የዚህ ፅሁፍ አላማ ለዶክተር አብይ ከምንቀኝለት ቅኔ የበለጠ የህወሃትን መሰሪነት ለመላው አለም የምናሳብቅበት ወቅት እንዲሆን ለማሳሳብ ነው። ብዙዎች በማርሽ ቀያሪው ዶክተር አብይና ጓዶቹ የሚነገረውን በመስማት ብቻ ለኢህአዴግ ወያኔ እጅ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።የትግራይን ክልል ለመገንጠል ወጥኖ የተቆረቆረው ህወሃት ከናዚዘረኛ ባህርዩ አንጻር ብቻ ሳይሆን ሃገር የሚበታትን ህገመንግስት ለምሳሌ አንቀፅ 38 ጋርጦብን እንዴት ከህወሃት ኢህአዴግ ጋር ሰው ስለመደመር ይስማማል። ጨለማ ከብርሃን ጋር ህብረት በፍጹም አይኖረዉም። የምንፈልገው ስር ነቀል ለውጥ ስለመሆኑ በቅድሚያ መነጋገር አያስፈልግም ወይ?ለማለት ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር የተካሄደ ያክል በማስተጋባት እየተሸወዱ ይገኛል።ጉልቻ ተለዋወጠ እንጂ ያው ወጡ ኢህአዴግ ወያኔ አሁንም በስልጣን ላይ እንደሆነ ከመንም በላይ ሰዎች ከኖሩበት ቀዬ መጤ በመባል ሰለመፈናቀላቸው ዜጎች አሁንም ሰለመታሰራቸው ወዘተ ሚዛናዊ ዜና የለም።
ሴቶች እንዳይወልዱ የሚያመክን መርፌ የሚወጉ በእስር ቤት በፍርድርቤት ወዘተ የሚዘገንን ደርጊት የሚፈጽሙ አረመኔ ማፍያዎች በሰው ዘር ፍጅት በጄኖሳይድ ክስ በአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ይቅረቡ እያልን እንዳልጮህን ሰልፍ እንዳልወጣን በአማላይ ንግግር ተማርከን እንዴት ሰው ከሰይጣን ጋር ይደራደራል። ህወሃት እስካለ ድረስ የሚያደርጉት ጥገናዊ ለውጥ ብቻ እንደሆነና የወትሮውን ዘረኝነታቸውን አሸባሪነታቸውን ሳንዘነጋ ብሎም ሳንታክት ለ አለም አቀፉ ህብረተሰብ የምናሳውቅበት ጊዜ ነው።ወያኔም እኛም አለም አቀፉ ማህበረሰብም ባንድላይ ባንድ ጊዜ አንድን ሰው ብቻ ማድነቃችን ተጠቃሚው ህወሃት ብቻ ነው።ሚዛን የሚደፋ ከተባለ ብዙ አመታት ያስቆጠረ አዲሱ ጠቅላይ ምኒስትር ያልሸፈነው አሁንም የሚደረግ ብዙ የወያኔ ግፍ አለ።
የውሸት ፌደራሊዝም ጦስ /Falseralism :-ተአምር ከሰማይ የወረደ ያሕል ስናጋንን አገራችን ወደ ከባድ አደጋ እያመራች ነው። ዶክተር አብይ አፍሪካ ወደ አንድነት እያመራች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ የመገነጣጠል የመለያየት ምሳሌ አትሆንም ባሉን በዚህ ወቅት እንኳ ወቅትም ህወሃት ለሃያሰባት አመታት የዘራው ዘረኝነት ምክንያት ግፍ እያጨድን ነው ለምሳሌ ወቅታዊው መፈናቀል ከባሰባቸው ውስጥ:-
– በቤንሻንጉል ጉምዝ በአማራው ላይ አሰቃቂ ግድያና ማፈናቀል እስከ ብልት መስለብ
-በደቡብ ክልል በወንድማማቾቹ በጉራጌና በቀቤና መካከል የተከሰተው ግጭት
