት የማህበሩ አመራር ቡድን ታዳጊዎች ኳስ በጭንቅላታቸው መምታትን በተመለከተ የቀረበውን የባለሙያ አስተያየት ይደግፈዋል ብለዋል።
በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ለተደረገው ጥናት መነሻ የሆነው የቀድሞው ዌስት ብሮም አጥቂ ጄፍ አስቴል ለህልፈት የተዳረገው በተደጋጋሚ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ነው የሚል አስተያየት ከተሰነዘረ በኋላ ነው።
በ2002 (እኤአ) አስቴል ከሞተ በኋላ፣ በጥናቱ መዘግየት ቤተሰቦቹ ቁጣቸውን በመግለጻቸው፣ በእግር ኳስ ማህበሩና በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር አነሳሽነት ጥናቱ ተደርጓል።
የሟቹ እግር ኳስ ተጫዋች ሴት ልጅ የሆነችው ዳውን ጥናቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ በውጤት "እንደደነገጠች" ተናግራለች።

No comments:

Post a Comment

wanted officials