Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, November 3, 2019

የሮናልድ ሬገን ቤተ መጻሕፍትን ከካሊፎርኒያ እሳት የታደጉት ፍየሎች


ቡናማ ፍየል
Image copyrightGETTY IMAGES
ለቀናት በሰደድ እሳት የተለበለበችው ካሊፎርኒያ ከወራት በፊትም ተመሳሳይ መጥፎ እጣ ደርሶባት ነበር።
የተራቡ 500 ፍየሎች ባይታደጉት ኖሮ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሮናልድ ሬገን ፕሬዘዳንታዊ ቤተ መጻሕፍትም ካሊፎርኒያን ካቃጠላት ሰደድ እሳት አይተርፍም ነበር።
የቤተ መጻሕፍቱ ዙሪያ ተቀጣጣይ በሆኑ ደረቅነት ባህሪ ባላቸው ተክሎች የተከበበ በመሆኑ በሰደድ እሳቱ ለመበላት የተዘጋጀ ቦታ ስለነበር ባለፈው ግንቦት ላይ የተራቡ 500 ፍየሎች እነዚህን ተክሎች እንዲበሉ ቦታው ላይ ተሰማሩ።
ፍየሎቹ ተቀጣጣይ አትክልቶቸን ለመብላት ሥራ የተሰማሩት ከአንድ ፍየል አርቢ ኩባንያ በቅጥር መልክ ነበር።
ሰደድ እሳቱ ቤተ መጻሕፍቱ ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም የተራቡት ፍየሎች ከስር ከስር ተቀጣጣይ አትክልቶቹን መብላታቸው ቦታው ላይ ለተሰማሩት የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ጊዜ ሰጣቸው።
የእሳት አደጋ ሠራተኞቹ ፍየሎች ሥራቸውን እጅግ እንዳቀለሉላቸው እንደተናገሩ የቤተ መጻሕፍቱ ሥራ አስኪያጅ ሜሊሳ ጊለር ለሮይተርስ ተናግረው ነበር።
መጀመሪያ 13 ኤክር መሬት እየበሉ ለማፅዳት የተቀጠሩት 805 ፍየሎች ነበሩ።
ፍየሎቹ የመጡበት ኩባንያ ባለቤት ስኮት ሞሪስ በአንድ ኤክር መሬት ለፍየሎቹ ስራ አንድ ሺህ ዶላር እንደሚከፈል ገልፀዋል።
ካሊፎርኒያ በሰደድ እሳት መቃጠል ከቀጠለች የፍየሎቻቸውን ቁጥር መጨመር እንደሚኖርባቸውም ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials