Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, March 20, 2017

Books burned in South Africa




የመናፍቁ "መነኲሴ" ነኝ ባይ መጻሕፍት ተቃጠሉ.! ወጣቶቹ መጻሕፍቱን አፈነዱት.!

✔ ወደፊት በስም ዝርዝር የሚገለጹ የተሃድሶአውያን የመዝሙር ሲዲዎችና የኑፋቄ መጻሕፍትን የማቃጠሉ ዘመቻ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች የሆኑትና የጆሃንስበርግ መድኃኔዓለም ማኅበረ ምእመናን ወጣቶች በዛሬው ዕለት በቁጥር ከ400 በላይ የሆኑ የዚህን ሐራጥቃ መናፍቅ ፓስተር መጻሕፍት ሲያቃጥሉ ውለዋል ። ይህ በውስጡ የቅዱስ ጠበልን ፣ የቅብዓ ቅዱስና ቅብዓ ሜሮንን በአጠቃላይ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶን ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና በመንቀፍና በመቃወም ተደርሶና በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲሸጥ የነበረ መጽሐፍን ነው ዛሬ ወጣቶቹ ሲያቃጥሉ የዋሉት ።

እነዚሁ ወጣት የተዋሕዶ ልጆች ፤ በነገው ዕለት ይህን ከሃዲ እና መናፍቅ ግሪሳ ቅድስት ቤተክርስቲያን አክብራ የሰጠችውን እና እሱም እስከ ዛሬ ድረስ ሲከበርበትና ሲዘርፍበት በስሙም ሲነግድበት የኖረውን የምንኩስና ቆብ ፣ ቀሚስና ፈረጅያውን ፣ እንዲሁም ክቡር መስቀሉን በክብር በማምጣት የሚያስከብርበት ዕለት ነው ።

በዚሁም መሠረት በአዲሱ ትውልድ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ በገዛ መሪዎቻችን እመነታች መዋረዷ ይብቃ በማለት መብታቸውን በግልጽ የሚያስከብሩባት የነገው ዕለት ማለትም የዛሬዋ እሁድ የደብረ ዘይት ማግስት ዕለተ ሰኞ በመላው ዓለም ላይ በሚገኙ የእምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በጉጉትና በናፍቆት የምትጠበቅ ዕለት ሆናለች ።

ይህ መናፍቅ.! አበው መነኮሳትን የማይወክልና ሆዱ ያሸነፈው ከሃዲ ሲሆን በዚህ ከሃዲ አሳፋሪ ድርጊት የተነሳ ብዙዎች ንጹሐን አበው መነኮሳት አንገታቸውን እንደደፉና በመንፈሳዊ ተልእኮአቸው ላይም እንቅፋት እንደፈጠረባቸው በማዘን እየገለጹ ይገኛሉ ።

የመናፍቃኑም ዋና ዓላማ በመነኩሴ ስም ፣ በካህናትና በባህታውያን ፣ በዲያቆናትና በመዘምራን እንዲሁም በሰባክያነ ወንጌሎች ስም አሳፋሪ ድርጊት በየቡናቤቱ ፣ በየሆቴሉ ፣ በየአውራጎዳና ኘው ፣ በየ ጭፈራ ቤቱ ፣ በየውስኪና ድራፍት ቤቱ እየዞሩ የማይገባ ድርጊት በመፈጸም ተመልከቱ ኦርቶዶክስ ማለት እኮ እንዲህ ነው በማለት እመነቱን ማሰደብ ፣ አማንያኑን እንዲሸማቀቁና በእመነታቸውና በአባቶቻቸው ላይ አመኔታን በማሳጣት እምነት አልባም በማድረግ ወደ እነሱ ጎሬ የሚያስገቡበት አንዱና ዋነኛው ዘዴ ነው ። እናም ሊታወቅባቸውና ሊነቃባቸው ይገባል ።

አሁን ደቡብ አፍሪካዎች የማጽዳትና የቤተክርስቲያንን ክብር የማስጠበቅ ሥራ መሥራትን በግልጽ ጀምረዋል ። ከአንበሳና ከዘንዶ ጋር ታግለው በስንት የመከራና የሞት ሸለቆ ውስጥ አልፈው በእግዚአብሔር ቸርነት በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱሳን ጸሎትና ልመና ደቡብ አፍሪካ ከደረሱ በኋላ በዚያም ከሚታየው እና ከሚሰማው መዓት ሁሉ ተጠብቀው የእለት እንጀራቸውን በደስታ እንዲበሉ ያደረጋቸውን የቅድስት ቤተክርስቲያንን አምላክ በማመስገን ይህን ልዩ ተልእኮ በመፈጸም ችቦውን ለኩሰዋል ።

ይሄ ምእመናን ለቅዳሴ ሲሮጡ ከጥዋቱ 4 ሰዓት ላይ በአደባባይ ካፌ ተቀምጦ በአብይ ጾም ማኪያቶውን የሚጠጣ ድራፍቱንና ቢራውን የሚጨልጥ መለኩሴ ሁሉ ሃይ ሊባል ይገባዋል ።

ስልካችሁን ተጠቀሙበት ፣ የዘመኑ ትውልድ ካላየ ፣ ካልሰማ አላምን ባይ ነውና ያለርህራሄ ቅረጿቸው ። መነኩሴ ሆኖ በባለጌ ቢራውን እየጨለጠ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጋለሞታ ሲያሽኮረምም ቅረጹት ፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳትን ፣ የንጹሐን መምህራን ወንድሞቻችንን ክብር በሚያጎድፍ ዘልዛላ ሰባኪና አውደልዳይ ዘማሪ ነኝ ባዩን ቅረጹት ። አዎ ቅረጹትና ወደ እኔ ላኩት ከዚያ የሚሆነው ሁሉ ይሆናል ።

ሰሞኑን ለአዲስ አበባዎች የቤት ሥራ የሚሆኑ ልክ እንደ ደቡብ አፍሪካው ቀሳጢ ሃይ ሊባሉ የሚገባቸውንና መናፍቃን ሆነው በቅድስት ቤተክርስቲያን አልባሳት የሚቀልዱ ግለሰቦችን ምስል የሚያሳዩ መረጃዎችን እለቅቃለሁና በትእግስት እየጠበቃችሁን የአዲስ አበባ ወጣቶችም በማንም ላይ አካላዊ ጥቃት ሳታደርሱ እንዲሁ እንደደቡብ አፍሪካ ወንድሞቻችሁ ታደርጉ ዘንድ ይሁን ብለናል

ጎበዝ የምን ዝምታ ነው አስወልቁአቸው ። አለቀ በቃ ። አራት ነጥብ ። እስከመቼ እሹሩሩ ፣ እስከመቼ እዬዬ ። አዎ በቃ ሊባሉ ይገባል ። ይሄ ደግሞ መብት ነው ።

እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።

"ጌታ ሆይ! በሆነውና እየሆነ ባለው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ። አሜን "

"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "

ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።

ሻሎም.! ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መጋቢት 12/2009ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ ።

ሻሎም.! ሰላም.!

No comments:

Post a Comment

wanted officials