Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 8, 2017

በኢራቅ ልብሱን በማውለቁ ከISIS ታጣቂ ሀይሎች የተረፈው ልጅ

በኢራቅ የISIS ታጣቂ ሀይሎች በርካታ የኢራቅ ጦር አባላትን የጨረሱት በልብሳቸው ወሰጥ በሚታጠቁት ቦምብ ነው።
በሞሱል ከተማ በነበረው የሁለቱ ሀይሎች የደፈጣ ትንቅንቅ ወጊያ መሳሪያቸውን ጥለው እጅ የሚሰጡ የሚመስሉት የISIS ታጣቂ ሀይሎች እጃቸውን ወደ ላይ ብለው ወደ ወታደሮቹ በሰላም ከተጠጉ በኋላ የታጠቁትን የአጥፍቶ መጥፊያ ቦምብ በመጫን እነሱም ይሞታሉ፤ ወታደሮችንም ይገላሉ።
በዚህ ድርጊት የተማረሩት የኢራቅ ወታደሮች በዚህ
ዙሪያ የጠረጠሩት ሰው ካለ። ገና ሰይቀርባቸው ከርቀት የተኩስ እሩምታ በመክፈት ተጠርጣሪን የሚገሉበት ሁኔታ አለ።
በጦርነት በፈራረሰችው ከተማ ወደቤቱ ለመግባት ጉዞ ላይ ባለበት ወቅት በድንገት በወታደር እንዲቆም ትዕዛዝ የተሰጠው ኢራቃዊ በተኩስ እሩምታ አካሉ ከመበሳሳቱ በፊት የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ያልታጠቀ ንፁህ ዜጋ መሆኑን መሆኑን ከቃል ማስረዳት ባለፈ በተግባር ለማሳየት የነበረው አማራጭ ልብሱን ማወላለቅ ነበር። አደረገውም ።
በዚህም ከተደቀነበት መሳሪያ የጥይት እሩምታ ተርፎ በሰላም ቤቱ መግባት ችሏል።
Like

No comments:

Post a Comment

wanted officials