Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 2, 2019

ፌስቡክ ሐሰተኛ ዜናዎችን መለየት ሊጀምር ነው facebook to identify fake news

ፌስቡክImage copyrightAFP
ፌስቡክ የሚሠራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል ያለመ አዲስ ስልት ሊተገብር መሆኑን አስታወቀ።
አንጋፋው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ የሆነው ፌስቡክ፤ በመግለጫው ላይ እንዳለው በፌስቡክና በኢንስታግራም ላይ የሚሠራጩ ሐሰተኛ ዜናዎችን ሦስተኛ ወገንን በመጠቀም ጥሬ ሐቁን ሊያጠራ እንደሆነ ገልጿል።
ፌስቡክ በቅርቡ ጥሬ ሐቅ አረጋጋጭ ፕሮግራሙን ከሰሃራ በታች ባሉ 10 አገራት ያስፋፋ ሲሆን እነዚህም ኢትዮጵያ፣ ዛምቢያ፣ ሶማሊያ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኒ እና ጋና ናቸው።
የአፍሪካ ፖሊሲ ዋና ኃላፊ ኮጆ ቦክይ እንዳሉት ፕሮግራሙ እንደ አፍሪካ ቼክ፣ ፔሳ ቼክ፣ ዱባዋ፣ ፍራንስ 24 እና ኤ ኤፍ ፒ ፋክት ቼክ ካሉ አጋር ድርጅቶቻቸው ጋር በጋራ በመሆን ይተገበራል።
እነዚህ ድርጅቶች በፌስቡክ ላይ የሚሠራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመቆጣጠር በጨረታው ተሳትፈዋል።
"በፌስቡክ ላይ የሚሠራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን መዋጋት ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ሐሰተኛ ዜና ምን ያህል ችግር እንደሆነ እናውቃለን፤ በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት እነዚህ እርምጃዎች ወሳኝ ናቸው" ብለዋል ኃላፊው።
ኮጆ ቦክይ አክለውም ሦስተኛ ወገን ጥሬ ሐቅ አረጋጋጭ ብቻውን ለችግሩ መፍትሔ ባይሆንም፤ ሰዎች ፌስቡክ ላይ የሚያዩዋቸውን መረጃዎች ጥራት ለማሻሻል ከሚያከናውኗቸው በርካታ ተግባራት መካከል ይህ አንዱ ነው።
"በርካታ ሥራዎችን አከናውነናል፤ አሁንም ፌስቡክ የበርካታ ሃሳቦች መንሸራሸሪያ እንዲሆን ለማረጋጋጥ እንጂ የሀሰተኛ መረጃዎች መናሃሪያ እንዲሆን አንፈልግም" ብለዋል።።

No comments:

Post a Comment

wanted officials