ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ሞት ለህወሓት ውድቀት ለወያኔ የሚሉ መልዕክቶች በብር ኖቶች ላይ እየተፃፈ እየተሰራጨ ይገኛል።
በጎንደር ፣ባህርዳር ፣ደሴ ፣ ሞጣ፣ ደጀን ፣ ግልገልበለስ ከተሞች ላይ ተበትነው የሚገኙት የብር ኖቶች በውጭ ሃገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዩጲያውያን ወገኖቻችን የጀመሩትን "ዶላር ወደ ኢትዩጲያ ያለማላክ " ዘመቻ ለመደገፍ የታሰበ መሆኑ ታውቋል።
ወያኔ ከውጭ ሃገራት ከሚያገኘው የዶላር እርዳታ ይበልጥ በኢትዩጲያውያን የሚላከው ዶላር የውጭ ምንዛሬ በመጠቀም የምንገደልበት መሳሪያ ግዥ ሲጠቀምበት መቆየቱ ይታወቃል።
አሁን ግን አስቸኳይ ካልሆነ በስተቀር ወደ ኢትዩጲያ የሚላከው ዶላር ለወያኔ እንዳይደርስ በማድረግ ዘመቻው የተዋጣ መሆኑን በወያኔ ካድሬወች ከሚለፈፈው የዶላር እጥረት ገጥሞናል ከሚል አንደበታቸው በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። ሌላው እራሱ በሚዘውራቸው ይሁን በግል ባንኮች የውጭ ሃገር የገንዘብ ኖቶች የዘረዘረ የዕጣ ሽልማት በማዘጋጀት ደንበኞችን ለመሳብ የሚደረገው ጥረት የወያኔ ስርዓት ምንኛ በዶላር እጥረት ጠኔ መመታቱን ያሳያል። በባህርዳር የተጀመረው ይህ ዘመቻ አድማሱን አስፍቶ በተለያየ የንግድ መስመሮችና በባንክ ዝውውር ተጠቅሞ መላ ኢትዩጲያን እንዲያዳርስ የታለመ ሲሆን ተጨማሪ ከቅርብ አመት ወዲህ በወያኔ የተዘጋጀው የ1 ብር ሳንቲም የማጠራቀም ስራም በተለያዩ ነጋዴወች እየተፈፀመ ይገኛል።የባለ 5 ፣የባለ 10 ፣የባለ 50 ፣ባለ 100 ብር ኖቶች ላይ የተፃፋት መልዕክቶች "ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ፣ሞት ለህወሓት ፣ውድቀት ለወያኔ " የሚሉ መልዕክቶችን ይገኙበታል። እነዚህ የብር ኖቶች በተለያየ መንገድ ከሊስትሮ እስከ ባለስልጣን ድረስ እየተዳረሱ እንደሆነ ታውቋል።
'ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ፣ሞት ለወያኔ ' የሚል መልዕክት የተፃፈበት የባለ ሃምሳ ብር ኖት በባህርዳር አልማ ውስጥ ባለ ካፌ የደረሰው የህወሓት/ብአዴን ሰው በመናደዱ የብር ኖቱን እንደቀደደው ተሰምቷል።18 % ወለድ በዓለም ታይቶ የማይታወቅ ወለድ በገበሬው ላይ የሚጭነውና አማራጭ እንዳይኖረው በወያኔ ጥገኛ እንዲሆን ያደረገው አብቁተ የሚያስገቡ ገበሬወችም የዚህ ትግል ተሳታፊወች መሆናቸው ተረጋግጧል።

ይህ የሆነበት ምክንያት በሁለም ዘርፍ ለነፃነት ትግሉ ህዝቡ እንዲነሳ መልዕክ ለማስተላለፍ ነው። ህዝቡ ስለነፃነት ትግሉ መነጋገር እንዲኖርበት መንገድን ይከፍታል። በንግድ እንቅስቃሴ ፣በከተማ ታክሲወች ፣በሬስቶራንቶች ፣በካፌወች፣በሀገር አቋራጭ መኪናወች ወዘተ መስኮች ትግሉ በህዝባዊ ታጋዩች በውስጥ አርበኞች ለሁሉ እንዲዳረስ እንቅስቃሴው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በባህርዳር ና ጎንደር የተለያዩ ነጋዴወች በየቀኑ ባገኙት አጋጣሚ 3 የብር ኖቶች ላይ 'ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ፣ሞት ለህወሓት' በማለት ፅፈው እንደሚያሰራጩ ነግረውኛል።
የህወሓት የኢኮኖሚ መሰረቶችን ዳግም እንዳያንሰራሩ ያደረገው ህዝባዊ ትግል መልኩን እየቀየረ በሁሉም የማህበረሰብ አካል ተደራሽ እየሆነ እንደሆነ ታውቋል።
በመጨረሻም የዚህ ህዝባዊ ትግል ዘመቻ አስተባባሪወች ሁሉም ሰው በቀላሉ የሚያደርገው ና የሚሳተፍበት የትግል ስልት በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ባገኘነው አጋጣሚ የግብይይት ሂደት እንድንሳተፍ ጥሪ አስተልፈዋል።

No comments:
Post a Comment