Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 2, 2019

የኩዌት ባለስልጣናት የተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሰዎችን እንደ 'ባሪያ' ሲሸጡ የነበር ያሏቸው ግለሰቦች ላይ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ ገለጹ።

ኩዌት በድረገጽ ሰዎችን ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረች

በበይነ መረብ የሚሸጡት ሴቶች

የቢቢሲ አረብኛ ክፍል የምርመራ ቡድን በዚህ ሳምንት ባስተላላፈው ዘገባ፤ እንደ ጉግል እና አፕልን የመሳሰሉ የበይነ መረብ መድረኮችን በመጠቀም ኩዌታውያን ከተለያዩ አገራት የመጡ ስደተኞችን እንደሚሸጡ ያሳያል። በፌስቡክ ስር በሚተዳረው በኢንስታግራም ጭምርም ሰዎች እንደሚሸጡ ዘገባው ያትታል።

ለሽያጭ የሚቀርቡት አብዛኛዎቹ ሴቶች ሲሆኑ፤ ለቤት ሠራተኝነት ነው የሚፈለጉት። ሻጮቹም እንደ #maids for transfer እና #maids for sale የመሳሰሉ ሀሽታጎችን በመጠቀም ሴቶቹን ለሽያጭ ያቀርቧቸዋል።
ይህንን መሰል ማስታወቂያዎችን በመጠቀም የቤት ሠራተኞችን ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች ማስታወቂያቸውን እንዲያወርዱ መታዘዛቸውንም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በዚህ ተግባር ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎች በድጋሚ እንደማይፈጽሙት የሚገልጽ ሕጋዊ ወረቀት እንዲፈርሙና መጸጸታቸውን እንዲገልጹ ተደርገዋል በማለት ስለተወሰደው እርምጃ ገልጸዋል።
ኢንስታግራም በበኩሉ ቢቢሲ ጉዳዩን ካሳወቀው በኋላ እርምጃ እንደወሰደ አስታውቋል። አክሎም ኢንስታግራምና ፌስቡክን በመጠቀም ሰዎችን ለሽያጭ ለማቅረብ የተከፈቱ ገጾችን እንደሚከታተልና እንደሚያግድ ገልጿል።
ቢቢሲ የምርመራ ዘገባውን ሲሠራ በብዛት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩት ገጾች በሙሉ በአሁኑ ሰአት እንቅስቃሴያቸው ቆሟል።

በኩዌት የሰው አቅርቦት ባለስልጣን የሆኑት ዶክተር ሙባራክ አል አዚሚ ደግሞ በምርመራ ዘገባው ላይ የታየችውን የ16 ዓመት ጊኒያዊ ታዳጊ ጉዳይን በቅርበት እንደሚከታተሉትና ጥቅም ላይ የዋለው 'ፋቱ' የተባለው መተግበሪያ ምርመራ እንደሚደረግበት ገልጸዋል።
በዘገባው የቀረበውና አንዲትን ሴት ለመሸጥ ሲስማማ የነበረው የፖሊስ አባልም ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል። ሌሎች ሰዎችም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን ተጎጂዎችም ካሳ ይከፈላቸዋል ብለዋል ባለስልጣኑ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials