Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 2, 2019

በፌስቡክ የሐሰት ዜና ለማሰራጨት ሲል ፖለቲካኛ ለመሆን ያሰበው ግለሰብ

አድሪዬል ሃምፕተንImage copyrightADRIEL HAMPTON/ WIKIMEDIA
በማህበራዊ ሚዲያዎች የሀሰት ዜና ማሰራጨት ትፈልጋላችሁ? እንግዲያውስ ፖለቲካኛ ብትሆኑ ያዋጣችኋል፤ ይላል አሜሪካዊው አክቲቪስት አድሪዬል ሃምፕተን። ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎች ላይ ፌስቡክ ያለውን አቋም መፈተሽ እፈልጋለው ብሏል አድሪዬል።
ሳንፍራንሲስኮ የሚገኘው አድሪዬል ሃምፕተን ፌስቡክ ፖለቲካዊ ቅስቀሳዎችን ምንም ማጣራት ሳያደርግ እንዲተላላፉ ይፈቅዳል፤ የሌሎች ሰዎችን መልዕክት ግን አብጠርጥሮ ይመለከታል ሲል ይከሳል።
ለሃሳቡ ማጠናከሪያ እንዲሆነው ደግሞ በ2022 ለሚካሄደው ምርጫ በካሊፎርኒያ ተፎካካሪ ለመሆን አስቧል። በዚያውም ሐሰተኛ ፖቲካዊ መልዕክቶቹን በፌስቡክ ያስተላልፋል።
''የዚህ ሃሳብ ዋነኛው ግብ ፌስቡክ በፖለቲካዊ መልዕክቶች ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር መመርመርና እንደ ዶናልድ ትራም ያሉ ፖለቲከኞች ሐሰተኛ መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ ዝም እየተባሉ ሌሎች ላይ እንዴት ቁጥጥር እንደሚደረግ ማሳየት ነው'' ብሏል አድሪዬል።
ፌስቡክ በበኩሉ ይህ ሰው ይህንን በማለቱ በራሱ ሐሰተኛ ዜና እያስተላለፈ ነው ጉዳዩንም በቀላሉ አልተወውም ብሏል።
ፌስቡክ የምትጠቀም ሴትImage copyrightPA MEDIA
ማህበራዊ ሚዲያን ከሚጠቀሙ ሰዎች መካከል 99 በመቶ የሚሆኑትን እንወክላለን የሚለው የበይነ መረብ ሊግ አባል የሆነው አድሪዬል፤ ግባችን አጥባቂ ፖለቲከኞች በማህበራዊ ሚዲያዎች እንዴት ጡንቻቸውን እንደሚጠቀሙ ማሳየትን መከላከል ነው ይላል።
''ከሩሲያ የኢንተርኔት ምርምር ኤጀንሲ እስከ ትራምፕ 'ዲጂታል ብሬይን ትረስት' ድረስ ፖለቲከኞች በማህበራዊ ሚዲያ ቀውስ በመፍጠር ነው የሚታወቁት። እኛ ደግሞ እነሱን እየተዋጋን ነው'' ይላል አድሪዬል።
አክሎም ''ማህበራዊ ሚዲያ በጣም ትልቅ አቅም አለው። ፌስቡክ በራሱ የምርጫ ሂደቶችን ማስቀየር ይችላል'' ብሏል።
የአድሪዬል ውሳኔ የፌስቡክ 200 ሰራተኞች ለዋና ሥራ አስኪያጁ ማርክ ዙከርበርግ ድርጅቱ ፖለቲካዊ መልዕክት ያላቸው ማስታወቂያዎችን በተመለከተ ስላለው ፖሊሲ ይፋዊ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ የመጣ ነው።
''ነጻ ንግግርና የተከፈለባቸው ንግግሮች እኩል አይደሉም'' ይላል ሰራተኞቹ የጻፉት ደብዳቤ። ''በፖለቲካዊ ሃላፊነቶች ላይ ያሉ ሰዎችና ለስልጣን የሚወዳደሩ ፖለቲከኞች ስለሚያስተላልፉት መልዕክት ቁጥጥር አለመደረጉ ከፌስቡክ ዓላማ ጋር ይጣረሳል'' ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አድሪዬል ሃምፕተን ለፖለቲካዊ ስልጣን እወዳደራለሁ ማለቱን ተከትሎ ፌስቡክ የመረጃ ማጣራት ካደረግኩ በኋላ ፖለቲካዊ መልዕክቶቹን አጠፋቸዋለው ብሏል። ጉዳዩ ደግሞ ወደ ፍርድ ቤት ሊያመራ እንደሚችል እየተዘገበ ነው።
የፌስቡክ ቃል አቀባይ ለሲኤንኤን በሰጡት መግለጫ ''ይህ ሰው በእኛ ፖሊሲዎች ላይ እንከን ለማግኘት ሲል እንደ አንድ የፖለቲካ ተፎካካሪ ተመዝግቧል፤ ይህ ደግሞ መልዕክቶቹን በፌስቡክ ማስታወቂያ በኩል ሊያስተላልፍ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ሌላ ሦስተኛ ወገን እንዲያጣራው እናደርጋለን'' ብለዋል።
አድሪዬል ሃምፕተን ደግሞ የእኔ ጉዳይ ተለይቶ በሦስተኛ ወገን እንዲጣራ የሚያደርጉ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፍር ቤት ለመውሰድ እያሰበ እንደሆነ አስታውቋል

No comments:

Post a Comment

wanted officials