-በአፋር ሕዝብና በአማራ ሕዝብ መካከል የተከሰተው ግጭት
– በጌድዎ ሕዝብና በጉጂ ኦሮሞዎች መካከል በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው ግጭት
– በኦሮሞና በሲዳማ ሕዝብ መካከል የሚደረገው ግጭት
– የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይሎች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርጉት ግድያና ማሳደድ
– የኦሕዴድ ካድሬዎች አማራውን እያፈናቀሉ ቤቱን እያቃጠሉ እየገደሉ ማሳደድ አላቆመም።
የዚህ ሁሉ መንስኤ ብሄርና ብሄርን እያጋጨ በዳኝነት ለመቀጠል ተንኮል ጠንስሶ ብሎም አማራ ጠላት ነው መጥፋት አለበት ብሎ የተቆረቆረው ህወሃት የጎሳ ፌደራሊዝም ጦስ ነው።በየትኛውም አለም በቋንቋ ዘርን መስረት ያደረገ ፌደራሊዝም የለም።ስለዚህ የዘረ ፖለቲካን ልንቃወመው ይገባል።No to Racist Federalism ልንለው ይገባል።በወሬ ስላስመረቀነን ብቻ ዶክተር አብይን ና ጋልበን ከማለታችን በላይ በየአለሙ ሚዲያ ልናሳውቃቸው የሚገቡን ህጻኑ አማራ በመሆኑ ብቻ ብልቱ በቤኒሻንጉል መሰለቡ፤የሶማሌ ክልል ወታዶሮች በኦሮሞ ወገናቸውን ላይ የሚፈጽሙት ሬሳ ማስጎተታቸው ፤እንዲሁም በደቡብ ክልል የታየው ሬሳ ማቃጠል ሊለፈፍና ለተጎጆዎች ጠበቃ ሊቆምላቸው ይገባል።
ይህን ጽሁፍ ጨርሼ ልልክ ስል እንኳ ወያኔ የቀበረው የዘረኝነት time bomb ሌላ ቦታ ጊዜዉን ጠብቆ መፈንዳቱ አላቆመም።ዶክተሩ ኤርትራን አስታረቁ በተባለበት ማግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የበርታ ማህበረሰብ ወጣቶች ሰሞኑን ስልጠና በሰጣቸው አባይ ጸሃዬ ተወስወሰው የኦሮሞና አማራ ወገኖችን በቆመጥ በገጀራ እያባረሩ አየገደሉ ይገኛል።የሩዋንዳና ሁቱ ቱትሲ ጭፍጨፋ ምኑን ተለዬ ?ልዩነቱ በአለም አቀፍ ሚዲያ አለመዘገቡ እንጂ እምቦቀቅላ ህጻናትን አናታቸውን በቆሙበት ተርትሩ ብሎ ስልጠና የሰጣቸው አባይ ጸሃዬ እንደሁቱ መሪ በአለም ኣቀፉ ፍርድ ቤት ልክ እንደ
Ruwandan Genocide መዳኘት ያንሰዋል። የቀን ጅቦችን ሊያስር ብቅ ያለው አብይ አህመድ የሩዋንዳዉን የዘር ፍጅት ሊያብስ መሪ ሆኖ ብቅ እንዳለው ፓል ካጋሜ ሙሴ ሊሆነን ከቻለ አርቲስት ማሰልጠኑን ትቶ በቅድሚያ የዘረኝነት ትብታቡን ይበጥስልን።
ወያኔ በአለም አቀፍ ታዋቂው አሸባሪ ድርጅትየነሱን በአሸባሪነት ለመክሰስ ከሌሎች የውጭ ዜጎች ምስክርነት ካስፈለገም የኢትዮጵያ መንግስት ታክሲ ውስጥ ቦምብ አፈንድቶ በኦነግ እና በኤርትራ ያመካኛል ብለው መረጃውን ለዊኪሊክስ የሰጡትን ያንድ ወቅት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባልደረባ ጥቆማን ማየት በቂ ነው።
