Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, March 20, 2017

The Ethiopian prison rejects enterence of Pharmacy Tablet



የቂሊንጦው የልማድ ፋርማሲስት የዶክተሩን መድሃኒት አገደ
==================
የሆድ ድርቀትን ለመከላከል በወህኒ ቤት ለሚገኙት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ታዞላቸው ይወስዱት የነበረ Bisacodyl የተባለ መድኃኒት በቂሊንጦ እንዳይወስዱት መደረጋቸው ተሰምቷል፡፡
በቅርቡ የቀዶ ህክምና በማድረግ ወደ ቂሊንጦ ለተመለሱት ዶክተር ፍቅሩ መድኃኒቱን እንዳይወስዱ በቂሊንጦ የተከለከሉበት ምክንያት አስገራሚም አስቂኝም ሆኗል፡፡
ቂሊንጦው የልምድ ፋርማሲስት መድሃኒቱ የደም ብዛት ላለበት ህመምተኛ የሚታዘዝ ባለመሆኑና ዶክተሩም ደም ብዛት ያለባቸው በመሆኑ መድሃኒቱን ሊወስዱት አይገባም ማለቱ ተሰምቷል፡፡ዶክተር ፍቅሩ በታዘዘላቸው መድሃኒት ላይ የሚገኘው ማብራሪያ ግን መድሃኒቱ የደም ብዛት ባለባቸው ህመምተኞች ሊወሰድ እንደሚችል በግልጽ የሰፈረ ማረጋገጫ ቢኖረውም ‹‹የቂሊንጦው የልምድ ፋርማሲስት ›› አይወሰድም በማለቱ መድሃኒቱን ዶክተሩ እንዳይወስዱ ተደርገዋል፡፡
ዶክተሩ በድጋሚ በአቃቤ ህግ የቂሊንጦን ወህኒ ቤት እንዲቃጠል አድርገዋል በማለት ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት ምላሽ ወህኒ ቤቱ ሲቃጠል እርሳቸው ሆስፒታል እንደነበሩ ሲናገሩ በልምድ ፋርማሲስቱ የተመከረው አቃቤ ህግ ዶክተሩ ሆን ብለው ብዙ ቼኮላት በመብላት እራሳቸውን በመሳት ሆስፒታል የተወሰዱት ሆን ብለው ነው ››በማለት መናገሩም አይዘነጋም፡፡
No automatic alt text available.

No comments:

Post a Comment

wanted officials