የኢትዮጵያን የ2016 አም አጠቃላይ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ የገመገመው አመታዊ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
(State Department) ሪፖርት ይፋ ሆነ። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2016 ዓም የኢትዮጵያ መንግስት
የጸጥታ ሃይሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከልክ ያለፈ ሃይል እንደጠተቀሙ የገለጸው ይኸው ሪፖርት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ
መገደላቸውና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን አመልክቷል።
ሪፖርቱ፣ የህዝባዊ እምቢተኝነት ተቃውሞዎች የተደረጉት በአብዛኛው በኦሮሚያና አማራ ክልሎች መሆናቸውና፣ ይህኑም ተከትሎ በታህሳስ 2016 መጨረሻ ከ10ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላ ከታሰሩት ኢትዮጵያውያን አብዛኞቹ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ሲሆን፣ የህግ አገልግሎት እንዳላገኙ ወይም ደግሞ በወንጀል ስለመሳተፋቸው ይፋዊ ክስ አልቀረበባቸውም ሲል በሪፖርቱ አስፍሯል።
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ዋቢ ያደረገው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪፖርት፣ በኦሮሚያ ስለተገደሉት 173 ዜጎች፣ እንዲሁም በአማራ ክልል በቅማንት ህዝብ ላይ ስለደረሰው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ዝርዝር መረጃ ሰጥቷል። በነሃሴ ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከ500 ሰዎች በላይ መገደላቸውን ማመናቸውንም በሪፖርቱ አካቷል። ሪፖርቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ዋቢ በማድረግ ከ800 በላይ ዜጎች መገደላቸውን አስፍሯል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብጥ ጥሰት የሚፈጸመው በጸጥታ ሃይሎች የሚደርሰው ከልክ ያለፈ ሃይል መጠቀም መሆኑን የገለጸው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪፖርት፣ እስር፣ ግድያ፣ ፖለቲከኞችን በፍርድ ቤት ማንገላታት፣ ዋና ዋና የመንግስት ድርጊቶች እንደሆነ ይተነትናል።
አመታዊ ሪፖርቱ፣ ግድያ፣ ከቤት ወጥቶ አለመመለስ፣ ሰቆቃ ፣ እና ጭካኔ የተሞላበት የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ሰብዓዊ ክብርን ማዋረድና ማንቋሸሽ፣ አሰቃቂ የእስር ሁኔታዎች መኖ፣ የግል ህይወት በሚጻረር መልኩ ግላዊ መብት መዳፈር፣ የንግግር፣ የኢንተርኔትና፣ የአካዳሚ ነጻነቶች አለመኖር፣ በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ መግባት፣ በዘር ላይ የተመሰረተ ጥቃት መፈጸም በኢትዮጵያ ጸጥታ ሃይሎች የሚፈጸሙ ጥሰቶች መሆናቸው ዝርዝሯል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት እንዳመለከተው የኢትዮጵያ መንግስት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ወንጀል የፈጸሙትን የጸጥታ አካላት ለፍርድ አለማቅረቡ ወይንም ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ አለማድረጉን በሪፖቱ አካቷል።
ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተጨማሪ የተለያዩ አገራት፣ የአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና እንዲሁም ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ እየወሰደ ያለውን መጠነ ሰፊ ግድያ፣ እስርና አፈና በተመለከተ ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
source; ኢሳት

No comments:
Post a Comment