Wikileaks Ethiopia Files: Ethiopia Bombs Itself, Blames Eritrea: In a report from 2006 marked “Secret ; Subject: Ethiopia: Recent Bombings Blamed on Oromos Possibly the Work of GOE [Government of Ethiopia]…by: Charge [d’Affairs] Vicki Huddleston”, “An embassy source, as well as clandestine reporting, suggests that the bombing may have in fact been the work of the GoE security forces.” Cable reference id: #06ADDISABABA2708
በመስቀል አደባባይ ላይ የህዝብ ፍቅር ሲፈነዳ ቀንተው ቦንብ ያፈነዱት “ሰው ሲታረቅ ሲፈታ ደማቸው አይን የሚለብሰው” የታሪክ አተላዎች አማካኝነት መሆኑ አይጠራጥርም።።በነኤርትራ ኦነግ ወይ ግንቦት ሰባት እንዳያመካኝ ቀድመው እነሱ ሰላማዊ ያልሆነ ትግል ማቆማቸውን አውጀዋል።የቦምብ ፍንዳታውን ሊያጣራ አሜሪካ ኢትዮጵያ የገባ የአሜሪካው የስለላ ኤጀንሲ FBI በዛዉም አዲስ አበባ በድጋፍ ሰልፍ ስትቀወጥ መቀሌና ጉሙዝ ውስጥ መሽገው ቦምብ ሲያድሉ ለነበሩት እነበረከት ስምዖንን ይመርምርልን።
ከራሳቸው ከወያኔዎች አንደበት በፓርላማ ስብሰባ ላይ ዶክተር አብይ ያለውን እንዳሉት እስረኞችን በማይገባ አያያዝ ያገተው የነሱ የፍትህ ስርዓት ተቋማት ይጠየቁ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በባዶ እጁ ሰልፍ በወጣ ህዝብ ላይ ታንክ ይዞ ለፓርቲ የሚሰራ ፖሊስናወታደራዊ ተቋማት ናቸው አሸባሪዎች ያሉትንም ምስክርነት በመጥቀስ በአለም አቀፉ ወታደራዊ ፍርድቤት ይታዩ።
ህወሃት ከጥንት ጀምሮ በአለም አቀፉ የሽብር መረጃ ቋት/Global Terrorism Database(GTD) ውስጥ በአሸባሪነት ከተፈረጁት ድርጅቶች ውስጥ ስሙ እስካሁን አለ።ኢትዮጵያ ውስጥ በፈጸማቸው በምስሉ ከተጠቀሱት 10 በላይ የማፍያ ድርጊቶች እንዲሁም ለሃያሰባት አመት ሙሉ ለሰራው ወንጀል እንደ እነ አልቃኢዳ/Al Qaeida: IS ወዘተ በምዕራባውያኑ ዘንድ እንደ አሸባሪነትእንዲወገዝ ግፊት ግፊት ማድረግ ከኛ ይጠበቃል።በየሚዲያዎቻቸው በማስተጋባት። ዶክተር አብይ”አሸባሪ ግለሰብ የለም አሸባሪ ድርጅት ግን መጠየቅ አለበት” ባለውም መሰረት ዘረኛና አሸባሪ ድርጅት ህወሃት ከምድረገጽ መጥፋት አለበት።እነአሜሪካ አፍጋኒስታን ቶራቦራ ተራራ ውስጥ ተደብቆ የነበረውን ኦሳማ ቢንላደንን ለመግደል እንደደከሙት ያህል ሀገር መምራት ደረጃ ላይ የደረሰን አሸባሪ ስብስብ ወያኔህወሃትን በቀላሉ ማደን አያቅታቸውም።
ኢሰብአዊነት በወያኔ ማጎሪያ ቤት:- ቀንደኛ የለውጥ አራማጁ የዶክተር አብይ የፕሬስ ነጻነትን አስጀምራለው ያሉትን ተከትሎ ድንገተኛ ሀቀኝነት በኢቲቪ ቀርቦ ነበር።የኢቲቪ ጋዜጠኞች ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት አቅንተው የታራሚውን ብሶትና ታራሚ የሚሰቃይበትን የጨለማ እስር ቤት ቀርፆ አስተላልፏል፡ጥያቄው አዲሱ ጠቅላይ ምኒስትር በሚነግሩን ተስፋ ብቻ የግድያው የአፈናው እስር ቤት ውስጥ ታራሚዎች ስለሚፈጸምባቸው ዘገባ በኢቲቪ ሳይቀር የቀረበውን ዘግናኝ ድርጊት ችላ ብለነዋል። ራሳቸውን ያጋለጡበትን ዘገባ ሆነ የቀን ጅብነታቸውን ይፋ እያደረገ የመጣውን የለውጥ ሃይል አዎ እኛም 27 አመት ሁሉ ስንቃወም የነበረው ይሄው ነው ብሎ ለውጪው አለም ማሳውቅ አሁንስ ምን ይከለክለናል።
ስለለማ ቲም ከምናወራው ከምንጽፈው የበለጠ የህወሃትን መሰሪነት አውሬነት ዘረኝነት አሸባሪነት በየድጋፍ ስልፉ ሳይቀር ማስተጋባት ጥቅሙ ለኛው ነው። አደራዳሪዎቻችን ወይም ሃያል አገራት ህወሃት ለሽግግር መንግስት ለስር ነቀል ለውጥ የሚገፋፉት አብይን ከምንክበው በላይ ህወሃት በአሁኑ ወቅትም ቢሆን አሸባሪነቱን እንዳልተወ ስናሳስባቸው ነው።ካለበለዚያ ጥገናዊ ለውጡን ተቀበሉ ይሉናል። የፈለገ ቅን ቢመስልም አዲሱ ጠቅላይ ምንስትር አብይ አህመድ እንደ ሟቹ መለስ ዜናዊ ትግራይን ወርቃማ ህዝብ ብሎ አውጆ ሌላውን ንቋል; የሙስና ንግስት የሆነችውን አዜብ መስፍንን ሿሟል::የህወህትን ጄነራል ሳሞራን ቢሽርም የተካው ሰዓረ ያው ስለሆነ ምንም ለውጥ እንዳልሆነ መላው ኢትዮጵያውያን ብሎም መላው አለም ሊያውቀው እና ልናሳውቅ ይገባል::በሌሎች ግፊት ራሳቸውን ማጋለጥ የጀመሩ አመራሮች ፤ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው የሚለቁ ካድሬ ሹመኞች የመኖራቸውን ያህል አሁንም ቢሆን
የደደቢት ምሩቃን ለሃገር ክህደታቸው ይቅርታ ሲሉ አይታይም።ለድርድር ኢትዮጵያ የገቡ የሚገቡ ውጭ ሃገር የነበሩ ተቃዋሚዎችስ ዋስትናቸው ምንድነው።በድርድሩ ካልተስማሙ ዘው ብሎ አንደገቡ ዘው ብለው እስር ቤት አንደማይዳርጓቸው ዋስትናው ምንድን ነው። የዶክተር አብይ የድጋፍ ሰልፍ ላይ እንደተወረወረው ቦንብ አይነት ሰለባ ቢያደርጓቸውስ። ሰው እንዴት ከ አራጁ ጋር ይውላል።በግሌ ሁሉም ኢትዮጵያ ያገባኛል የሚሉ አካላት ቢወያዩ ህወሃትን አግልለው መሆን አለበት። ወቅቱ የመደመር መሆኑ እውን እንዲሆን የመገነጣጠል ህገመንግሰት ያነገበው ህወሃት ሱሱን ስሙን መቀየር አለበት።
በጥባጩ የጫካ ህግ እያለ የዲሞክራሲን ውሃ መጠጣት አይቻልም።ስለዚህ የደደቢቱ ህወሃት በቅድሚያ ይስተካከል።አብርሃም ዘሪሁን ታዬ